2011-11-17 10:10:32

ቤተ ክርስትያን፡ አፍሪቃን ታስባለች።


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ከነገ ወድያ ዓርብ ወርሃ ሕዳር 18 ቀነ እኤአ በምዕራባዊ አፍሪቃ ወደ ምትገኘው በኒን በመጓዝ ሐውርያዊ ዑደት ይፈጽማሉ ።

ይህ ቅድስነታቸው በበኒን የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ዑደት ሃያ ሁለተኛ ሀገራት አቀፍ ዑደት መሆኑ ነው ።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በአፍሪቃ የሚያካሄዱት ሐዋርያዊ ዑደት ሁለተና መሆኑ ነው። ከአሁን በፊት በካመሩን እና አንጎላ ሐዋርያዊ ዑደት ማካሄዳቸው የሚታወስ ነው ።

ይሁን እና በነዲክቶስ 16ኛ በኒን ላይ የሚያካሄዱት ሐዋርያዊ ዑደት ዋነኛ ጉዳይ በ2009 እኤአ እዚህ ሮማ ውስጥ ቤተ ክርስትያን ለዕርቅና ሰላም አገልግሎት ተሰይሞ የተካሄደው ሁለተኛ የአፍሪቃ ጳጳሳት ሲኖዶስ ውጤት ኤሶርታጽዮነ አፖስቶሊካ ማለት ሐዋርያዊ ሰነደ- ምዕዳን ለአፍሪቃ ጳጳሳት ለማስረከብ ፡ በኒን በተያዝነው ዓመት አሀዱ በማለት ቅዱስ ወንጌል የተሰበከበት 150ኛ ዓመት የሚከበርበት ዓመት በመሆኑ ቅድስት መንበር ላይ የወጣ መግለጫ ዘግበዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ እዚህ በቫቲካን ውስጥ በቅድስት መንበር መዋቅር የካርዲኖሎች ጉባኤ ሊቀ መንበር ሁነው ለርጂም ግዜ ያገለገሉ እና ከቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ቅርብ መንፈሳዊ እና ሰብአዊ ግንኙነት የነበራቸው አፍሪቃዊ የበኒን ዜጋ ብጹዕ ካርዲናል በርናርደን ጋንተን መቃብር ለመድረስም እንደሆ ተመልክተዋል።

የሀገሪቱ መንግስት ብፁዕ ካርዲናሉ ለበኒን እና ለአፍሪቃ ያተረፉት መልካም ስም በማድነቅ የሀገሪቱ ርእሰ ከተማ ኮቶኑ አውሮፕላን ማረፍያ ብስማቸው እንዲጠራ ማደረጉ የሚታወስ ነው።

ከብፁዕ ካርዲናል በርናርደን ጋንተን ሌላ በኒን በተለይ የካቶሊካዊት ቤተክርስትያን አገልጋዮች ያፈራች መሆንዋ እና ብጹዕ አቡነ ኢስዶሮ ሶዛ አንድ ከነሱ መሆናቸው ተገልጸዋል።

በኒን በምዕራባዊ አፍሪቃ የምትገኝ በመልክዓ መሬት አቀማመጥ ትንሽ ብትሆንም ከሚእተ ዓመት ተኩል በፊት ቅዱስ ወንጌ የበራካት በዓይን ቤተ ክርስትያን ትልቅ አፍሪቃዊ ሀገር መሆንዋ ተገልጸዋል።

ከዚህ ባሳገር ቅዱስ ወንጌል አፍሪቃዊ ባህል የተላበስበት እና ሂደቱ በመቀጠል ላይ መሆኑ ተነግረዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲቶስ በአፍሪቃ ክፍለ ዓለም ሰላም ዕርቅ እና ፍትሕ ለማንገስ የሚረዳ ሐዋርያዊ ዑደት መሆኑም ተያይዞ ተመልክተዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ በበኒን የንዑሳን አኀው ካፑቺኒ ማሕበር የበላይ ሐላፊ አባ ዳምያኖ አንጀሉቺ እንዳመለከቱት ፡ ከሃያ አራት ዓመታት በፊት በየኮቶኑ ጳጳስ ጥያቄ ሀገሪቱ ውስጥ የተመሠረት ማሕበራቸው ከሀገሪቱ ቤተ ክርስትርያን ጋር በመተባበር በትምህርት ሕክምና እና ማሕበራዊ ስራ ተሰማርቶ ይገኛል።

በኒን ድሃ ከሚባሉ ሀገራት የተመደበች ሀገር ብትሆንም ቅሉ ዓቢይ ሃብትዋ ሰላም መሆኑ መረጋጋት መኖሩ ጠቅሰው በኒን ውስጥ ጦርነት ህውከት የማይታይባት ሀገር መሆንዋ አባ ዳምያኖ አንጀሉቺ መግለጻቸው ተዘግበዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በኒን ላይ ለሶስት ቀናት የሚያካሄዱት ጉብኝት አበራታች እና ተስፋ ሰጪ በመሆኑ ህዝቡ ቅድስነታቸውን በጉጉት እተጠባበቃቸው መሆኑም የንዑሳን አኅው ካፑቺኒ የበላይ ሐላፊ አባ ዳምያኖ አንጀሉቺ ጨምረው ማስገንዘባቸው ተመልክተዋል።

በሌላ በኩል የበኒን ዜጋ ጂን ባፕቲስት ሶሩ ደራሲ እና የዩኒቨርሲቲ አስተማሪ በበኩላቸው እንደገልጡት፡ የቅዱስ ጰጥሮስ ወኪል ሐዋርያዊ ጉብኝት ራሱ ደስታ የሚፈጥር እና ትልቅ መንፈሳዊ ፍጻሜ እና የእምነት ዋስትና ስለ ሆነ እጅግ ደስ ያላል ማለታቸው ከኮቶኑ የመጣ ዜና አስታውቀዋል።

በማያያዝም የበነዲክቶስ 16ኛ ሐውርያዊ ጉብኝት ለበኒን ብቻ ሳይሆን መላ አፍሪቃ መሆኑ እና የ35 አፍሪቃ ሀገራት ረኪበ ጳጳሳት ኮቶኑ ላይ ስለሚገኙ ለአፍሪቃውያን ኩራት እና ደስታ ይቀሰቅሳል ማለታቸው ተዘግበዋል።

ደራሲው እና የዩኒቨርሲቲ መምህር ጂን ባፕቲስት ሶሩ ብጹዕ ካርዲናል ጋንተን አስታውሰው የበነዲክቶስ ሐዋርያዊ ጉብኝት በኒን ከቤተ ክርስትያን ጋር ያላትን ጥብቅ ትስስር ያስረዳል ማለታቸውም ተገልጸዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ አንድ ሱሳና ካነሊ የተባሉ የቅዱስ ኤጂድዮ ማሕበረ ሰብ አባል በቅርቡ የደረሱት የአፍሪቃ ካቶሊካውያን የተሰየመ መጽሐፍ ለጋዜጠኞች አስታዋውቀዋል።

መጽሐፉ የበኒን ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የሀገሪቱ ኮሚኒስታዊ አምባገነን ታግዶ ሥርዓተ ዲሞክራሲ ለማስፈን የተጨወተችው ሚና የሚያብራራ ነበር እና መጽሐፉ ይፋ በሆነበት መድረኽ የቀድሞ በበኒን የሮማዊት ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ሐዋርያዊ ወኪል አምባሳደር ባርቶሎሚ አዱኮኑ ጨምሮ በርካታ የቤተ ክርስትያን እና ሲቪል የሥነ ጽሑፍ ኤክስፐርቶች ተገኝተው ነበር ።

የበኒን ምሕበራዊ እኩልነት እና ዲሞክራስያዊ ምህደራ ለአፍሪቃ ሀገራት አርአያ መሆኑ በርካታ አምነውበታል ። በኒን ውስጥ ግጭት እና ሁከት የታየው ከአንድ መቶ ሀምሳ ዓመታት በፊት መሆኑ እና ይህ በበርካታ አፍሪቃ ሀገራት እንደማይታይም አስምረውበታል።

ውሁዳን ክርስትያን የሚኖሩባት በኒን ሰላም የሰፈነባት የርስ በርስ ትብብር እና መፈቃቀድ የሚታይባት የተረጋጋች ሀገር እንደሆነችም ተስማምተውበታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.