2011-11-16 13:45:28

ብፁዕ አቡነ ቶማዚ፦ አደገኛ የጦር መሣሪያ በሕይወት እና በተፈጥሮ ላይ የሚያስከትለው አደጋ


ከትላትና በስትያ ዋና መሥሪያ ቤቱ ጀነቭ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ አስከባሪ የበላይ ድርገት ሕንጻ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ አደገኛ የጦር መሣሪያ በተለይ ደግሞ ተፈናጣሪው ቦምብ መጠቀም በሰው ሕይወት እና በተፈጥሮ ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ግምት RealAudioMP3 በመስጠት ለመወሰን በሚል ርእስ ሥር በተካሄደው በድርጅቱ እራተኛው ክፍለ ጉባኤ በመገኘት ንግግር ያሰሙት በዚህ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ብፁዕ አቡነ ሲልቫኖ ማሪያ ቶማዚ፣ ተፈናጣሪው ቦምብ በሰው ሕይወት ላይ የሚያስከትለው አደጋ ከፍተኛ እና የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ውሳኔ የሚያዳክም፣ የሰው ልጅ ሕይወት እና አካባቢንም ጭምር ለከፋ አደጋ የሚያጋልጥ መሆኑ በማስመር፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፈናጣሪው አደገኛው ቦምብ እገዳ ታልሞ የሚደረገው ጥረት አለ ምንም ወጤት በመቅረቱ ምክንያት ቅድስት መንበር የተሰማትን ቅሬታ ገልጠው፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የጸረ ሰው ፈንጆች እገዳ የሚደረገው ጥረት አወንታዊ ቢሆንም ቅሉ፣ ይህ አደገኛው የጦር መሣሪያ ከሚያስከትለው የሕይወት እልቂት እና ካለው ተፈጥሮ የመበከል አቅም አንጻር ሲታይ በዓለማችን ላለ መጠቀም የሚደረገው ጥረት ጎታታ መሆኑ ብፁዕነታቸው አስገንዝበዋል።
አደገኛው ተፈናጣሪው ቦምብ መጠቀም ያስከተለው ሰብአዊ እና ቁሳዊ ችግር ብሎም የተፈጥሮ ብከላ አደጋ ለመቋቋም እና ለመቅረፍ ባለፉት አምስት ዓመታት ይህ በጀነቭ የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፍጻሜዎች የሚደነቅ ቢሆንም፣ ነገር ግን ይህ የጦር መሣሪያው መጠቀም የሚያስከትለው ጉዳት ለመጠገን የሚደረገው ጥረት በቅድሚያ በተፈናጣሪው ቦምብ የጠፋው የሰው ልጅ ሕይወት ዳግም መመለስ የማይቻል፣ ያስከተለው የተፈጥሮ ብከላ ለማስወገድ የሚጠይቀው ወጪ እና ግዜ ከፍተኛ እና ረዥም በመሆኑ አድካሚ ነው። ስለዚህ ጉዳቶችን ለመጠገን ከመራወጥ ይልቅ የጦር መሣሪያው ጨርሶ ማጥፋት አምክንዮ ያለው ውሳኔ ነው እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
የጀነቩ ድርጅት የዜጎች ደህንነት ጥበቃ የሚያነቃቃ ብሎም ዋስትና እንዲኖረው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ውሳኔ መሠረት በማድረግ የሚንቀሳቀስ ዓለም አቀፍ ድርጅት መሆኑ የጠቀሱት ብፁዕ አቡነ ቶማዚ ስለዚህ በሁሉም መስክ የሰው ልጅ ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ እንዳይጣስ የጥበቃ ኃይሉን ከፍ ያደርግ ዘንድ የሁሉም ድጋፍ እና ትብብር ያሻዋል እንዳሉ ደ ካሮሊስ ያጠናቀሩት ዘገባ ያብራራል።







All the contents on this site are copyrighted ©.