2011-11-16 13:42:53

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ እውነትን መፈለግ በጋራ የሚናከናወን ጉዞ ነው


የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ከአለማዊው ዓለም ጋር የጋራው ውይይት ለማነቃቃት “Cortile dei Gentili-የአሕዛብ ቅጥር ግቢ” በሚል መጠሪያ ያስጀመረው እና በተለያዩ አገሮች እያካሄደው ያለው ባህላዊ የጋራው ውይይት እና ዓውደ ጥናት መርሃ ግብር በመቀጠል ይኸው እ.ኤ.አ. ከህዳር 14 ቀን እስከ ህዳር 15 ቀን 2011 ዓ.ም. በአልባኒያ ርእሰ ከተማ ቲራና የማያምን ምንን ያምናል በሚል ጥያቄ RealAudioMP3 ዋና ርእስ ሥር፣ የማይታወቅ አምላክ ንዑስ ርእሰ በማስከተል “አማንያንና ኢአማንያን የድህረ ዘመናዊ ኅብረተሰብ ተጋርጦ ፊት በጋራ” በተሰኘው ቅዉም ነገር ዙሪያ የተለያዩ የሥነ ባህል ዘርፎች አማንያንና ኢአማንያን ሊቃውንት ውይይት ማካሄዳቸው ሲገለጥ፣ ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. 16ኛ የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ ፊርማ የተኖረበት ለጉባኤው ባስተላለፉት መልእክት በጋራ ወደ እውነት መጓዝ አልሞ የባህል ጉዳይ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ያነቃቃው ዓወደ ጥናት መሆኑ በማብራራት፣ እውነት የመፈለጉ ሂደት የጋራ ጎዞ መሆኑ በጥልቀት ማብራራታቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ክላውዲያ ቡምቺ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚ ይህ የአሕዛብ ቅጥር ግቢ የተሰኘው በኢአማንያንና አማንያን መካከል የሚደረገው የጋራው ውይይት በሌላው መልኩ የኅብረ ባህል ውይይት ጭምር መሆኑ የመናብርተ ጥበብ አስተማሪዎች የተለያዩ የሥነ ባህል ሊቃውንት የፖለቲካ አካላት ጭምር በቲራና መንበረ ጥበብ የጉባኤ አድራሽ በተገኙበት ባሰሙት ንግግር ገልጠዋል። በዚህ ምሁራን አካላት የአባኒያ መለያ ብዙ እክሎች በግሮ ዳግም በመኖር ዘንድ ያለው መንፈሳዊው አድማስ፣ በኮሙኒዝም የኢእግዚአብሔርነት ባህል በተስፋፋበት ወቅት የተኖረው ድብቅ ሃይማኖታዊ አድማስ፣ ዜጎች እግዚኣብሔር የሚመለክበት አቢያተ ክርስታያን ቢነፈገውም መኖሪያ ቤታቸውን ቤተ ክርስትያን በማድረግ በግል ደረጃ መንፈሳዊ አድማሱን አቅቦ ለመኖር መቻሉ፣ እና በዚህ ዓይነት መንፈስ የተኖረው ሃይማኖት ምን እንደሚመስል የተብራራበት ዓወደ ጥናት ሲሆን፣ የዚህ የአሕዛብ ቅጥር ግቢ ወጣቶችም መንፈሳዊነት ማስታወቂያ እና የመገናኛ ብዙሃን በሚል ርእሰ ሥር የክብ ጠረጴዛ ውይይት “ክርስትና የሚጠይቀው ተግባር የማይከተሉትን ነገር ግን ክርስትያን ነን የሚሉት ዜጎች እርሱም ግብረ ሃይማኖትን ችላ የማለት በወጣቱ የኅብረተሰብ ክፍል ጎልቶ የሚታይ ዝንባሌ ‘ኢአማንያንነትና አማኒያንነትን’ በማደባለቅ የሚኖረው አዲሱ ባህል፣ ሥነ ምግባር በሁሉም የሕንጸት ዘርፎች ማስተማር እና ማስፋፋት በተሰኘው እቅድ መሠረት ምላሽ ሊሰጠው ይገባል እንዳሉም ዓወደ ጥናት የተከታተሉት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ክላውዲያ ቡምቺ ባጠናቀሩት ዘገባ ያስታውቃል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለዓውደ ጥናቱ በብፁዕ ካርዲናል ራቫዚ ስም የላኩት መልእክት በቲራና የቅድስት መንበር ሓዋርያዊ ልኡክ ብፁዕ አቡነ ራሚሮ ሞሊናሪ እንግለዝ አማካኝነት ለተጋባእያኑ መነበቡም እና ቅዱስ አባታችን በመልእክቱ የዚህ ዓይነት ዓወደ ጥናት ወደ እውነት በጋራ የሚደረገው ጉዞ የሚጠይቀው ጥረት ዳግመ ኅዳሴ የሚያነቃቃ ተግባር መሆኑ ማስረዳታቸውም ልእክት ጋዜጠኛ ቡምቺ ባጠናቀሩት ዘገባ ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.