2011-11-15 12:06:24

ሥርዓተ ብጽዕና አባ ካርል ላምፐርት ፡


ትናትና ሰንበት ከቀትር በኃላ በአውስትርያ ፎርአልበርግ በቅዱስ ማርቲን ቤተ ክርስትያን በቅድስት መንበር የቅዱሳን ጉዳይ ዋና ተጠሪ ብጹዕ ካርዲናል አንጀሎ አማቶ የአባ ካርል ላምፐርት የብፅና ሥርዓት መፈጸማቸው ታውቆዋል።

የብፅዕና ስርዓቱ የተፈጸመላቸው አባ ካር ላምፐርት በናዚ ጀርመን ግዜ ብካቶሊካዊ እምነታቸው የተሳደዱ እና የሞት ሰለባ የሆኑ አባ ካርል ላምፐርት መሆናቸው ተመልክተዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ትናትና እሁድ ከምእመናን ጋር መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በደገሙበት ግዜ ብጽዕና የተቀበሉ አባ ካርል ላምፐርት በማስታወስ ካህኑ በናዚ ጀርመን አስከፊ ግዜ በእምነታቸው የተነሳ ተሳደው በሞት መቀጣታቸው አመልክተው ይህ እኩይ ተግባር የተፈጸመው አባ ካርል ላፐርት ክርስቶስ በመከተላቸው ብቻ መሆኑ አስገንዝበዋል።

ቅድስነታቸው አያይዘው እንዳመለከቱት አባ ካርል ላምፐርት የኢየሱስ ክርስቶስ እና የቅድስት ማርያም ወላዲተ አምላክ ስም እየጠሩ ብጭካኔ ለሕለፈት ተዳረገዋል። ይህ የሆነው በሁለተኛ የዓለም ጦርነት መሆኑ የሚታወስ ነው ።

በቅድስት መንበር የቅዱሳን ጉዳይ ዋና ተጠሪ ብጽዕ ካርዲናል አንጀሎ አማቶ በአውስትርያ ፎርአልበርግ ውስጥ በሚገኘው የቅዱስ ማርቲን ቤተ ክርስትያን ሥርዓተ ብፅዕና በመሩበት ግዜ እንዳመለከቱት ፡ ካርል አልበርት ከመሞቱ በፊት ለወንድሙ ዩልዩስ የጻፈለት መልእክት እንደሚነበበው በየዕለቱ በቅዱሳን ሚስጢራት በኩል ኢየሱስ ክርስቶስ ከኔ እንዳለ ተረዳሁኝ አምላክ በራእይ ተገልጾልኛል ይላል።

ኀይለኞች ችግሮች ጭንቆች መታወክ በሚከሰቱበት ግዜ ክርስቶስ እና ማርያም ባይታዩም እዚያው ቦታ እንደሚገኙ ብጹዕ ካርል ላምፐርት በተደጋጋሚ የሰበከው ስብከት መኖሩ ብጹዕ ካርዲናል አንጀሎ አማቶ ማስገንዘባቸው ተመልክተዋል።

መስዋዕትነት ከሁሉ የበለጠ ታላቅ የእግዚአብሔር ፍቅር እና የቅድስና ጉዞ መሆኑ ብፁዕ ካርዲናሉ አክለው መስበካቸው ሥርዓተ ብጽዕና የተከታተል የቫቲካን የዜና አገልግሎት ዘግበዋል።

ብፁዕ ካርል ላምፐርት ለሁላችን ክርስትያን መልካም አርአያ መሆናቸው ብጹዕ ካርዲናል አንጀሎ አማቶ ማመልከታቸው ተዘግበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.