2011-11-14 14:01:15

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፦ በቀውስ ላይ የሚገኘው ኤኮኖሚ ለአሳቢነት አድማስ ክፍት መሆን


ሁሌ በሳምት ማገባደጃ የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ በመቀጠል “የኤኮኖሚ ቀውስ ኤኮኖሚ ለአሳቢነተ አድማስ ክፍት ይሆን ዘንድ የሚጠይቅ ነው” በሚል ርእስ ሥር፣ RealAudioMP3 ትርፍ ለማካበት በገንዘብ ሃብት ለመደለብ የሚድረገው ቁጠባዊ እና ኤኮኖሚያዊ ብሎም በግምት ላይ የሚጸናው የቁጠባ ሽርጉድ ዓለማችንን እጅግ በከፋው የኤኮኖሚ ቀውስ እንዲትጥለቀለቅ ማድረጉ አብራርተው፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ካሪታስ ኢን ቨሪታተ-ፍቅር በሐቅ በተሰየመቸው አዋዲት መልእክት አማካኝነት በሰጡት ሥልጣናዊ አስተምህሮ፣ የቤተ ክርስትያን የማኅበራዊ ጉዳይ አንቀጸ ትምህርት የሚያቀርበው አማራጭ ራእይ መሠረት እኩልነት እና እድገትን ዋስትና የሚሰጡ ተቀባይነት እና ተገቢነት ያላቸው የኤኮኖሚ አማራጭ አብነቶች እንዳሉ በማረጋገጥ፣ ኤውሮጳን እያጥለቀለቀ ያለው የኤኮኖሚ ቀውስ ማኅበራዊ ውጥረት ሥጋትን እና ፍርሃት እያዛመተ መሆኑ አባ ሎምባርዲ በርእሰ አንቀጹ በማብራራት፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. በዚህ 2011 ዓ.ም. የኤውሮጳ የበጎ አድራጎት ማኅበር ዓመት ምክንያት በሮማ የተሰበሰቡትን የበጎ አድራጎት ማኅበሮች ወጣት አባላት ተቀብለው በሰጡት መሪ ቃል እንዳሰመሩበት ገልጠው፣ በግል ጥቅም ፍላጎት ተመርቶ መኖር ከሚለው ራስ ወዳነት ተላቆ ለሌላው በሚያስብ ክብር የተመራ ኑሮ ማስፋፋት ወሳኝ ነው እንዳሉ አስታውሰው፣ ፍርቅ በሐቅ በተሰኘቸው አዋዲት መልእክት ሥር እወተኛው ፍትህ መተሳሰብን እና መደጋገፍን ያካተተ መሆኑ እና ይኽ ደግሞ በገበያው እና በኤኮኖሚ ዓለም መኖር የሚገባው ክብር ኤኮኖሚ ትርፍ ከሚለው አመክንዮ ነጻ እንደሚያደረግ ማመልከታቸው አባ ሎምባርዲ በርእሰ ዓንቀጹ በማስታወስ፣ ይኽ ደግሞ የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 10 ቁጥር 8 “ያለ ዋጋ የተቀበላችሁትን ያለ ዋጋ ስጡ” የሚለው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል መሠረት ያደረገ መሆኑ አብራርተው፣ እርስ በእርስ በመተሳሰብ በመከባበር አድርግልኝ ላድርግልህ ከሚለው አመለካከት ነጻ ተወጥቶ በሰው ዘር መካከል መተማመንን በመገንባት ብቻ ነው ዓለማችንን ከተነከረበት ቀውስ የሚያላቀው በማለት ርእሰ ዓንቀጹ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.