2011-11-14 14:11:40

አሲዚ፦ የሮማ መናብርተ ጥበብ ተማሪዎች ንግደት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በየዓመቱ የሮማ ኅየንተ ሰበካ የመናብርተ ጥበብ ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የሚንከባከበው ድርገት የሚያነቃቃው የሮማ መናብርተ ጥበብ ተማሪዎች RealAudioMP3 ወደ አሲዚ የቅዱስ ፍራንቸስኮስ ከተማ መንፈሳዊ ንግደት መሠረት ትላትና 9ኛ መንፈሳዊ ንግደት ላካሄዱት ወጣቶች ባስተላለፉት መልእክት መንፈሳዊው ንግደት ክርስቶስን መከተል እና ወንጌላዊ ምስክርነት በቃል እና በሕይወት ማቅረብ የሚለው ቁርጥ ፈቃድ ዳግም የሚታደስበት እንዲሆን አደራ ማለታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
በዚህ በተካሄደው መንፈሳዊ ንግደት 4 ሺሕ ወጣቶች መሳተፋቸውም ለማወቅ ሲቻል፣ ይህ መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 26 ከቁጥር 8 እስከ 9 ባለው በተለይ ደግሞ “እቤቱ ፊትህን እሻለሁ” በሚለው ቃል ተመርቶ የተካሄደው መንፈሳዊ ንግደት እግዚአብሔር ልጆቹን ፈጽሞ ለብቻቸው እንደማይተው እና በአሁኑ ወቅት ወጣቱ ትውልድ ተስፋ ቆርጦ የአብነት ቀውስ ተከናንቦት በሚታየው ዓለም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመለየት እርሱን በመከተል እንደ ቅዱስ ፍራንቸስኮስ ሁሉን ለማግኘት ሁሉንም ለእግዝኣብሔር መተው የሚለው ከእውነተኛው አማኝ ሕይወት የሚፈልቀው ክርስቶሳዊ ቃል ለመኖር የሚደግፍ መንፈሳዊ ጉዞ መሆኑ የሚያስገነዝብ እና የሚያነቃቃ መሆኑ ለማወቅ ሲቻል፣ የእግዚአብሔር ፈቃድ ፈልጎ ለመኖር የተጠራው የሰው ዘር ይኸንን ጥሪው ችላ ከማለት የሚያጋጥመው ቀቢጸ ተስፋነት አለ ክርስቶስ እውነተኛ ተስፋ የሚሆን አለ መኖሩ የሚያረጋግጥ መሆን እና ይኸንን የላቀው መንፈሳዊነት በወጣቱ ትልድ ዘንድ እንዲሰርጽ የሚደግፍ መንፈሳዊ ንግደት እንደሆነም ሲር የዜና አገልግሎት ካሰራጨው የዜና ምንጭ ለመረዳት ተችለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.