2011-11-14 13:57:35

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ የተሟላ ጤንነት ለጸረ ሕይወት ምክንያት ሊሆን አይችልም


በአገረ ቫቲካን አዲሱ የሲኖዶስ አዳራሽ ዓለም አቀፍ የጎልማሳ ሕዋስ ጥንተ ክፍለ አካል ወይንም ሥርወ ሕይወት ሕዋስ ላይ ያተኮረ ሥነ ምርምር፣ የሰው ልጅ መጻኢና ባህል በሚል ርእስ ሥር የተመራው የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት እና የሕይወት ግንድ ለሕይወት የተሰየመው ማኅበር RealAudioMP3 በጋራ ያዘጋጁት፣ እ.ኤ.አ. ከህዳር 9 ቀን እስከ ህዳር 12 ቀን 2011 ዓ.ም. የተካሄደው ዓወደ ጥናት ተጋባእያን ባለፈው ቅዳሜ በቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ አቀባበል ተደርጎላቸው መሪ ቃል ተቀብለዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በሰጡት መሪ ቃል፣ የጎልማሳ ሕዋስ ጥንተ ክፍለ አካል ወይንም ሥርወ ሕይወት ሕዋስ ላይ የሚደረገው ሥነ ምርምር ሥነ ምግባራዊ ጥያቄዎች መሠረት ያለው ምንም አይነት ችግር የማያስከተል እና ሥነ ምርምር ለሰብአዊ እርባና አገልግሎት እንዲውል የሚያግዝ መሆኑ ጠቀሰው፣ ሆኖም ግን የሕዋስ ጥንተ ክፍለ አካል ወይንም ሥርወ ሕይወት ሕዋስ ምርምር በተመለከተ በሽል ላይ የሚደረገው ሥነ ምርምር የሕይወት መብት እና ፈቃድ የሚጥስ አደገኛ ጸረ ሕይወት ተግባር ነው በማለት እንዳስገነዘቡ፣ የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ ያጠናቀረው ዘገባ ያመለክታል።
አንዳንድ የሥነ ምርምር ክፍሎች የጤና ጉዳይ በተመለከተ የሚደረገው ጥናት እና ጤንነት በበለጠ ለማሻሻል የሚደግፍ ተስፋ ላይ ብቻ ሳይሆን እጅግ ከፍተኛ ገቢ ለማካበትም ዓላማ በማነጣጠር የሥነ ምግባር መመዘኛ እና ገደብ የማይሹ ሆነው ይገኛሉ። ስለዚህ ሕይወት የእግዚአብሔር የተቀደሰ ሥጦታ ወይንም ጸጋ መሆኑ የማይታበል እማኔ ባላት ቤተ ክርስትያን ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው አመለካከት መሆኑና መቼም ቢሆን እንደማትቀበለው ካብራሩ በኋላ፣ በጎልማሳው ሕዋስ ጥንተ ክፍለ አካል ወይንም ሥርወ ሕይወት ሕዋስ ባጠቃላይ የሕዋስ ጥንተ ክፍለ አካል ወይንም ሥርወ ሕይወት ሕዋስ ምርምር እና በሽል ላይ የሚደረገው ሥነ ምርምር መካከል ያለው የራእይ ልዩነት በትክክል በማስገንዘብ፣ ሥነ ምርምር የሰው ልጅ ያለው የማሰብ ወይንም የአዕምሮ ችሎታ በመሆኑ የሥነ ፍጥረት አስደናቂነትን፣ የተፈጥሮ የተወሳሰበው ረቂነት፣ ልዩ የሆነው የሰው ልጅ ሕይወት ያካተተ የሕይወትን ውበት የሚፈትሽ ነው። ከዚህ አኳያ ሥነ ምርምር ያለው ውበት ገልጸው፣ የሰው ልጅ የማይሞት ነፍስ የተካነ በእግዚአብሔር አርአያና አምሳያ የተፈጠረ በመሆኑም፣ ይህ የሰውብአዊው መለያ የኅልውና ስፍረት ለመገደብ ብቃት ያለው የተፍጥሮ ሥነ ምርምር ውስንነትን ልቆ የሚሄድ ነው እንዳሉ ጋዜጠኛ ደ ካሮሊስ ከጠናቀረው ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
የጎልማሳ ሕዋስ ጥንተ ክፍለ አካል ወይንም ሥርወ ሕይወት ሕዋስ ላይ ያተኮረ ሥነ ምርምር ሥነ ምግባር የሚያኖረው ገደብ የሚያከብር፣ የሰው ልጅ ክብር በመጠበቅ በማክበር እና በማነቃቃት ወደር የማይገኝለት አስተዋጽዖ ይሰጣል። ስለዚህ የጎልማሳ ሕዋስ ጥንተ ክፍለ አካል ወይንም ሥርወ ሕይወት ሕዋስ እርሱም እጣው ገና ያልተለየ እና ያልተፈጸመ መለያየት በሚል የሥነ ምርምር ሥልት አማካኝነት፣ የተለያዩ የሰውነት የውስጥ አካሎች እንዲሁም የአካል ቁራጭ እንዲሆኑ ማድረግ በሚኖረው ብቃት አማካኝነት፣ አካልን ቀስ በቀስ በሚመክን በሽታ እንዲሁም ሥር የሚሰደውን አደገኛ በሽታ ለመፈወስ ይቻል ይሆናል፣ ሆኖም ግን በዚህ ምክንያት በሽል ላይ የሚደረገው ሥነ ምርምር ምክንያታዊ ማድረግ አይቻልም። በዚህ የሥነ ምርምር ሂደት አማካኝነት የሚረጋገጠው ሥነ ፈውስ አቢይ ተስፋ ያለው ነው። ስለዚህ ከዚህ አኳያ በመነሳትም ቤተ ክርስትያን በጎልማሳ ሕዋስ የሚደረገው ሥነ ምርምር የሰው ልጅ የተሟላ ሰብአዊ ኅልውናውን የሚያከብር እና ለማኅበራዊ ጥቅም ያለመ እስከ መሆኑ መጠን ታበረታታለች ካሉ በኋላ፣ በሥነ ምርምር እና በሥነ ምግባር መካከል ያለው ግኑኝነት የሥነ ሕክምና እድገት የሰው ልጅ ሕይወት ክፍያ የሚጠይቅ የሚለው አመለካከት ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው መሆኑ ማረጋገጫ ነው። ከዚህ ሥነ ምግባራዊ ራእይ ሌላ የሥነ ሕክምና እድገት ቅንነት የተካነው ለሁሉም በእኩል ደረጃ አገልግሎት የሚሰጥ መሆን አለበት ለሚለው፣ ሁሉም የጤና ጥበቃ አግልግሎት የማግኘት መብት ለማክበር ያለመ መሆኑ ማኅበራዊ ኤኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ገጽታውን ጭምር እንዳብራሩ የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ደ ካሮሊስ ያጠናቀረው ዘገባ በመግለጥ፣ የሥነ ምርምር እድገት ለሁሉም ካለ ምንም አድልዎ እና የኤኮኖሚ አቅም ልዩነት ለመላ የሰው ልጅ አገልግሎት የሚል አላማ ያለው መሆን አለበት እንዳሉ ክተላለፈው ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.