2011-11-11 13:01:58

የፖርቱጋል ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ስለ ወቅታዊው ኤኮኖሚ


ገንዘብ ከግብር ክፍያ ነጻ በማድረግ ወይን ከግብር ክፍያ በማሸሽ የሚፈጸመው የገንዘብ ሃብት የማካበት ተግባር በርግጥ በዓለማችን አሰቃቂው RealAudioMP3 ድኽነት፣ ኢፍትሃዊነት እንዳለ የሚያረጋገጥ ነው። ስለዚህ የገንዘብ ሃብት ከግብር ክፍያ በማሸሽ የማካበቱ ሂደት እስካለ ድረስ ድኽነት እና ኢፍትሃዊነት መቅረፍ ፈጽሞ የሚቻል እንዳልሆነ የፖርቱጋል ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ማኑኤል ሞራዣው በመግለጥ፣ በፋጢማ ከተማ የተሰበሰበው የፖርቱጋል ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ስለዚሁ ጉዳይ በመምከር ይህ የኢሰብአዊነት የድኽነት እና የኢፍትሃዊነት መሠረት የሆነው አምባገነናዊ የገንዘብ ሃብት ኤኮኖሚ እንዲወገድ የሚያነቃቃ እና በዚሁ ሂደት “ተስፋ ቀውስ ባለበት ወቅት” በሚል ርእስ ሥር የተመራ የሃዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ሰነድ ይፋ እንደሚያደረግ ማረጋገጣቸው ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
የገንዘብ ሃብት እና የቁጠባው ዘርፍ በመንግሥታት ላይ ተጽዕኖ በመሆን የመምረጥ ነጻነትንም ጭምር በመንጠቅ አምባገነናዊ የገንዘብ ሃብት ኤኮኖሚ በብሔራዊ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ እያንሰራፋ ድኻው የኅብረተሰብ ክፍል ወደ ከፋው ድኽነት በመዳረግ፣ የድኻው ሕዝብ ብዛት ከፍ እንዲል በማድረግ፣ ብሎም ሃብት በጥቂቱ የኅብረተሰብ ክፍል እጅ በማስገባት እያስከተለው ያለው ማኅበራዊ ሰብአዊ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ቀውስ በቀላሉ የሚታይ አይደለም፣ ስለዚህ የፖርቱጋል ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ይኽ አምባገነናዊ የኤኮኖሚ መሥተዳድር ሥልት እንዲወገድ የሚያግዝ ሁሉም ለመተባበር እና ለመደጋጋፍ በተለይ ደግሞ በድኽነት ጫንቃ ሥር ለሚገኘው የኅብረተሰብ ክፍል ልዩ ትኩረት እንዲደረግ የሚመራ ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ሰነድ ይፋ እንደሚያደርግ እና ብፁዓን ጳጳሳት በፖርቱጋል የምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን አማካኝነት ከፖርቱጋል አዲስ መንግሥት ጋር በአገሪቱ የምርት ኤኮኖሚ ለማነቃቃት በሚደርገው ጥረት ለመተባበር ዝግጁ መሆንዋንም ጭምር ገልጠዋል ሲል ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.