2011-11-11 13:04:10

የተባበርት መንግሥታት ድርጅት ውሳኔ


ፍልስጥኤም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሙሉ አባላትነት መቀመጫ የሚያሰጣት እውቅና ጥያቄ ዙሪያ መክሮበት ለድንጋጌ ጥያቄ እንዲቀርብ RealAudioMP3 የሚያጠናቅረው የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ እና የደህንነት የበላይ ምክር ቤት የመለመለው ኮሚቴ አለ ምንም ስምምነት መጠናቀቁ የሚያመለክት ጭምጭምታ የተሰማ ቢሆንም ቅሉ፣ የኮሚቴው ሰነድ በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ እና የደህንነት የበላይ ምክር ቤት ስብሰባ ዛሬ በይፋ ቀርቦ ውሳኔ እንደሚሰጥበት ተገልጠዋል።
እ.ኤ.አ. መስከረም 23 ቀን 2011 ዓ.ም. የፍልስጥኤም ራዝ ገዝ ብሔራው መንግሥት ርእሰ ብሔር ማህሙድ አባስ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያቀረበት የፍልስጥኤም የሙሉ እውቅና ጥያቄ ከ 15 የዚህ የበላይ ምክር ቤት አባላት አገሮች ውስጥ ስምንት አገሮች የሚደገፉት መሆናቸው ከወዲሁ ሲታወቅ፣ ታላቅዋ ብሪጣንያ የምትገኝባቸው አገሮች ድምጸ ተአቅቦ የሚል ውሳኔ የሚከተሉ እንዲሁም በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የሚመሩ ተቃዋሚ አገሮች እንዳሉ ነው። ስለዚህ የበላይ ምክር ቤቱ ድጋፍ ተቃውሞ እና ድምጸ ተዓቅቦ በሚሉት አገሮች ለሦስት ተከፋፍሎ የሚገኝ ሲሆን፣ ይኽንን እግምት ወስጥ በማስገባት የፍልስጥኤም ጥያቄ ተቀባይነት የሚያሰጠው ከአስራ አምስቱ የበላይ ምክር ቤቱ አባላት ውስጥ የዘጠኝ አባላት ድምጽ የሚያስፈልገው በመሆኑ ምክንያት የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ያለው መከፋፈል እግምት ውስጥ በማስገባት ድምጽ በድም የመሻር መብት ለመጠቀም አላስፈላጊነት ያረጋገጠ መሆኑ የሥነ መካከለኛው ምሥራቅ ሊቀ ጆርጆ በርናርደሊ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በማብራራት፣ የፍልስጥኤም ጥያቄ በፍልስጥኤም ከ 2006 ዓ.ም. ምንም አይነት ሕዝባዊ ምርጫ አለ መከናወኑ አስታውሰው ስለዚህ ለውጭ ፖሊቲካ ጉዳይ ጉዳይ የሚመለከት ቢሆንም ቅሉ በክፍተኛ ደረጃ በፍልስጥኤም ውስጥ ላለው ፖለቲካዊ ሁኔታ የሚመለከት ነው ካሉ በኋላ የፍልስጥኤም ጉዳይ በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ አንገብጋቢ ሆኖ ባለው የኢራን ጉዳይ ምክንያት የተጋረደ እንደሚመስል ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.