2011-11-11 13:00:12

ቫቲካን፣ የኤውሮጳ ካቶሊክ የበጎ አድራጎት ማኅበራት ጠቅላይ ጉባኤ


በቅዱስ ጴጥሮስ ጥላ ሥር የመላ ኤወሮጳ ካቶሊክ የበጎ አድራጎት ማኅበራት ጠቅላይ ጉባኤ፣ የገላጋይነት ብቃት እና የመጻኢ እንቅስቃሴ መስተዳድራዊ መርሃ ግብር ለመወጠን የሰብአዊ እና የክርስትያናዊ እድገት የሚያነቃቃው የቅድስት መንበር የተራድዖ ተግባር የሚያሰባብረው ጳጳሳዊ ኮር ኡኑም - የውሁድ ልብ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ድጋፍ RealAudioMP3 ሥር ትላንትና መጀመሩ እና እነዚህ በዚህ በመካሄድ ላይ ባለው ጉባኤ የሚሳተፉት በተለያዩ የኤውሮጳ አገሮች በምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሥር የሚመሩት የተራድዖ ማኅበራት አስተዳዳሪዎች ብፁዓን ጳጳሳት፣ የተለያዩ የግብረ ሠናይ ድርጅት ተጠሪዎች ብፁዓን ጳጳሳት፣ የካቶሊክ ብሔራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የበጎ አድራጎት ማኅበራት ተጠሪዎች በጠቅላላ ተጋባእያን ዛሬ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ አቀባበል እንደሚደረግላቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
በዚህ ጉባኤ በመሳተፍ ላይ የሚገኙት የኤውሮጳ ኅብረት ዓለም አቅፍ የትብብር እና የሰብአዊ ድጋፍ ድርገት ተጠሪ ክርስታሊና ጆርገይቫ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በኤውሮጳ የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴ ጠንካራ እና የተዋጣለት ነው። በየዓመቱ አንድ መቶ ሚሊዮን የኤውሮጳ ዜጎች በተለያየ በኤውሮጳ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ለድጋፍ እና ለትብብር መሥክ የጉልበት እና የመዋጮ አስተዋጽዖ እንደሚለግሱ ገልጠው፣ ይህ ከጥንት እየተወራረሰ የመጣው የግብረ ሠናይ ባህል ከመቸውም በበለጠ በዚሁ የኤኮኖሚ እና የቁጠባ ቀውስ ባንሰራፋበት በአሁኑ ወቅት ለከፍተኛ የድጋፍ አስተዋጽዖ መሠረት ነው ብለዋል።
በርግጥ የክርስትናው ሃይማኖት የድጋፍ እና የትብብር በጠቅላላ የግብረ ሠናይ እንቅስቃሴ በብርታት የሚያጎላ መሆኑ ሲያብራሩ፣ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ባህል ለሌላው ማሰብ ማእከል ያደረገ የሚሠዋ ፍቅር የሚያሳስብ እና በዚህ ዘርፍ የሚያንጽ ነው። ስለዚህ በቫቲካን ይህ ዓይነት ጉባኤ ማካሄድ የተገባ አቢይ ትርጉም አለው።
ይህ በተለያዩ የበጎ አድራጎት የግብረ ሠናይ ማኅበራት የሚፈጸሙት የድጋፍ እና የትብብር እንቅስቃሴ መንግሥታት በዚህ የግብረ ሠናይ ዘርፍ ካለባቸው ኃላፊነት እዲሸሹ የሚያደርግ ተግባር ሊሆን ይችላል ወይ ለሚለው ጥያቄ ሲመልሱ፣ የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴ መንግሥታት ላለባቸው የትብብር እና የድጋፍ አቅርቦት ኃላፊነት ያበረታታል ካሉ በኋላ እ.ኤ.አ. በ 1975 ዓ.ም. 78 የተለያዩ የተፈጥሮ አደጋ ባለፈው 2010 ዓ.ም. 385 የተከሰቱት የተፈጥሮ አደጋ ምክንያት መንግሥታት የሰጡት ዘርፈ ብዙ ድጋፍና ትብብር ምስክር ነው ብለዋል።
መንግሥታት የእነዚህ የበጎ አድራጎት የድጋፍ እና የትብብር የግብረ ሠናይ ማኅበራት አስፈላጊነት በጽናት የሚያምኑበት ነው። ስለዚህ አለ እነዚህ ማኅበራት ትብብር እና ተሳትፎ መንግሥታት ይህ ዘርፈ ብዙ የድጋፍ እና የትብብር ተልእኮ ለብቻቸው የማይዘለቁት መርህ ግብር በሆነ ነበር በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.