2011-11-10 10:46:31

የተባበሩት መንግሥታት አመሪካ ጳጳሳት ቪዚታ አድ ሊሚና


የዩናይትድ ስቴትስ ካቶሊካውያን ብጹዓን ጳጳሳት ቫቲካን ላይ ቪሲታ ኣድ ሊሚና ሐዋርያዊ ጉብኝት እያካሄዱ እንደሚገኙ ቫቲካን አስታውቃለች።
የዩስ ኤስ አመሪካ ጳሳት ሐዋርያዊ ጉብኝት እስከ ፊታችን ቅዳሜ የሚዘልቅ መሆኑ የቫቲካን መግለጫ አመልክተዋል።
ዩናይትድ ስቴትስ ጨምሮ በምዕራቡ ዓለም እምነተ ሃይማኖት ከህዝባዊ ሕይወት ለማግለል ተጽዕኖ እየበዛበት መሆኑ የሚታወስ ሲሆን በስቴትስ የባርሊንግቶን ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሳልቫቶረ ሮናልዶ ማታኖ ይህንኑ ጉዳይ ትኩረት ሰጥተው እንዳመለከቱ ፡ የዩናይትድ ስቴትስ ቤተ ክርስትያን ኢየሱስ የሰጠን ቅዱስ ወንጌል ለክርስትና ሕይወት ተኪ እንደ ሌለው በመረዳት በዚሁ አኳያ ትራመዳለች።
ህዝቡ በተለይ ማሕበረ ክርስትያን ቅዱስ ወንጌል ለሰው ነፃነት እንቅፋት እንዳልሆነ በመገንዘብ ሕይወታቸው እንዲመሩ ቤተ ክርስትያን ጥረትዋ አጠናክራ እየተንቀሳቀሰች መሆናው የባርሊንጎን ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሳልቫቶረ ሮናልድ ማታኖ በማያይዝ አመልክተዋል።
እውነተኛ ነፃነት ከእግዚአብሔር የተሰጠ ነፃነት እንደሆነ ያመለከቱት ብጹዕ ጳጳሱ ክርስትያኖች ሁሉ በጥምቀት በኩል የእግዚአብሔር ቤተ ሰቦች መሆናቸው መዘንጋት እንደማይገባም አክለው ገልጠዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ቤተ ክርስትያን በትምህርት ብሕክምና እና በሌሎች የተለያዩ ማሕበራዊ ጉዳዮች ለሕብረተ ሰቡ ከፍተኛ አስተውጽኦ እያደረገች ቢሆንም እምነተ ሃይማኖት እንደ እንቅፋት የሚታይበት ጉዳይ ባይኖርም ለቤተ ክርስትያኒቱ የሚያጋጥምዋት እክሎች በሰላማዊ መንገድ መፍትሔ እንደምታገኝለት በዩ ኤስ አመሪካ የባርሊንግቶን ጳጳስ ብጹዕ ኣአቡነ ሳልቫቶረ ሮናልድ ማታኖ እዚህ ቫቲካን ውስጥ ከሰጡት መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.