2011-11-09 12:51:56

ከሱዳን ብፁዓን ጳጳሳት ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የተላለፈ ጥሪ


በሱዳን አንድ አዲስ የእርስ በእርስ ጦርነት እንዳይከሰት የዓለም አቀፍ ማኅበረስብ ድጋፍ አስፈላጊ መሆኑ የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ጥሪ ማስተላለፉ RealAudioMP3 ዜኒት የዜና አገልግሎት አስታወቀ። በሱዳን ማእከላዊ እና ምስራቃዊ ክልል ያለው ውጥረት ወደ የእርስ በእርስ ጦርነት እንዳያዘግም፣ ብሎም በጠቅላላ በሱዳን እና በደቡብ ሱዳን ጭምር የእርስ በእርስ ጦርነት መንስኤ ሊሆን ስለሚችል የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ሰላም በማክበር ዓላማ ይሳተፍም ዘንድ የሱዳን ብፁዓን ጳጳሳት ጥሪ በማቀረብ፣ በክልሉ ያለው ውጥረት እ.ኤ.አ. ከ 1983 እስከ 2005 ዓ.ም. የታየው የአንድ ሚልዮን ከግማሽ የአገሪቱ ዜጋ ሕይወት የቀጨው፣ አምስት ሚሊዮን ሕዝብ ለመፈናቀል አደጋ ያጋለጠው የእስር በእስር ጦርነት የሚያስታውስ አዝማሚያ ያለው እንደሚመስልና ውጥረቱ ገና ወደ የእርስ በእርስ ጦርነት ሳይሻገር ከወዲሁ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ለክልሉ ሰላም እና መረጋገት የተቻለውን ሁሉ እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረባቸው ዜኒት የዜና አግለግሎት አስታወቀ።
በክልሉ የሚታየው ውጥረት እ.ኤ.አ. ጥር 9 ቀን 2005 ዓ.ም. በሱዳን የተደረሰው የሰላም ስምምነት መሠረት በማድረግ የአፍሪቃ ኅብረት ሰላማዊ መፍትሄ ያፈላልግ ዘንድ የሱዳን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት አደራ በማለት፣ በሁለቱ ሱዳኖች በሚያዋስነው ክልል ሠፍሮ ያለው ተፈናቃይ ሕዝብ የሰብአዊ ድጋፍ ይቀርብለትም ዘንድ ጥሪ በማቅረብ፣ የሁለቱ ሱዳን ብፁዓን ጳጳሳትን የሚያቅፈው የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በሁለቱ ሱዳኖች ርእሰ ከተሞች ማለትም በካርቱም እና በጁባ የዋና ጸሓፊ ቢሮ እንዲከፈት ማድረጋቸውም ዜቲን የዜና አገልግሎት ያመለክታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.