2011-11-09 12:49:47

ብፁዕ ካርዲናል ራቫዚ፦ ከሥነ ሕክምና ወዲያ ማዶ መመልከት


በአገረ ቫቲካን አዲሱ የሲኖዶስ አዳራሽ ዓለም አቀፍ የጎልማሳ ሕዋስ ጥንተ ክፍለ አካል ወይንም ሥርወ ሕይወት ሕዋስ ላይ ያተኮረ፣ ሥነ ምርምር፣ የሰው ልጅ መጻኢና ባህል በሚል ርእስ ሥር የተመራ የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት እና የሕይወት ግንድ ለሕይወት የተሰየመው ማኅበር በጋራ RealAudioMP3 ያዘጋጁት፣ ዛሬ የተጀመረው የሦስት ቀናት ዓወደ ጥናት በማስመለከት ትላትና የዚህ የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚ እና የዚሁ ጳጳሳዊ ምክር ቤት የሥነ ምርምር ጉዳይ የሚከታተለው ክፍል ተጠሪ ክቡር አባ ቶማጽ ትራፍንይ እና የኒዮ ስተም የመድሃኒት ኢንዳስትሪ ስዩመ አስተዳዳሪ እና የሕይወት ግንድ ለሕይወት ማኅበር ሊቀ መንበር የሥነ ምርምር ሊቅ ሮቢን ስሚዝ በቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል አዳራሽ በጋራ ከሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ለማወቅ ተችለዋል።
የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ይህ ዛሬ የጀመረው የሦስት ቀናት ዓወደ ጥናት አቢይና ተስፋ የተጣለበት የባህል እና የሥነ ምርምር ሁኔታ ነው በማለት ሲገልጡ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የተሳተፉት የባህል ጉዳይ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚ ሥርወ ሕይወት ሕዋስ ወይም የሕይወት ግንድ የሚመለከተው ጥያቄ የሥነ ሕክምና ጉዳይ ወይም የሥነ ሕይወት ብሎም የግብረአዊነት ጥያቄ ብቻ አይደለም፣ ስለዚህ ጥያቄው ፈጽሞ ከሥነ አካል ጉዳይ ብቻ ከሚለው አመለካከት ልቆ የሚሄድ ሰፊ እና የተወሳሰበ ጥያቄ ነው።
ጥያቄው ሰፊ እና የተወሳሰበ በመሆኑ ረገድ ጠቅላይ ባህላዊ ራዕይ ወይም አስተያየት ሊኖረው ይገባል። ስለዚህ ባለንበት ዘመን የሥነ ምርምር ዘርፎች በግብረአዊነት ላይ ብቻ ሳይቆሙ የተለያዩ አስተያየቶች አቢይ ግምት እንደሚሰጡ ሲያብራሩ፣ የዚህ ጳጳሳዊ ምክር ቤት የሥነ ምርምር ጉዳይ የሚከታተለው ክፍል ተጠሪ ክቡር አባ ቶማዝ ትራፍይን የዚህ ዛሬ የተጀመረው ዓለም አቀፍ አውደ ጥናት አስፈላጊነቱ እና ዓላማው ሲገለጡ፣ የሥነ ሕዋስ ጥንተ ክፍለ አካል ምርምር ለሥነ ሰብአዊ የምርምር ጥናቶች እርሱም ለፍልስፍና ለቲዮሎጊያ ለሥነ ማኅበረሰብ ለሥነ ሕንጸት ለሥነ ባህል አቢይ ተጋርጦ ነው ካሉ በኋላ፣ በተለይ ደግሞ የሕዋስ ጥንተ ክፍለ አካል ጥናት ለተወሰኑ ሊቃውንት የሚመለከት የተራቀቀ ልዩ በእነርሱ ብቻ ሊታወቅ ሊገለጥ የሚቻል ሆኖ እንዳይቀር፣ ለሁሉም ለማስረዳት ብቃት ያለው ሥነ ምርምር እግብር ላይ ለምዋል እና ሥነ ሕዋስ ጥንተ ክፍለ አካል ጥናት በተመለከተ በተለያዩ ሥነ ምርምር ሊቃውንት ማኅበረሰብ እና በተራው ህዝብ መካከል ግኑኝነት እንዲኖር፣ የዚህ የሥነ ሕዋስ ጥንተ ክፍለ አካል ምርምር ከመላ ጎደል ሁሉም እንዲረዳው ማድረግ የሚል መሆኑ አብራርተዋል።
የሥነ ምርምር ሊቅ ሮቢን ስሚዝ በበኩላቸው በዚህ በምንኖርበት ዓለም በአሁኑ ወቅት 12 ሚሊዮን 700 ሺህ የነቀርሳ በሽታ፣ 346 ሚሊዮን የስኳር በሽታ፣ ሌሎች 583 ሚሊዮን በበሽታ መቋቋም ብቃት ማነስ የተጠቁ ኅሙማን እንዳሉ ጠቅሰው ከዚህ ከተሰጠው ተጨባጭ አኃዛዊ መግለጫ ቁጥር መስተጀርባ ሰው ነው ያለው፣ ስለዚህ የጎልማሳ ሕዋስ ጥንተ ክፍለ አካል ወይንም ሥርወ ሕይወት ሕዋስ እርሱም እጣው ገና ያልተለየ እና ያልተፈጸመ መለያየት በሚል የሥነ ምርምር ሥልት አማካኝነት፣ የተለያዩ የሰውነት የውስጥ አካሎች እንዲሁም የአካል ቁራጭ እንዲሆኑ በማድረግ የሥነ ምርምር ሂደት በመጠቀም ፈውስ ሊገኝላቸው የሚቻል በመሆኑ ገልጠው፣ ስለዚህ ይህ የሥነ ምርምር ዘርፍ ያለው እምቅ ኃይል እግብር ላይ እንዲውል ለምደረግ ያለመው የሥነ ምርምር ሂደት ውጤት ገና ቢመስልም ቅሉ ሩቅ ባልሆነ ጊዜ ውስጥ ተጨባጭ ሊሆን እንደሚችል ነው። ስለዚህ ይህ የሥነ ምርምር ሂደት በቀላሉ የሚገመት ባለ መሆኑም። የተገባ አጠቃቀሙ ከወዲሁ መለየት እጅግ ወሳኝ ነው ብለዋል።
የዚህ ዓወደ ጥናት ተሳታፊዎች እፊታችን ቅዳሜ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ቫቲክን በሚገኘው ሐዋርያዊ ሕንጻ አቀባበል እንደሚደረግላቸውም የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.