2011-11-08 10:06:55

የር.ሊ.ጳ የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ


ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፤ የዛሬው እሁድ ሥርዓተ አምልኮ የሚያቀርበው የቅዱስ መጽሐፍ ምንባቦች ባለፈው ሳምንት ባስተወስናቸው የሁሉም ቅዱሳንና የሁሉም ሙታን ዕለታት የጀመርነውን የዘለዓለማዊ ሕይወት አስተንትኖ እንድንቀጥል ጥሪ ያቀርቡልናል፣ በዚህ ነጥብ ላይ በሚያንና በማያምን መሀከል ያለው ልዩነት ጥርት ብሎ ይታያል። በሌላ አነጋገር ተስፋ ባለው ተስፋ በሌለው ለማለትም ይቻላል፣ ለዚህም ነው ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ “ወንድሞች ሆይ፥ ተስፋ እንደሌላቸው ሰዎች እንዳታዝኑ፥ ስለ ሞቱት ሰዎች እውነቱን እንድታውቁ እንወዳለን፣” (1ተሰ 4።23)፣ በዚህ ረገድ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ያለን እምነት ቊርጥ መለያችን ነው፣ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ኤፈውሶን ሰዎች ሲጽፍ ሁሌ መልካም ዜናን ከመቀበላቸው በፊት ተስፋ ቢስና በዓለም ውስጥ እግዚአብሔር ያልነበራቸው ሰዎች መኖራቸውን ያስታውሳቸዋል (2፤12)፣ ጥንታዊው የግሪካውያን እምነትና የአረማውያን አምልኮና አፈ ታሪክ የሞት ምሥጢር ሊገልጹት አልቻሉም፣ በጥንታዊው ጽሑፋቸው “ኢን ኒሂል አብ ኒሂሎ ኳም ቺቶ ረቺዲሙስ - ከኢምንት ወደ ኢምንት ተሎ ብለን እንወድቃለን” ይላል፣ እግዚአብሔርን ከሕይወታችን ያወገድን እንደሆነ ክርስቶአስ ከሕይወታችን ያወገድን እንደሆነ ዓለማችን ወደ ኢምንትና ጨለማ ይሰጥማል፣ ይህ ሁኔታ በዘመናችን ባሉ በኢምንት በሚያምኑ በተለይ ብዙ ወጣቶችን በሚበክል ደንታ ቢስ ኢምንትነት ይታያል፣
በዛሬ ዕለት የቀረበልን ወንጌል ትልቅ ምሳሌ ይሰጣናል፣ የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ በሆነ የሠርግ በዓል እንዲሳተፉ ጥሪ ስለተደተገላቸው አሥሩ ደናግል ይናገራል (ማቴ 25፤1-13)፣ ምሳሌው ደስ የሚያሰኝ ነው፣ ጌታ ኢየሱስ በዚሁ ምሳሌ አንድ ሁሌ የሚያከራከርን እውነት ያስተምረናል፣ ከአሥሩ ደናግል አምስቱ በበዓሉ ተገኝተዋል። ምክንያቱም ሙሽራው ሲደርስ መብራቶቻቸውን ለማብራት በቂ ዘይት ነበራቸው፣ የቀሩት አምስት ደናግል ግን ውጭ ቀርተዋል። ምክንያቱም በቂ ዘይት አላመጡም፣ በሰርጉ በዓል ለመሳተፍ መሠረታዊ አስፈላጊነት ያለው ይህ ዘይት ምን ያመለክታል፤ ብለን የጠየቅን እንደሆነ ቅዱስ አጎስጢኖስና ሌሎች ጥንታውያን ጸሐፊዎች የዚህ ዓይነት ጥሪ የፍቅር ምልክት ሆኖ በገንዘብ ሊገዛ የማይቻል ሆኖም ግን እንደሥጦታ የምትቀበለውና በልብህ በመያዝ በተግባር የሚገለጽ መሆኑን ያመልክታሉ፣ እውነተኛ እውቀት ገና በሕይወት እያሉ የምሕረት ሥራዎች ማድረግ ነው። ምክንያቱም ከሞት በኋላ እነኚህን ማድረግ አይችላምና፣ ለመጨረሻው ፍርድ ከሞት በምንነሣበት ግዜ የምንፈረደው በምድር ሕይወታችን ባደረግነው የፍቅር ሥራ መሠረት ሊሆን ነው (ማቴ 25=31-46)፣ ይህ ፍቅር የክርስቶስ ሥጦታ ሆነ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በእኛ ላይ ይሠርጻል፣ ፍቅር በሆነው በእግዚአብሔር የሚያምን ሁሉ የማይሸነፍ ተስፋ ይዞ ይጓዛል፣ ይህ ተስፋ ከሞት ወዲያ ያለወን የሌሊት ጨለማን ለመሻገርና በትልቁ የሕይወት ድግሥ ለመድረስ እንደ መብራት ያገልግለናል፣
መንበረ ጥበብ የሆነችውን እመቤታችን ድንግል ማርያም በኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ የለበሰውን እውነተኛው ጥበብ እንድታስተምረን እንለምናት፣ ኢየሱስ ከዚህ ዓለም ሕይወት ወደ ዘለዓለማዊ በእግዚአብሔር የሚገኝ ሕይወት የሚያደርስ እውነተኛ መንገድ ነው፣ እርሱ እግዚአብሔርን ገለጠልን ፍቅር የሞላው ተስፋም ሰጠን፣ ለዚህም ነው ቤተ ክርስትያን እናትዋ ለሆነችው ደንግል ማርያም ሰላም ለኪ ኦ ንግሥት ብላ ስትጸልይ “ኦ ጥዕምት ሕይወትነ ወተስፋ መድኃኒትነ - ጣፋጪቱ ሕይወታችንና የመድኃኒት ተስፋችን” ሰላም ላንቺ ይሁን ስትል የምትጠራት፣ በማይሳሳት ተስፋ ለመኖርና ለመሞት ከእርስዋ እንማር፣
ጥሪ
    ናይጀርያ። “ባለፉት ቀናት በናይጀርያ የተፈጸሙትን አዛሳኝ ሁኔታዎች እየተከታተልኩኝ ነው፣ የአደጋው ሰለባ ሆነው ሕይወታቸውን ላጡ ስጸልይ፣ በአማኞችም ሳይቀር ጥላቻና መከፋፈል በማስከተል ችግሮችን የሚያባብስ እንጂ መፍትሔ የማያመጣ ይህንን ዓመጽን ወዲያውኑ እንዲያቆሙ እማጠናለሁ፣”
    ጀኖቫ “ኃሳቤ በዛሬው ዕለት በውኃ መጥለቅለቅ አደጋ እጅጉን ለተጐዳችው የጀኖቫ ከተማ ሳላስታውስ ለማለፍ አልችልም፣ የአደጋው ሰለባ ለሆኑት በጸሎቴ አስባቸዋለሁ እንዲሁም ስለ ቤተ ሰቦቻቸውና በአደጋው ብርቱ ጉዳት ስለ ደረሰባቸውም እጸልያለሁ፣ የጥበቃ እመቤታችን ተወዳጁን የጀኖቫ ሕዝብ ይህንን ፈተና እንዲያሸንፉ ትደግፋቸው፣”









All the contents on this site are copyrighted ©.