2011-11-07 14:11:36

ጳጳሳዊ ረጂና አፖስቶሎሩም መንበረ ጥበብ


እ.ኤ.አ. ከ ህዳር 9 ቀን እስከ ህዳር 11 ቀን ሮማ በሚገኘው ጳጳሳዊ ረጂና አፖስቶሎሩም መንበረ ጥበብ “የሥነ አካል ቲዮሎጊያ” በሚል ርእስ ሥር ዓውደ ጥናት እንደሚካሄድ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
አካል በተለያዩ የሥነ ምርምር ዘርፍ የሚሰጠው ራእይ የተስተካከለ እንዲሆን አካል ያለው ክብር እና አስደናቂ መሆኑን በድህነት እቅድ ያለው ሚና ለማበከር ያቀደ የሥነ አካል ቲዮሎጊያ አውደ ጥናት የሥነ ሕይወት ሥነ ምግባር፣ የፍልስፍና የሥነ ሕግ፣ የሥነ ቅዱስ መጽሓፍ፣ የሥነ ሰብአዊነት፣ የቲዮሎጊያ የሥነ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ፣ የሥነ ጥበብ የሥነ መገናኛ ብዙኃን ሊቃውንት የሚያሳትፍ መሆኑ የዜና አገልግሎት በመጥቀስ፣ እ.ኤ.አ. ህዳር 10 ቀን 2011 ዓ.ም. የሥነ አካል ቲዮሎግያ በር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ አስተሳሰብ በሚል ርእስ ሥር የኢጣሊያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክት ሊቀ መንበር የፍልስፍና ሊቅ ሮኮ ቡቲሊዮነ ሰፊ አስተምህሮ ቀርቦ፣ በዚሁ ርእስ ሥር ሰፊ ውይይት ከተካሄደ በኋላም እ.ኤ.አ. ህዳር 11 ቀን 2011 ዓ.ም. የሥነ አካል ቲዮሎጊያ እና ዳግመ አስፍሆተ ወንጌል በሚል ርእስ ሥር የዳግመ አስፍሆተ ወንጌል ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ሳቪዮ ሆን ታይ ፋሪ በመቀጠልም የሥነ አካል ቲዮሎጊያ እና ጤና ጠበቃ በሚል ርእስ ሥር የጤና ጥበቃ እና የጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎች ሐዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ዝይግሙንድ ዞሞውስኪ አስተምህሮ እንደሚያቀርቡ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.