2011-11-07 14:10:00

በኒን እና ቅድስት መንበር


በቅድስት መንበር የቤኒን ልኡከ መንግሥት ልዩ አሳቢነት መሠረት ቤኒን እና ቅድስት መንበር በሚል ርእስ ሥር ያችን አፍሪቃዊት አገር በሚገባ ለማወቅ እና ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ከህዳር 18 ቀን እስከ ህዳር 20 ቀን 2011 ዓ.ም. በእዚያች አገር የሚያካሂዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት ያለው የላቀው ቅዱስ ዓላማ የሚያጎላ በፈረንሳይኛ ቋንቋ የተደረሰው መጽሓፍ በቫቲካን ማተሚያ ቤት ታትሞ በራዲዮ ቫቲካን ሕንፃ በ 1980 ዓመታት በበኒን የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ በመሆን ያገለገሉት የአገረ ቫቲካን መስተዳድር ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ጁዘፐ በርተሎ በተገኙበት በራዲዮ ቫቲካን ማርኮኒ መለስተኛ የጉባኤ አዳራሽ ለንባብ መብቃቱ የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።
ብፁዕነታቸው ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ቤኒን በማርክሲዝም ሌሊኒዝም ርእዮት ተከታይ ነበር አምባ ገነን መንግሥት ሥር ያሳለፈችው አስከፊው የቅድመ የእርስ በእርስ ጥርነት ሁኔታን ዘክረው፣ የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ረገጣ እርሃብ ያስፋፋ ሁኔታ እንደነበርም አስታውሰው፣ በአገሪቱ ሰላም እና መረጋጋት የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ጥበቃ መከበር በተደረጉት ግሥጋሴ የቤተ ክርስትያን አቢይ አስተዋጽዖ ነፍሰ ኄር ብፁዕ አቡነ ደ ሱዛ እና እ.ኤ.አ. ግንቦት 13 ቀን 2008 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት የተለየት ብፁዕ ካርዲናል ጋንቲን ጠቅሰው እ.ኤ.አ. በ 1982 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በቤኒን ያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት በአገሪቱ አንሠራፍቶ ለነበረው ጸረ ቤተ ክርስትያን አመለካከት እና ተግባር እንዲያከትም ፈር ማስያዙ እና በመቀጠልም በ 1992 ዓ.ም. የፈጸሙት ሐዋርያዊ ጉብኝት በአገሪቱ ለዓቢይ ዘርፈ ብዙ ለውጥ መሠረት ተብለው ከሚጠቀሱ የታሪክ ምዕራፎች ናቸው። የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በበኒን የሚፈጽሙት በእቅድ ተይዞ ያለው ሐዋርያዊ ጉብኝት በኒን እና የቤኒን ሕዝብ በጉጉት የሚጠባበቀው ለአፍሪቃ የሚናገር እንደሚሆንም ገልጠው የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.