2011-11-04 14:09:22

ደቡብ ሱዳን፦ የካቶሊክ ራዲዮ ጉድ ኔውስ


በሆላንድ የተቋቋመው ገና በማደግ ላይ በሚገኙት አገሮች በመገናኛ ብዙኃን መስክ አቢይ አገልግሎት የሚሰጡ እና ለነዚያ አገሮች የመገናኛ ብዙሃን RealAudioMP3 እድገት ድጋፍ የሚሰጡ በሁሉም መስክ ለአወንታዊው ባህል ሕንጸት አቢይ ሚና የሚጫወቱትን በመለየት እና በመምረጥ በየዓመቱ ፍሪ ቮይስ ነጻ ድምጽ የሚል ሽልማት የሚያዘጋጅ መንግሥታዊ ያልሆነው ድርጅት የ2011 ዓ.ም. የፍሪ ቮይስ-የነጻው ድምጽ ሽልማት አሸናፊ በደቡብ ሱዳይ የሩምበክ ሰበካ “ጉድ ኔውስ” ለካቶሊክ ረዲዮ ጣቢያ መሆኑ ይፋ ባደረገበት መልእክት፣ እ.ኤ.አ. ሓምሌ 9 ቀን 2011 ዓ.ም. በይፋ ሉአላዊነቷ ለታወጀላት ደቡብ ሱዳን ሉአላዊነቷ በይፋ ከመታወጁ በፊት ለሰላም ባህል ግንባታ እና የደቡብ ሱዳን ሕዝብ የጋራው ዓላማ በሁሉም እንዲታወቅ በማድረጉ ሂደት የሰጠው አገልግሎት መሆኑ በማስመር፣ የሽልማቱ ባለቤት የሆኑት የዚህ የጉድ ኔውስ ራዲዮ ጋዜጠኛ አዉት ማቦክ አኮት ሴት ጋዜጠኛ ሲሆኑ ከሚሰጣቸው የአንድ ሺሕ ስተርሊን ሌላ ከሌልች 10 የዚህ ራዲዮ ጣቢያ ጋዜጠኞች ጋር በመሆን የከፍተኛ የሥነ መገናኛ ብዙኃን ሕንጸት ዕድል እንደሚሰጣቸውም ታውቀዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ጉድ ኔውስ ራዲዮ ጣቢያ እ.ኤ.አ. ጥር 24 ቀን የጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙሃን ሠራተኞች ጠባቂ ቅዱስ ፍራንቸስኮ ዘ ሳለስ ዓመታዊ ክብረ በዓል በተከበረበት በ 2010 ዓ.ም. እንደነበርም የሚዘከርም ነው።








All the contents on this site are copyrighted ©.