2011-11-04 14:07:01

የታንዛኒያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት፦ የቁጠባው ቀውስ እና መንስኤው


የታንዛኒያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የፍትህ እና የሰላም ድርገት በቅርቡ ጳጳሳዊ የፍትሕ እና ሰላም ምክር ቤት ዓለም ሓቅፍ ሕዝባዊ ሥልጣን ምሥረታ አስፈላጊነቱ RealAudioMP3 ያመነ የገንዘብ ሃብት የማስተዳደር ደንብ ኅዳሴ ማረጋገጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀስቅሶ ላለው የኤኮኖሚ ቀውስ መፍትሔው ይሆናል በማለት ያቀረበው ሰነድ በማስደገፍ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 24 ቀን 2011 ዓ.ም. ማኅበራዊ ጥቅም የሚያስቀድም እና የጋራው ጥቅል ለማረጋገጥ ያለመ፣ የጋራ ጥቅም የሚል ትርጉም ያለው ኃላፊነት ውሳኝ እና አስፈላጊ ነው በሚል ርእስ ሥር ባወጣው መግለጫ፣ ወቅታዊው የዓለም የኤኮኖሚ መርሃ ግብር የሰው ልጅ ደንበኛ ወይንም ተገልጋይ እርሱም ባለው የተጠቃሚነት ባህርይ ላይ ብቻ ሳያቶክር፣ ምሉእ መሆናዊው ሰብአዊነቱንም ጭምር ማክበር ማእከል የሚያደርግ መሆን እንዳለበት በማብራራት፣ ሥነ ቁጠባ ወይንም ኤኮኖሚ ግብረ ገብ የማያጠቃልል ከብግረ ገብ ነጻ የሆነ ሉኣላዊነት የለውም፣ ስለዚህ የሰው ልጅ ማእከል ያደረገ በእውነት ላይ የጸና መሆን እንዳለበት በማብራራት፣ በርግጥ በአሁኑ ወቅት የሚታየው የኤኮኖሚ እና የቁጠባው ቀውስ በቅድሚያ የገንዘብ ሃብት ቀውስ ሳይሆን ስግብግብነት ልቅ ራስ ወዳድነት ያስከተለው የግብረ ገብ ቀውስ ነው ይላል።
ገበያ ለሰው ልጅ አገልግሎት እርባና ላይ ያቀና ሆኖ ሥነ ምግባር እና ፖለቲካ ከቁጠባ እና ከኤኮኖሚ በላይ መሆን አለባቸው። ስለዚህ የገንዘብ ሃብት እና የገንዘብ ይዞታ በጠቅላላ ገንዘብ አለ ሥነ ምግባር እና ተገቢ ፖለቲካ የሚያስከተለው ችግር በዓለማችን እየታየ ነው። ኤኮኖሚን ሰብአዊነት ማልበስ አስፈላጊ መሆኑ የታንዛኒያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የፍትሕ እና ሰላም ድርገት ባወጣው መግለጫ በመጥቀስ፣ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ባንክ ቤት ብቻ ማቋቋም ሳይሆን በማያያዝ ዓለም አቀፍ የግብረ ገብ አስከባሪ ድርጅት ማቋቋም አስፈላጊ ነው። ሰለዚህ የማኅበረሰብ ኃላፊነት የሚሰማው በግረ ገብ የሚመራ የፖለቲካ መሥተዳድር መረጋገጥ ይኖርበታል። እንዲህ ካልሆነ ግን የተከሰተው የገንዘብ ሃብት ቀውስ ለማስወገድ የሚቀርበው መፍትሔ ጊዚያዊ ብቻ ሆኖ፣ ያለው ቀውስ ከነበረበት ደረጃ ካፍ ብሎና አይሎ ዳግም እንዲከሰት ምክንያት እንደሚሆን የታንዛኒይ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የፍትሕ እና ሰላም ድርገት መግለጫ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.