2011-11-04 15:58:36

ርሊጳ በነዲክቶስ ከዚህ ዓለም ለተለዩት ካርዲናላት እና ጳጳሳት ሥርዓተ ቅዳሴ አሳረጉ ፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ትናትና ከቀትር በኃላ

በቅዱስ ጰጥሮስ ካተደራል በታች በሚገኘው የቫቲካን ዋሻ በዚሁ በተያዝነው ዓመት 2011 እኤአ ከዚህ ዓለም ስለተለዩት ብጹዓን ካርዲናልት እና ጳጳሳት መሥዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው ቫቲካን ላይ የወጣ መግለጫ አስገንዝበዋል።

በርካታ ካርዲናላት ጳጳሳት ካህናት እና ገዳማውያን በዚሁ በነዲክቶስ 16ኛ ያሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ተሳታፊ መሆናቸው መግለጫው አመልክተዋል።

እንደሚታውሰው ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን በዚሁ በተያነው ሳምንት መጀመርያ ላይ በቅደም ተከተል የቅዱሳን እና ሙታን ዕለት አስባ እና አክብራ ውላለች።

ለአንድ ክርስትያን የእግዚአብሔር መድኅን ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ አገልግሎ እና አክብሮ መሞት የእምነት ተስፋ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ በቫቲካን በቅዱስ ጰጥሮስ ካተድራል ትሕተ መሬት በሚገኘው ዋሻ ውስጥ ሥርዓተ ቅድሴ በመሩበት ግዜ ባሰሙት ስብከት አስገንዝበዋል።

በዚሁ በተያዝነው ዓመት 2011 እኤአ አስር ካርዲናላት እና በርካታ ጳጳሳት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው የሚታውስ ነው።

የብጹዓን ካረዲናልት እና ጳጳሳት ሕልፈት ስናስታውስ አሉ ቅድስነታቸው ስሜታችን እንደሚቀሰቀስ እና ሰብአዊ ሁኔታን ማሰባችን አይቀሬ ነው ማለታቸው ተዘገበዋል።

የሞት ፍርሐት እና ብሎም የገሀነመ እሳት ቃጠሎ በእግዚአብሔር ፍቅር እንደሚተካ መዘንጋት እንደሌለብን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለኛ ተስቃይቶ ተሰቅሎ ሞቶ መነሳቱ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ መስበካቸው ተነግረዋል።

ሞት በኢየሱስ ክርስቶስ እና በጥምቀት በኩል ከሱ ጋር ከተሳሰሩ ሰሰዎች ላይ ማኝኛውም ኃይል እንድሌለውም ቅድስነታቸው አክለው መግለጣቸው ተመልክተዋል።

ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ ያስገነዘበው ጠቅሰውም ፡ ከክርስቶስ ጋር ከሞትን ከሱ ጋር እንንነሳለን ብለዋል ቅድስነታቸው ።

ከሞት በኃላ ያለውን ሕይወት በመድኅን ክርስቶስ ብቻ እንደሚረጋገጥ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በማያያዝ ማመልከታቸው በዚሁ በተያዝነው ዓመት ከዚህ ዓለም በሞት ለተለዩ ብጹዓን ካርዲናላት እና ጳጳሳት

በቅዱስ ጰጥሮስ ካተድራል በታች በሚገኘው የቫቲካን ዋሻ ውስጥ በቅስነታቸው ተመርቶ የተካሄደውን መሥዋዕተ ቅዳሴ የተከታተሉ የቫቲካን የዜና ኣውታሮች አስታውቀዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በዚሁ በርካታ ብጹዓን አበው መኒኲስያት እና መነኮሳን የተገኙበት በቫቲካን ዋሻ ውስጥ የተካሄደው ሥርዓተ ቅዳሴ የተከታተሉት የቫቲካን የዜና አውታሮች እንዳስገነዘቡት ፡

አለ የመድኅን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል የፍጥረታት ሁሉ ኀይል የሐጢአት ኀይል ለመቋቋም ባልቻለ ነበር ።

ከሄሉ ኩሉ እግዚአብሔር ከሰው እውቀት በላይ መሆኑ ማውቅ መረዳት መገንዘብ ማስተዋል እንደሚገባም ማመልከታቸው የዜና አውታሮቹ ለጠቀው አስታውቅዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.