2011-11-04 14:10:52

መካከለኛው ምሥራቅ፣ ጅምላዊ ቅድመ ጥላቻ የሚያገል የሰላም ባህል


የስእራኤል የመከላከያ ኃይል ትላንትና በጋዛ ሰርጥ ክልል የሰነዘሩት የወራራ ጥቃት እስራኤልን እና ጋዛን በሚያዋስነው ክልል በቀሰቀሰው የቶክስ ልውውጥ ሳቢያ RealAudioMP3 ሁለት የፍልስጥኤም ዜጎች ለሞት መዳረጋቸው ሲገለጥ፣ በሌላው ረገድም የእስራኤል ባህር ኃይል ወደ ጋዛ ያቀኑ ሁለት የሰብአዊ እርዳታ አቅራቢ መርከቦች ከቱርክ የተነሱ እንዳሉ በመለየት አግቶ በቁጥጥር ሥር ለማዋል ዝግጁ መሆኑ ከወዲሁ አስጠንቅቀዋል።
በነዚህ ባለፉት ቀናት የተባበሩት መንግሥታት የሕንጸት የሥነ ምርምር እና የባህል ጉዳይ የሚንከባከበው ድርጅት ለፍልስጥኤም አገራዊ እውቅና በይፋ ከሰጠ በኋላ እስራኤል ባሽቸኳይ በዮርዳኖስ ምዕራባዊ ዳርቻ ክልል የእስራኤል መንደሮች ግንባታ እቅድ እግብር ላይ ለማዋል እና ግንባታው ለማቀላጠፍ የሰጠችው ውሳኔ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ ያለው ውጥረት እጅግ እንዲከር ማድረጉ ለማወቅ ሲቻል፣ እስራኤል ለተባበሩት መንግሥታት የሕንጸት የሥነ ምርምር እና የባህል ጉዳይ የሚንከባከበው ድርጅት የምትሰጠው የገንዘብ መዋጮ እንደምታቋርጥ በይፋ አስታውቃለች።
ይኽ በመካከለኛው ምሥራቅ እያየለ በመሄድ ላይ ያለው ውጥረት የቅድስት መሬት ክልል ማኅበረ ክርስትያን በክልሉ ለመኖር ያላው ተስፋ እንዲመነምን እያደረገ መሆኑ ሲገለጥ፣ ጉዳዩ በማስመልከትም በመካከለኛው ምሥራቅ የላቲን ሥርዓት የሚከተሉትን አቢያተ ክርስትያን የሚያቅፈው የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ አባ ፒየሮ ፈለት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በአረብ ክልል አገሮች የሚገኙት ማኅበረ ክርስያን የሚጠይቁት የህሊና የሃይማኖት ነጻነት ነው። አለ ምንም ሥጋት ሃይማኖታቸውን በግል እና በማኅበር ደረጃ የመኖር ነጻነትን ነው የሚጠይቁት። የክልሉ ህዝብ አለ ምንም የኃይማኖት ልዩነት ክርስትያን ሙስሊም እና የሌሎች ሃይማኖት ተከታዮች ጭምር የአረብ ታርክ ክፍል ናቸው። ስለዚህ የአረብ ባህል እና ታሪክ ሲባል ሁሉንም በአረብ አገሮች ክልል የተለያየ ባህል የተለያየ ሃይማኖት የሚከተል ሕዝብ ያቀፈ ነው።
የክልሉ ማኅበረ ክርስትያን ባካባቢው የሚያየው ሁኔታ ለሰላም የሚደረገው ጥረት ኮሳሳ በመሆኑ ያለው ተስፋ እየመነመነ ክልሉን ለቆ የመውጣቱ ውሳኔ እንደ አማራጭ እየተጠቀመበት ነው። ሰለዚህ በመካከለኛው ምሥራቅ ሰላም እንዲረጋገጥ ከተፈለገ አለ ጅምላዊ ቅድመ ጥላቻ የሚል ሁሉም የሃይማኖት ነጻነት የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ውሳኔ የሚያከብር የሰላም ባህል ሕንጸት ወሳኝ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.