2011-11-03 09:30:28

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮቡዕ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ (እ.ኤ.አ. 02/11/2011)


የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ
በዓለ ሁሉም ቅዱሳኖች እ.ኤ.አ. ህዳር 1 ቀን 2011 ዓ.ም. (በላቲን ሥርዓት) ካከበርን በኋላ ቅድስት ቤት ክርስትያን ዛሬ (እ.ኤ.አ. ህዳር 2 ቀን 2011 ዓ.ም.) ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን እንዘክር ዘንድ፣ እይታችን ምድራዊ ጉዞአቸውን ያጠናቀቁት ቀድመውን ወዳለፉት ገጽ እንድናቀና ጥሪ ታቀርብልናለች። RealAudioMP3 ስለዚህ በዚህ የዛሬው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ለእኛ ክርስትያኖች በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ አማካኝነት የተገለጠውን በዘለዓለማዊ ሕይወት ላይ ያለን እምነት ዳግም እንድናድስ ስለ ሞት ተጨባጭነት በተመለከተ ያልተወሳሰቡ አንዳንድ አመለካከቶችን ላቀርብላችሁ እወዳለሁ።
ትላትና (እ.ኤ.አ. ህዳር 1 ቀን 2011 ዓ.ም.) በሁሉም ቅዱሳኖች በዓል ምክንያት ጽሎት መልአከ እግዝአብሔር ከማሳረጌ ቀደም በማድረግ ባቀረብኩት ስብከት እንዳመለከትኩት በነዚህ ቀናት ከዚህ ዓለም በሞት ስለ ተለዩት ወዳጆቻችንን ለመጸለይ ለእነርሱ ያለንን ፍቅር እና ወዳጅነት ዳግም ለመግለጥ እና ቅርብነታቸውንም በጥልቀት ለማዳመጥ ጸሎት ለማድረስ ወደ መቃብር ሥፍራ እንሄዳለን፣ እንዲህ ባለ አገባብ የተአምኖተ ሃይማኖት ዓንቀጽ እንደሚያመለክተው በቅዱሳኖች ሱታፌ አማካኝነት በእኛና ዘለዓለማዊ ሕይወት ከተቀዳጁት ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ጋር ያለውን ጥብቅ ትሥሥር ያረጋግጥልናል።
ከጥንት ጀምሮ የሰው ልጅ ከዚህ ዓለም በሞት ለተለዩት በሚሰጠው ትኩረት፣ አሳቢነት እና ፍቅር አማክኝነት የዳግመ ህይወት (ካለፈው ምድራዊ ሕይወት ጋር የሚመሳሰል) አምሳያ የሆነ ዕድል ለመስጠት ሞክረዋል። ይህ ደግሞ በጠቅላላ በምድራዊ ሕይወት ሳሉ ሆነው የኖሩትን፣ ያፈቀሩትን የጠሉትን ተስፋ ያደረጉበት፣ ጥላቻ ያሳደሩበት ሁሉ፣ እኛ እነርሱ ባረፉበት የተለያዩ ትውስቶች በተሞላበት መቃብራቸው ፊት ሆነን ስንገኝ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ በኋላ የምረዳው ነው። ስለዚህ ከሞላ ጎደል የእነርሱ፣ የኖሩት የገዛ እራሳቸው ዓለም መሥተዋት ናቸው።
እንዲህ ለምን ይሆናል? በምንኖርበት ማኅበርሰብ ሞት የተሰኘው ርእሰ ጉዳይ እና አሳቡም ጨርሶ እንዳይኖር ከአዕምሮ የመፋቅ ሙከራ የሚታይበት ቢሆንም ቅሉ፣ እያንዳንዳችንን የሚመለከት የሁሉም ዘመን እና ሥፍራ የሆነው በጠቅላላ የሰው ዘር የሚመለከት እውነት በመሆኑ ነው። በዚህ ምሥጢር ፊት ባለ ማስተዋልም ይሁን ሁላችን ተስፋ እንድናደርግ የሚጋብዘንን አንድ ነገር፣ የሚያጽናና አንድ አዲስ መጻኢ ያሚያቀርብልን አድማስ እንሻለን። በእውነቱ የሞት መንገድ የተስፋ መገድ ነው። ወደ መቃብር ሥፍራ መጓዝ በመቃብር ሥፍራ እያንዳንዱ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ባረፈበት መቃብር ራስ የተቀመጠው ጽሑፍ ማንበብ፣ የዘለዓለማዊነት ተስፋ ያመለከተው ጉዞ ማከናወን ማለት ይሆናል።
ሆኖም ግን በሞት ፊት ፍርሃት ለምን ይሰማናል? የሰው ልጅ፣ ብዙሃኑ ከሞት ማዶ አንድ ባዶ የሆነ ነገር ብቻ አለ በማለት ለምን እርግፍ አድርጎ በመተው ሳያምን አይቀርም? ለዚህ ጥያቄ ብዙ መልስ አለው። በሞት ፊት ፍርሃት የሚሰማን ባዶነት ስለ ሚያስፈራን ነው። ወደ የማይታወቀው እና ወደ እማናውቀው ሥፍራ የሚደረግ ጉዞ በመሆኑም ነው። ይህ ደግሞ በእኛ ውስጥ በኅልውና ዘመን የተፈጸመው መልካም እና አቢይ የሆነው ሁሉ በአጋጣሚ ሲመክን እና ሲደለዝ ወደ አንድ የባዶነት ጭለማ ሲያዘግም ፈጽሞ እንዳንቀበለው የሚገፋፋን እምቢ የማለት ዝንባሌ አለ። ከሁሉም በላይ ፍቅር እንደሚጠራ እና ዘለዓለማዊነትን እንደሚሻ ይሰማናል፣ ከመቅጽበት በሞት አማካኝነት በአንዴ ሁሉም ይወድማል የሚለው አመለካከት ፍጽሞ ለመቀበል ያዳግተናል።
አሁን በሞት ፊት ፍርሃቱ አለን? በምድራዊ ሕይወት ፍጻሜ ስንገኝ እንፈራለን። ምክንያቱም የሕይወት ዘመን ተግባራችንን ሕይወታችንን እንዴት እንደመራንና በተለይ ደግሞ ከኅሊናችን ብዙውን ጊዜ ባለን ችሎታ የደለዝነውም ይሁን ለመደለዝ የምንሞክረው አጠራጣሪው እና የማያስተማምነው ክፉ ተግባራችን የሚመለከት ፍርድ እንዳለ ቅድመ ግንዛቤው ስላለን ነው። የፍርድ ጉዳይ ብዙውን ጊዜ የሰው ልጅ ከዚህ ዓለም በሞት ለተለዩት በሕይወት እያሉ አቢይ ግምት ይሰጣቸው ለነበረው፣ በዚህ ወደ ዘለዓለማዊነት በሚያደርገው ጉዞ ለተለዩት ለሚሰጠው ትኩረት እና ጥበቃ ዋነኛ ምክንያት እንደሆነ እንረዳለን። ስለዚህ በሕይወት ያለው ከዚህ ዓለም በሞት ለተለዩት ወዳጆቹ የሚሰጠው ትኩረት የሚያሳየው አሳቢነት እና እንክብካቤ በፍርድ ቀን ለብቻቸው እንዳይሆኑ ብሎ ያለመ ነው። ይኽ ዓይነቱ አመለካከት ከሰው ልጅ የባህል ታሪክ በሥፋት የምንረዳው ነው።
ዛሬ ዓለም በማስተዋል ብቃት ክፍ ብሎና የበለጠ በመሆኑም፣ ማንኛው ተጨባጭ የሞት ጉዳይ ያካተቱ አበይት ጥያቄዎች በእምነት ሳይሆን፣ መመዘኛው የሥነ ምርምር ሙክራ ነው በሚለው በሙከራ ላይ በሚጸናው እውቀት አማካኝነት መልስ የመስጠቱ ዝንባሌ የተስፋፋበ ሆነዋል። ስለዚህ ይህ የሥነ ምርምር አመለካከት ሙከራ ብቻ የሚለው አዝማሚያም የሰው ልጅ ፍጻሜ የዚህ የወቅታዊው ተጨባጭ ቅጅ እንደሆነ ለሚገፋፋው ከሞት ወዲያ ካለው ሕይወት ጋር ግኑኝነት ለማድረግ ለሚቃጣው በሙታን እና በሕያዋን መካከል ግኑኝነት አለ ለሚለው ለመናፍስትነት አመለካከት እድል የሚሰጥ እንደሆነም ግንዛቤ ያለ አይመስልም።
የሁሉም ቅዱሳኖች በዓል እና ሁሉም ሙታን የሚዘከሩበት ቀን፣ ሞት አቢይ የተስፋ ምልክት መሆኑ የሚያውቅ፣ ከተስፋ የተንደረደረ ሕይወት ለመኖር የሚቻል መሆኑ ያሳስበናል። የሰውን ልጅ በአግዳሚው አድማስ እርሱም በሥነ ምርምር ሙከራ ማእከል በማድረግ ብቻ የምንመለከት ከሆነ፣ ሕይወት ያለው ጥልቅ ትርጉምን ያጠፋል። የሰው ልጅ ዘለዓለማዊነት ያስፈልገዋል፣ ከዚህ ውጭ ሌሎች ተስፋዎች ዘላቂነት የሌላቸው እጅግ የተወሰኑ የአጭር ጊዜ ፍጻሜ ናቸው። ሰው የሚገልጠው ሞት፣ የሚያስከትለው የመገለሉ አዝማሚያም ጭምር በልጦ የሚሄድ ከሥፍራ እና ከጊዜ ባሻገር ምሉእነት የሆነ ፍቅር ብቻ ነው። የሰው ልጅ በጥልቀት የሚገልጠው ጥልቅ ትርጉም የሚሰጠው እግዚአብሔር ሲኖር ብቻ ነው። እግዚአብሔር ርቆ ከሚኖርበት ወጥቶ ለእኛ ቅርብ በመሆን አማክኝነት በሕይወታችን በመግባት “ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፣ የሚያምንብኝ ቢሞትም ይነሣል። ሕያው የሆነ የሚያምንብኝ ሁሉ ለዘለዓለም አይሞትም” (ዮሓ. 11. 25-26) ይለናል።
ለአንዴ እስቲ ቆም ብለን የቀራኒዮ ሁኔታን እናስብ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመስቀል ላይ ሆኖ በቀኙ ለተሰቀለው ፈያታዊ “በእውነት እልሃለሁ፣ ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር ትሆናለህ” (ሉቃ. 23፣ 43) በማለት የተናገረውን ቃል ዛሬ በኛ ሕይወት ገብቶ ዳግም ያስተጋባል። በኤማኡስ መንገድ የሁለት ደቀ መዛሙርት ታርክ መልሰን እንመልከት፣ ሁኔታውንም እናስብ፣ ከተነሣው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ትንሽ ከተጓዙ በኋላ ለይተው አወቁት ካለ ማመንታትና ካለ መዘግየት የጌታችን ትንሣኤ ለማበሠር ወደ እየሩሳሌም ተጓዙ (ሉቃ. 24፣ 13-35)። “ልባችሁ አይደንግጥ በእግዚአብሔር እመኑ በእኔም እመኑ። በአባቴ ቤት ብዙ ማደሪያና ማረፊያ አለ፣ እንዲህስ ባይሆን ኖር ቦታ ላዘጋጅላችሁ እሄዳልሁ እላችሁ ነበር” (ዮሓ. 14፣ 1-2) የሚሉት የመምህር ቃላት በኅሊና ዳግም በታደሰ፣ ግልጽነት በተሞላው መንፈስ ይመላለሳል። እግዚአብሔር በእውነት እራሱን ግልጧል፣ በሁሉም የሚደረስ ሆነዋል፣ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዲያገኝ እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ቤዛ አድርጎ እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲህ ወዶታል” (ዮሓ. 3፣16)። እንዲህ ባለ ፍቅር እስከ መውደድ ደርሷል። የላቀው የፍቅር መግለጫ በሆነው መስቀል ላይ፣ በሞት ድቅድቅ ጭለማ ውስጥ በመግባት ሞትን አሸነፈ፣ ተነሣም፣ እንዲህ ባለ ተግባር የዘለዓለም ሕይወት በር ለእኛ ከፈተልን። ክርስቶስ እርሱ ባለፈበትና በተሻገረው በሞት ሌሊትም መጠጊያችን ሆኖ ይደግፈናል፣ አለ ምንም ፍርሃት እማኔ የሚኖርበት መልካም እረኛም ነው። ጨለማም ባለበት ሥፍራ ሁሉ መልካም መንገድ የሆነውን የሚለይ ነው።
ዛሬ ተአምኖተ ኃይማኖት ስንደግም ይኸንን እውነት ነው አሜን ያልነው። ወደ መቃብር ሥፍራም በመሄድ ትኩረት አሳቢነት እና ፍቅር በተሞላው መንፈስ ጸሎት እናደርሳለን፣ ዳግም በዘለዓለማዊ ሕይወት ላይ ያለንን እምነት በቁርጠኝነት እና በብርታት እንድናድስ ብቻ ሳይሆን፣ በዚህ ተስፋ እንድንኖርና ከዚህ ምድራዊው ሕይወት ባሻገር ምንም ነገር የለም ለሚለው ዓለም እውነትን እንመሰክረውም ዘንድ ተጠርተናል። በዘለዓለማዊ ሕይወት ላይ እማኔ ለክርስትያን የምንኖርባት ምድር ብሩህ መጻኢ እንዲገነባበት አሰተማማኝ እውነት እና ደህንነት የተሞላው ተስፋ እንዲሰፍንባት አሁንም እጅግ የማፍቀር ብርታት እና ጽናት ይሰጣል።
በማለት ለሁሉም በተለያዩ ቋንቋዎች ሰላምታን አቅርበው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ወደ መጡበት ሸኝተዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.