2011-10-31 13:46:49

የጴንጠቆስጠ ባህል ዓወደ ጥናት


“ተስፋ እንደሌላቸው ሰዎች እንዳታዝኑ” (1ተሰሎንቄ ምዕ. 4 ቁ. 13) በሚል በአዲስ ኪዳን ቃል የተመራ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ “ስፐ ሳልቪ-በተስፋ ድነናል (ሮሜ. ምዕ. 8 ቁ. 24) RealAudioMP3 ርእስ ሥር የደረስዋት አዋዲት መልእክት ማእከል ያደረገ በተለይ ደግሞ ቁ. 7 “በወቅታዊው ሁኔታ ውስጥ መጻኢን የሚማርክ ተስፋ” የሚለው ሐሳብ የሚያጎላ የጴንጠቆስጠ ባህል ማእከል ያደረገ በኢጣሊያ ሪሚኒ ከተማ የኢጣሊያ ብሔራው የተሃድሶ እንቅስቃኤ ያዘጋጀው አቨኒረ የተሰየመው የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ዕለታዊ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ኡምበርቶ ፎለና የመሩት የኢጣሊያ ብሔራዊ የካቶሊክ የተሃድሶ እንቅስቃሴ ሊቀ መንበር ሳልቫቶረ ማርቲነስ የአፍቅሮተ ዘ ቤት ሊቀ መንበር ማሪያ ቮቸ፣ የኢጣሊያ ካቶሊክ ሠራተኞች ማኅበር ሊቀ መንበር አንድረያ ኦሊቨሮ አስተምህሮ ያቀረቡበት ዓወደ ጥናት ትላትና መጀመሩ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
በዚህ ነገ የሚጠናቀቀው ዓወደ ጥናት ቺዝል በመባል የሚጠራው የሠራተኞች ማኅበር ዋና ጸሓፊ ራፋኤለ ቦናኒ እና ሌሎች የተለያዩ የካቶሊክ ሃይማኖት እና አመለካከት የሚያንጸባርቁ የሠራተኞች ማኅበራት ሊቀ መናብርት የተሳተፉበት ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ቀጥሎም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ስለ ሥራ እና ሠራተኛ በተመለከተ የሰጡት ሥልጣናዊ ትምህርት እና የኢጣሊይ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ በበኩላቸውም የሰጡት መሪ ሓሳብ በማስደገፍ “የእግዚአብሔር ቃል እንዲሮጥ…ጸልዩ” (ሁለተኛ ተሰሎንቄ ምዕ. 3 ቁ. 1) የሚለው መንፈሳዊነት በማጉላት በጥልቀት ተስፋ እና ተስፋ ማን መሆኑ የሚብራራበት መሆኑ ተገልጠዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.