2011-10-31 13:51:55

የአሲዚ ከተማ ከንቲባ፦ የሃይማኖት የባህል የእምነት መለያ


እ.ኤ.አ. ባለፈው ጥቅምት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በአሲዚ ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ያነቃቁት የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች RealAudioMP3 መንፈሳውያን መሪዎች የጋራ የሰላም የፍትህ ውይይት ጸሎት ቀን የተጀመረበት 25ኛውን ዓመት ከሁሉም የተለያዩ የሃይማኖት መሪዎች ጋር በመሆን በአሲዚ የቅዱስ ፍራንቸስኮስ ከተማ ማክበራቸው ሲታወቅ፣ ስለ ተካሄደው የሰላም የፍትሕ እና የውይይት ጸሎት ቀን በማስመልከት የአሲዚ ከተማ ከንቲባ ክላውዲዮ ሪቺ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በዚህ የሰላም የፍትህ እና የውይይት የጋራው ጸሎት ሁሉም የራሱን መለያ አቅቦ የሚሳተፍበት እንጂ የአንዱ መለያ ከሌላው ጋር ተደባልቆ የሚደበዝዝበት መለያ የሚቀየጥበት መርሃ ግብር አይደለም። ስለዚህ አለ መደበላለቅ በመከባበር እና በመተዋወቅ አማካኝነት ውይይት የሚቻል መሆኑ የተረጋገጠበት ሁሉም በዚህ መንፈስ በጋራ ስለ ሰላም እና ለሰላም መረጋገጥ ብርታትን የሚጠይቀው የጋራ ዞ የተመሰከረበት ዕለት ነው።
ንግደት የላቲን ሥርወ ቃሉ እንደሚያመለክተው አቀበት የተሞላው መንገድ በእግር መውጣት ማለት መሆኑም ዘክረው፣ በዚህ በሚደረገው የጋራው የእግር ጉዞ ነጋድያን ያላቸው ባህላዊ ሃይማኖታዊ መለያ አቅበው ለአንድ ዓለማ አብረው ይጓዛሉ። በዚህ የአሲዚው የሁሉም የተላያዩ ሃይማኖቶች መንፈሳውያን መሪዎች የጋራው ጸሎት የር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ መንፈሳዊነት የጎላበት መሆኑም ከንቲባው በመግለጥ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲኮቶስ 16ኛ እዚህ በአሲዚ ከሁሉም የተለያዩ ሃይማኖት መሪዎች ጋር በመሆን ንግደት ሲፈጽሙ ማየቱም ደስ የሚያሰኝ አሲዚ የሰላም ኅያው ምስክርነት ቤተ መዘክር መሆንዋ አረጋግጠዋል። ሰላም የሁሉም ሰው ዘር ኃላፊነት ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.