2011-10-31 13:43:02

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፥ ከአሲዚ በአዲስ መንፈስ ተነቃቅቶ ዳግም ጉዞን መጀመር


ሁሌ በሳምንት ማገባደጃ የቅድስት መንበር የዜና እና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ በመቀጠል፣ ትላትና ልክ እንደ የዛሬው 25 ዓመት በፊት በእንተ ላእለ ኩሉ ቤተ ክርስትያን ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ RealAudioMP3 ያነቃቃቱ በየዓመቱ በቅዱስ ፍራንቸስኮስ ከተማ የሚካሄደው የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራ የጸሎት የአስተንትኖ እና የውይይት መርሃ ግብር መሠረት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለሁሉም መልካም ፈቃድ ላላቸው የሃይማኖት መሪዎች ያቀረቡት ጥሪ የጋራው ጸሎት አስተንትኖ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 27 ቀን 2010 ዓ.ም. ክንዋኔ ላይ በማተኮር ከአሲዚ በአዲስ መንፈስ ነተቃቅቶ ዳግም ጉዞን መጀመር በሚል ርእስ ሥር የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖት መሪዎች የጋራው መንፈሳዊ ንግደት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እንደ ሁሉም መንፍሳዊ ነጋዲ በመሆን አብረው በመጓዝ፣ ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እ.ኤ.አ. በ 2002 ዓ.ም. በተካሄደው የአሲዚው የሁሉም ሃይማኖት መሪዎች የጋራው የሰላም ጸሎት ወቅት እ.ኤ.አ. በ 2001 ዓ.ም. ዓለማችን ያናጋው የአሸባሪያን አሰቃቂው ግብረ ሽበራ እና ለግብረ ሽበራ የተነቃቃው ዓለም አቀፍ ግብረ መልስ በውስጠ ታዋቂነት በማስታወስ፣ ከሁሉም ሃይማኖት መሪዎች ጋር በመሆን ሦስቴ በመደጋገም አመጽ ዳግም እንዳይኖር ጥሪ በማቅረብ በእግዚአብሔር ስም መግደልም ሆነ የጥላቻ መንፈስ የማይቻል ነው። ምክንያቱም የእርሱ ስም የሁሉ የሰው ልጅ የጋራ የአባትነት መግለጫ መሆኑ በማብራራት፣ እግዚአብሔር የሁሉም አባት ፍቅር ነው።
ሆኖም ግን የሰው ልጅ በተለያዩ ጥንታውያንም ይሁን አዳዲስ ምክንያቶች አማካኝነት ሰላም ለማግኘት ተስኖት ይታያል፣ የአሲዚው መንፈሳዊው ንግደት አማካኝነት ሁሉም የተለያዩ ሃይማኖት መሪዎች በጋራ ትሁት እና ለሁሉም ክፍት በሆኑት ቃላቶች አማካኝነት የሰላም ጥሪ አስተላልፈዋል። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ በዚህ በአሲዚው የሁሉም ሃይማኖቶች መሪዎች የጋራ ግኑኝነት ባሰሙት ንግግር፣ እግዚአብሔር አንዳንዴም የእርሱን እውነተኛውን ማንነት የሚጋርዱ ሆነው የሚገኙት የሃይማኖት ተከታዮች የግል ንብረት ወይንም እነርሱን የሚመለከት ብቻ አይደለም፣ እውነትን ከሚፈልጉ ጋር በመሆን ሰላምን መፈለግ አስፈላጊ ነው። እውነተኛው እግዚአብሔር በአሸባርያን የሚመለክ አይደለም፣ አሸባሪያን እግዚአብሔርን መማጠን አይችሉም፣ ሆኖም ሰብአዊነቱን ካጠፋው ሰብአዊ አድማስ እግዚአብሔርን ማግለል ወይንም ማራቅ አይቻልም፣ በእርሱ አማካኝነት ሰብአዊነቱ ያጠፋው ሰው ዳግም ሰብአዊነቱን ይቀዳጅ ዘንድ የሰላም መሠረት የሆነው እግዚአብሔርን መማጠን ያስፈልጋል።
የቅዱስ ፍራንቸስኮስ መንፈሳዊነት የእግዚአብሔር ኅልውና ባልተወሳሰበ እና ቀላል በሆነ መንገድ በሁሉም የእርሱ ፍጠረት ዘንድ ማየት እና መስማት ማለት መሆኑ አባ ሎምባርዲ ባቀረቡት ርእሰ ዓንቀጽ በማብራራት፣ ይህ የቅዱስ ፍራንቸስኮስ መንፈሳዊነት አሁንም ክፍት ልብ እና አእምሮ ያለው ሁሉ ወደ አሲዚ ይማርካል፣ የሁሉም የጋራ ጉዞ ወደ ሆነው የውይይት እና የወንድማማችነት እና የደስታ መንፈስ የተለያዩ መለያ ያላቸው ሁሉን ያጠቃልላል።
በዚህ የአሲዚው ግኑኝነት ጥሪ ተደርጎላቸው ከተሳተፉት ኢአማኒያን የባህል ሊቃውንት ውስጥ ፕሮፈሰር ጁሊያ ክሪስተቫ፣ በአዲስ መንፈስ ለመፍጠር የነበረው ማውደም የሚለው መላ ምት ትክክል አይደለም ያሉትን ሃሳብ አባ ሎምባርዲ በርእሰ ዓንቀጹ በማስታወስ፣ ሰላም ተገቢው እና ብቸኛው መንገድ ብቻ ሳይሆን የሁሉም የጋራ ጥረት የሚጠይቅ ከአሲዚ በአዲስ መንፈስ ነተቃቅቶ የሚጀመር መሆኑ ዳግም የተመሰከረበት ዕለት ነው በማለት ርእሰ ዓንቀጹን አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.