2011-10-28 13:45:48

ጳጳሳዊ የላተራነንሰ መንበረ ጥበብ፦ ኤኮኖሚ ለሰው ልጅ እርባና


ሮማ በሚገኘው ከኢጣሊያ ግዛታዊ ውጭ በሆነው የአገረ ቫቲካን ክልል የሚገኘው ጳጳሳዊ ላተራነንሰ መንበረ ጥበብ ሥነ ምግባር እና ቁጠባ፦ ሥነ ምግባር RealAudioMP3 ቁጠባና እና ልማት በሚል ርእስ ሥር አኢሰስ በሚል አኅጽሮተ ቃል የሚታወቀው ካሪታስ ኢን ቨሪታተ-ፍቅር በሓቅ የተሰየመው የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ዓዋዲ መልእክት ማአክል በማድረግ ተቋቋመው ዓለም አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት ተቋሞች እና መናብርተ ጥበብ የኤኮኖሚ እና የማኅበራዊ እድገት ጉዳይ የሚንከባከበው ዓለም አቀፍ የሥነ ኤኮኖሚ የምርምር ማኅበር እና የሮማ ኅየንተ የመናብርተ ጥበብ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ጉዳይ የሚከታተለው ጽ/ቤት በጋራ ያዘጋጁት የሕንጸት ዓወደ ጥናት መካሄዱ ዓወደ ጥናቱን የተከታተሉት የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ያጠናቀሩት ዘገባ ይጠቁማል።
ኤኮኖሚን ሰብአዊነት ማልበስ እርሱም ለማኅበራዊ ጥቅም መረጋገጥ መሣሪያ መሆን እንዳለበት በዚህ የሥነ ባንክ ቤት፣ የሥነ ቁጠባ እና የሥነ ኤኮኖሚ እንዲሁም የሥነ ሕግ ሊቃውንት ያሳተፈው የላተራነንሰ ጳጳሳዊ መንበረ ጥበብ በማስገንዘብ ሰው፦ የማስተዳደር ብቃት እና ገበያ በተሰኙት ማእከላዊ ነጥቦች ላይ ያተኮር ጳጳሳዊ የላተራነንሰ መንበረ ጥበብ ዋና አስተዳዳኢ ብፁዕ አቡነ ኤንሪኮ ዳል ኮቮሎ አስተምህሮ በማቅረብ፣ ኤኮኖሚ የሰው ልጅ ደንበኛ ወይንም ተገልጋይ እርሱም ተጠቃሚነት ባህርዩ ላይ ብቻ ሳይሆን መላ መሆናዊው ላይ ያተኮረ የሰው ልጅ ክብር የሚያከብር መሆን አለበት ሲሉ፣ የቅድስት መንበር የሃይማኖት ተግባር የሚንከባከበው ተቋም ሊቀ መንበር የኤኮኖሚ ሊቅ ኤቶረ ጆቲ ተደስኪ በበኩላቸውም ካሪታስ ኢን ቨሪታተ ዋቢ በማድረግ ሥነ ቁጠባ ወይንም ኤኮኖሚ ግብረ ገብ የማያጠቃልል ከብግረ ገብ ነጻ የሆነ ሉኣላዊነት የለውም፣ ስለዚህ የሰው ልጅ ማእከል ያደረገ በእውነት ላይ የጸና መሆን አለበት ያሉትን ሃሳብ የተካሄደው ዓወደ ጥናት በማስተጋባት የልማት እቅድ የተስተካከለ ተቀባይነት ያለው ማንንም የማየግል ሁሉንም የሚያቅፍ የሚደግፍ እኩልነት የሚያንጸባርቅ መሆን እንደሚገባው መብራራቱም የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጆሶቲ ያጠናቀሩት ዘገባ ያመለክታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.