2011-10-28 13:43:59

የአሲዚ መንፈስ የውይይት ባህል ያለው አቢይ ክብር ለሁሉም ሃይማኖቶች መምህር


ልክ እንደ የዛሬው 25 ዓመት በፊት በእንተ ላእለ ኩሉ ቤተ ክርስትያን ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ያነቃቃቱ በየዓመቱ በቅዱስ ፍራንቸስኮስ ከተማ የሚካሄደው የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራ የጸሎት የአስተንትኖ እና የውይይት መርሃ ግብር መሠረት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ RealAudioMP3 ለሁሉም መልካም ፈቃድ ላላቸው የሃይማኖት መሪዎች ያቀረቡት ጥሪ እና የጋራው ጸሎት አስተንትኖ ትላትና እ.ኤ.አ. ጥቅምት 27 ቀን 2010 ዓ.ም. ተከናውኗል።
ቅዱስ አባታችን በዚህ የቅዱሳት መላእክት ንግሥት ቅድስት ድንግል ማርያም ባሲሊካ በተካሄው የሁሉም ሃይማኖቶች የጋራው ጸሎት እና አስተንትኖ ንግግር ከማሰማታቸው በፊት፣ የተለያዩ የምሥራቅ እና የምዕራብ አቢያተ ክርስትያን እንዲሁም የአይሁድ እና የምስልምና ሃይማኖት መንፈሳውያን መሪዎች በመቀጠልም ከባህል ዓለም የተወጣጡት ሊቃውንት ንግግር መደመጡ የቫቲካን ረዲዮ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ ዘገባ ያመለክታል።
በተለያዩ ሁሉም ሃይማኖቶች መካከል የጋራው ውይይት በተሳካ ሁኔታ ከተረጋገጠ በጥላቻ መንፈስ ላይ የመግባባት መንፈስ ድል እንደሚያደርግ እና ሥር እየሰደደ ከሚሄደው ግጭት በላይ ሰላም የበለጠ ተስፋ እና እድል ያለው ይሆናል የሚለው በዚያ የቅዱሳት መልእክት ንግሥት ቅድስት ድንግል ማርያም ባዚሊካ የተገኙት የሁሉም የተለያዩ የሃይማኖት መሪዎች ባሰሙት ንግግር የዛሬ 25 ዓመት በፊት አንድ በማለት ለሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራው ውይይት መሠረት የጣለው እማኔ መዘከሩ ለማወቅ ሲቻል፣ በዚህ የጋራው የጸሎት እና የውይይት መርሃ ግብር በመጀመሪያ ንግግር ያሰሙት የቁስጥንጥንያ የውህደት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ በርጠለሚዮስ አንደኛ፣ ይላሉ የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራው ውይይት የተለያዩ ቲዮሎጊያዊ እና ፍልስፍናዊ መሠረተ ደንችቦን ወይንም ሐሳቦች በአንድ ላይ ለማዋህድ ታልሞ የሚካሄድ ነው በማለት እንዳንዶቹ በአግቦ የሚሰነዝሩት ሃሳብ የሚያረጋግጥ ሳይሆን በሃይማኖት ያለው በኅብረተሰብ ዘንድ ሰላም የማነቃቃት ብቃት የሚያሳስብ የተለያዩ ሃይማኖቶች መሪዎች በጋራ ውይይት ይኸንን የሃይማኖት ብቃት የሚወድሱበት እና ግብራዊነቱን የሚጸልዩበት መንፈሳዊ መድረክ ነው ብለዋል።
የውህደት አንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን የበላይ መንፈሳዊ መሪ የካንተርበርይ ሊቀ ጳጳስ ሮዋን ዊሊያምስ እያንዳንዳቸው፣ ሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች በጋራ ላላቸው ጥልቅ ባህል ድምጽ በመስጠት፣ መላው የሰው ዘር የሚኖርበት ዓለም በመጠራጠር እና በፍራት ተማርኮ ለሌላው ጠላት በመሆን ላይ ታልሞ የሚከናወነው ርእሰ ጥበቃ ላይ የጸና ደህንነት እና ጸጥታ በማፍቀሩ ምክንያት በዓለም የሚታየው የሰው ልጅ ሕይወት እልቂት በተለይ ደግሞ በጦርነት እና በተለያዩ በሽታዎች ምክንያት የድኻው ክፍለ ኅብረተሰብ ሕይወት እልቂት በቸልተኝነት የመቀበሉ አዝማሚያ የሚያስፋፋው የጥፋት ባህል ለመዋጋት የሚያበቃ ጥበብ በጋራ የሚፈለግበት መድረክ መሆኑ አስምረውበታል።
የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የአይሁድ ኮሚቴ ከተለያዩ ሃይማኖቶች የግኑኝነት ጉዳይ ተጠሪ አቢይ መምህር ዳቪድ ሮሰን በቅዱስ መጽሓፍ ባህል መሠረት ነጋዲያነት የሚለው የአሲዚው መንፈስ በትክክል የሚገልጥ ሃሳብ ላይ በማነጣጠር፣ የአሲዚው ግኑኝነት የሰው ልጅ ወደ እግዚአብሔር ቤት ያቀና መሆኑ የሚያመለክተው ባህርይ በኩላዊነት ደረጃ የሚያረጋግጥ በጋራ የሚመሰክር ነው በማለት፣ ሁሉም ይኸንን ግኑኝነት የዛሬ 25 ዓመት በፊት ላስጀመሩት ለር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እና ከሳቸው በኋላ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው በካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ለተሰየሙት የአሲዚው ባህል ቀጣይነት እንዲኖረው ላደረጉት ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የተገባ ምስጋና ማቅረብ ግዴታ ነው ብለዋል።
የቁስጥንጥንያ ፓትሪያርክ እ.ኤ.አ. መስከረም 11 ቀን 2001 ዓ.ም. በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት አሸባሪያን የጣሉት አሰቃቂው ጥቃት ቀጥለውም ወቅታዊው የአረብ አገሮች ጸደይ ተብሎ የሚነገርለት ሕዝባዊ አብዮት በመጥቀስ፣ እያንዳንዱ እነዚህ በታሪክ የተከሰቱት ተግባሮች ተገን በማድረግ የገዛ እራሱ ሰልፈኛ አመለካከት ለማስፋፋት ከሚያደርገው መራወጥ ይቆጠብ ያሉትን ሃሳብ ያስታወሰ የሙስሊሞች ምሁራን ዓለም አቀፍ ጉባኤ ዋና ጸሓፊ ኪያህ ሓጂ ሓስይኒም ሙዛዲ ያሰሙት ንግግር፣ በአማንያን መካከል የሚቀሰቀሰው አልቦ ሃይማኖታዊ መሠረት ያለው የሃይማኖት ትምህርቶች ካባ ለብሶ ሃይማኖታዊ ዓላማ የሌለው ኢሃይማኖታዊ ተግባር በማጋለጥ እውነተኛው ከግል ጥቅም በላይ የሚለው የላቀው የሃይማኖት ትርጉም ለማሳወቅ ጥረት ካደረግን ከሃይማኖት አበው የተረከብነው የተስፋ ኩራዝ ዘወትር ቦግ እንዲል እናደርጋለን ብለዋል።
ፍትሕ እና እውነት ለእርቅ መረጋገጥ ተጨባጭ ቅድመ ሁኔታዎች እንደሆኑም በፈረንሳይ የአርመን ሓዋርያዊት ቤተ ክርስትያን የበላይ መንፈሳዊ መሪ ክቡር ሊቀ ጳጳሳት ኖርቫን ዛካሪያን በማብራራት፣ በተለያዩ ግጭቶች በሰው ዘር ላይ ጅምላዊ እልቂት የሚፈጽሙት ወንጀለኞች በመከታተል እውነት ገሀድ የሚያወጣ እውነተኛ ዓለም አቀፋዊ ፍርድ ቤት ለሰላም መረጋገጥ ወሳኝ ነው ሲሉ፣ ቅዱስ ፍራንቸስኮስ የሰጠው እውነተኛው የቃል እና የሕይወት ቅዱስ ምስክርነት ባይኖር ኖሮ ዛሬ ሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች በጋራ በመገናኘት ባንድነት ባልጸለዩ ነበር በማለት፣ ዛሬ በዓለማችን ሰላም ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የወጣቱ ተሳትፎ የሚያሻው ነው ስለዚህ ወጣቱ ትውልድ የቅዱስ ፍራንቸስኮስ አብነት እንዲከተል ማበረታታት ያስፈልጋል ብለዋል።
በዓለም የኢፉ እና ዮሩባ ሃይማኖት አፈ ጉባኤ የሁሉም የአፍሪቃ ባህላውያን ሃይማኖቶች ተበለው የሚጠሩትንም በመወከል ንግግር ካሰሙት አዊዘ አግባየ በመቀጠል የኮሪያ የቡድሃ ሃይማኖት ተጠሪ የዦግየ ማኅበር ሊቀ መንበር ዣ ሰኡንግ ንግግር በማሰማት ሃይማኖቶች ባለንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ አክብር በሚለው በወርቃማው መመሪያ መደምደሙ በቂ ኣይደለም፣ ስለዚህ ውደድ እና አክብር የሚለው ቃል ተፈጥሮንም ጭምር የሚመለከት ካልሆነ በምንም ተአምር ሰላም እና መረጋጋት ለማረጋገጥ አይቻልም ካሉ በኋላ፣ የሕይወት እና የሰላም ባህል የሚደግፍ ይኸንን ባህል የሚያስቀድም ወንድማማችነት አስፍላጊ ነው ሲሉ፣ የሂንዱ ሃይማኖት ወኪል አቻርያ ሽሪ ሽሪቫትዛ ጎዝዋኒ የአሲዚው የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖት የጋራው ውይይት የ 25ቱ ዓመት ታሪክ በመዳሰስ የጋራው ውይይት በትህትና በትዕግሥት ሌላውን በማክበር ፍላጎት ማለትም እድርግልኝ ላድርግልህ በሚል ሳይሆን በሚሠዋ ፍቅር ካልተሸኘነው ጥቅም የሌለው ሆኖ ይቀራል። ስለዚህ ኢፍትሓዊነትን የመሳሰሉት ጸረ ሰብአዊ ተግባሮች እምቢ ለማለት የሚያስችለን ከጸሎት የሚፈልቅ ጽናት የሚጠይቀው የሚሠዋው ፍቅር ነው ብለዋል።
በዚህ የአሲዚው የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራው ግኑኝነት እንዲሳተፉ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ጥሪ ከተደረገላቸው አራቱ ኢአማንያን ሊቃውንት ውስጥ የቡልጋሪያ ዜጋ ፕሮፈሰር ጁሊያ ክሪስተቫ ማንም እና ምንም አይነት ሃይማኖት ዋቢ ባላደረገው ንግግራቸው ሰብአዊነት ላይ በማተኮር ሰብአዊነት የሌላው አሳቢነት እና ፈቃድ የሚያስገኘው ወይንም የመንፈሳዊ ጉዳይ የሚያረጋገጠው ቀኖናዊ ሃሳብ ሳይሆን ውርርድ ነው። ስለዚህ የመጠራጠር ዘመን በቂ አይደለም የሰውል ልጅ ባለው ችሎታ በቀጣይነት በመተማመን ሰብአዊነት ለማረጋገጥ ጥረት ከማድረግ ተግባር መቦዘን አይገባውም እንዳሉ የራዲዮ ቫቲካን ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ ዘገባ ያመለክታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.