2011-10-26 14:36:35

የአሲዚው ግኑኝነት፥ የአንዳንድ ኢአማንያን ሱታፌ “ዓለማዊ ንግደት ወደ አበይት እሴቶች”።


ልክ እንደ የዛሬው 25 ዓመት በፊት በእንተ ላእለ ኩሉ ቤተ ክርስትያን ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ያነቃቃቱ በየዓመቱ በቅዱስ ፍራንቸስኮስ ከተማ የሚካሄደው የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራ የጸሎት የአስተንትኖ እና የውይይት መርሃ ግብር መሠረት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለሁሉም RealAudioMP3 መልካም ፈቃድ ላላቸው የሃይማኖት መሪዎች ያቀረቡት ጥሪ እና የጋራው ጸሎት አስተንትኖ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 27 ቀን 2010 ዓ.ም. ገቢራዊ ይሆናል።
በአሲዚ የሚካሄደው የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራው ጸሎት አስትንትኖ እና ውይይት ከተለያዩ 50 አገሮች የተወጣጡ የተለያዩ ሃይማኖቶች መሪዎች የሚያሳትፍ፣ የወንድማማችነት አድማስ የሚያንጸባርቅ ቅዱስ አባታችን የዚህ መንፈስ ምስክር በመሆን ወደ አሲዚ መንፈሳዊ ንግደት በማከናወን ሁሉም እንደ አንድ ቤተሰብ በአንድ ጥላ ሥር የሚያሰባስብ ዕለት እንደሚሆን አያጠራጥርም።
የዘንድሮው የአሲዚው የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች በጋራው ጸሎት አስተንትኖ እና ውይይት ለየት የሚያደርገውም፣ ቅዱስ አባታችን ለአራት ኢአማንያን ምሁራን ያቀረቡት የተሳታፊነት ጥሪ ሲሆን፣ ቅዱስ አባታችን ይላሉ የባህል ጉዳይ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ሳንቸስ ደ ቶካ፣ አማንያን ኢአማንያን እግዚአብሔርን እና ፍጹምነትን፣ ካለ ማቋረጥ እና ካለ መርካትም ዘወትር የሚሹ ናቸው የሚለው የሰው ልጅ በኑባሬ ያለው እውነትን የመሻት ባህርይ መሠረት በማድረግ ያቀረቡት ጥሪ ሲሆን፣ የባህል ጉዳይ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚ የኢአማንያን ሱታፌ በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ የኢአማንያን ምሁራን ሱታፌ ዓለማዊ ንግደት ወደ እሴቶች የሚል ትርጉም በመስጠት ወደ እውነት እና ወደ ሰላም የሚደረግ ንግደት ነው በማለት ገልጠውታል።
በዚህ በምንኖርበት ዘመን የእውነት ኅልዮ ባለፉት የመጨረሻ ዘመን ታሪኮች ካለው ጥልቅ ባህላዊ ግንዛቤው ጋር ሲነጻጸር ለወጥ እያለ መሄዱ ገልጠው። የእውነት በግሪክ እና በላቲን ሥነ ባህል የነበረው ትርጉም እንደሚያመለክተው እውነት ለገዛ እራሱ የቻለ ተጨባጭነት እንዳለው ይኽ ደግሞ ይፋዊ ዓላማ መሆኑ የሚያመለክት እንደነበር ቀድሞ የነበረ እና በልጦ የሚገኝ የላቀ ተብሎ ሲገለጥ፣ በአሁኑ ወቅት ግን እውነት ከባለ ቤትነት ጋር የተያያዘ ሆኖ ይታያል። ስለዚህ በግሪክ እና በላቲን የሥነ ባህል ዘመን እና በክርስትናው ባህል እውነት ለሚለው ቃል ይሰጠው የነበረው እን የሚሰጠው ትርጉም እና የነበረው ያለው ጥልቅ ግንዛቤ ዳግም መጎናጸ ይኖርብናል። በዚሁ ኃሳብ ዙሩያ የሚወያዩ እና አባባሉንም የሚያምኑበት የምሁራን ብዛት ከፍ እያለ ነው።
በርግጥ የአሲዚው የሁሉም ሃይማኖቶች ግኑኝነት በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል መቀራረብ እንዲኖር አግዘዋል። ሆኖም ግን አሁንም በተለያዩ የሃይማኖት ፅንፈኞች አክራሪነት የመሳሰሉት ዝንባሌዎች ትልቅ ችግር እየፈጠረ ነው። ስለዚህ በተለያዩ ሃይማኖት መካከል መቀራረብ እያየለ በሄደ ቁጥር ባንጻሩም እንዱ ሌላውን የማግለሉ አዝማሚያ እያሰፋ ያለ ይመስላል። ይህ የአሲዚው ግኑኝነት ይኸንን እውነት የሚያብራራ እንደሚሆን ነው ብለዋል።
የጋራው ውይይት ሂደት የተለያዩ የሥነ ፍልስፍና የሥነ ባህል እና የሥነ ሃይማኖት የተለያየ የማይገናኘውም አመለካከት የመደበላለቁ ፈተና ያሰጋዋል ቢባልን ይኽ አይነቱ አመለካከት ጊዜው ያለፈበት ከዚህ የአሲዚው የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች ውይይት አመለካከት የራቀም ነው። ሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች የሚያገናኛቸው መሠረታዊ የሆነው አዳማዊው አናሥር ላይ ማተኮር በሌላው ረገድም በሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች የሚገለጠው ምሥጢር፣ ከነገር ባሻገር የላቀው የነበረ ያለ የሚኖር ተብሎ በሚገለጠው እማኔ ላይ ማተኮር ይገባል። እንዲሁም የሚያገናኛቸው ሰብአዊ እሴቶች እውነት ፍትሕ በሕዝቦች መካከል የጋራው ግኑኝነት እና ሰላም ፍቅር የሚሉት ጉዳዮች የጋራ አካፋይ በሆኑት እሴቶች ላይ ማተኮር ነው። ስለዚህ ይኸንን ሁሉ መሠረት በማድርግም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በዚህ የአሲዚው ግኑኝነት ኢአማኒያን ምሁራን መጋበዝ ሊያከራክር የማይችለው እውነት፣ እርሱም የሰው ልጅ አማኝም ኢአማኝም ስለ አናሥር እና ፍጻሜ ከመጠየቅ አይቦዝንም ስለዚህ የኢአማኒያኑ ሲታፌ ወደ እሴቶች የሚደረገው ዓለማዊው ንግደት የሚገልጥ ሱታፌ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.