2011-10-26 14:38:27

የቫቲካን ረዲዮ “ክርስትያናዊ አድማስ” የሥርጭት መርሃ ግብር


እ.ኤ.አ. ባለፈው ጥቅምት 24 ቀን 2011 ዓ.ም. እዚህ በቫቲካን ረዲዮ ሕንጻ በሚገኘው በማርኮኒ የጉባኤ መለስተኛ አዳራሽ እ.ኤ.አ. መስከረም 11 ቀን 2001 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት RealAudioMP3 የተለዩት የዚህ ክርስትያናዊ አድማስ የተሰኘው የቫቲካን ረዲዮ የሥርጭት መርሃ ግብር ኃላፊ ነፍሰ ኄር ደራሲ የሥነ መንፈሳዊ ቲዮሎጊያ ሊቅ አባ ጆቫኒ ጆርጃኒ ታሪክ የሚያወሳ መጽሓፍ ለንባብ መቅረቡ ሲገለጥ፣ በተካሄደው ዓወደ ጥናት አባ ጆርጃኒ ካህን የመንፈሳዊ እና የልበ ወለድ ደራሲነት የጎላበት ሆኖ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ባሰሙት ንግግር፣ እሳቸው እና ቫቲካን ረዲዮ ሠራተኞች የአባ ጆርጃኒ ናፍቆት እንዳለባቸው ገልጠው፣ ለሳቸው ያለንን ናፍቆት ሌሎች የዚህ የቫቲካን ረዲዮ ሰራተኞች ብቃት እና ችሎታ ለማድነቅ ያግዘናል። ያደረጉትን የምንናፍቅ ብቻ ሳይሆን በበለጠውም እሳቸው ሆነው የኖሩት ማንነትን ነው የምንናፍቀው። መንፈሳዊ ምሁር ከሁሉም በላይ የማጽናናት የነበራቸው ተሰጥኦ የሚደነቅ ነው ብለዋል።
አባ ቪቶ ማኞ የሮጋተ ኤርጎ ማተሚያ ቤት አስተዳዳሪ በተራቸው ባሰሙት ንግግር፣ አባ ጆርጃኒ ኅልወተ እግዚአብሔር ላይ የነበራቸው እምነት የማያወላውል የማይጠራጠር ጽኑ እንደነበር ዘክረው፣ ይኽ ደግሞ በድርሰቶቻቸው በክርስትያናዊ አድማስ የሥርጭት መርሃ ግብር አማካኝነት ለማንም ሳያከብዱ በሙላት አለ ጥርጥር የኖሩት እና ያብራሩት ሕይወት ነው ብለዋል።
ሮማ በሚገኘው በሉምሳ መንበረ ጥበብ የሥነ ጋዜጠኝነት መምህር ፕሮፈሶር አንጀሎ ፓውሉዚ አባ ጆርጃኒ ስለ ዓለም የነበራቸው ራእይ ቀላሉ መንገድ የሚከተል ሳይሆን የተወሳሰበ ጥልቅ ጥናት የሚጠይቅ መንገድ የሚከተል የነበረ ቢሆንም የነበራቸው እምነት በምንም ተአምር በሥነ ጥበብ ደረጃ ሳይናጋ ይኸንን በነበራቸው የደራሲነት ተሰጥኦ በኩሉ ለሁሉም ለማሳወቅ እውነትን ለመሻት በዚህ እውነትን የመሻት ዙሪያ ውይይት በማነቃቃት የነበራቸው ጥልቅ እምነት የሰውን ልጅ ለማጽናናት አገልግሎት አውለውታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.