2011-10-24 14:19:51

የቅዱስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፦ “የእምነት ዓመት በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ 50ኛው ዝርከ ዓመት እይታ”።


ሁሌ በሳምንት ማገባደጃ የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ በመቀጠል፣ ቅዳሜ “የእምነት ዓመት በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ 50ኛው ዝክረ ዓመት እይታ” በሚል ርእስ ሥር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የዳግመ አስፍሆተ ወንጌል ጉባኤ እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 11 ቀን 2012 ዓ.ም. እስከ ህዳር 24 ቀን 2013 ዓ.ም. RealAudioMP3 የእምነት ዓመት ተብሎ እንዲታሰብ በማለት ለሰጡት ውሳኔ አቢይ ትርጉም ያለው ለመላ ቤተ ክርስትያን ተልእኮ እርሱም የሰው ዘር ዘወትር ከሚገኝበት ከምድረ በዳነት ሕይወት ተላቆ ከክርስቶስ ጋር ወዳጅነቱን እንዲኖር የሚያግዝ እና በአዲስ መንፈስ የሚያነቃቃ መሆኑ እና እንዲሁም አንዱ የር.ሊ.ጳ. መሠረታዊ ጥልቅ ዓላማ እና ተልእኮ ኩላዊነት ባህርይ ያለው መሆኑ የሚያረጋገጥ ነው ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባለፉት ቀናት ያወጁት የእምነት ዓመት የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይነታቸው አይነተኛው መለያ መሆኑ ኩላዊት ቤተ ክርስትያን የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ እንዲሆኑ በተሾሙበት ዕለት ቫቲካን በሚገኘው በሲስቲና ጸሎት ቤት ለመላ ካቶሊክ ብፁዓን ካርዲናሎች ባሰሙት እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ ቀዳሚ መልእክታቸው ከጌታችን ኢየሱስ ርክስቶስ ጋር መገናኘት የሚሰጠው ደስታ እና ያለው ተስፍኝነት የሚያበክር የእምነት ጎዞ ዳግም ማግኘት ወሳኝ ተቀዳሚ እና ፈጣን ድርጊት የሚጠይቅ ዓለማ ነው ያሉበት ቀን በእቅድ ያስቀመጠው አዋጅ እንደሚመስል እና በመቀጠልም በተለያየ ወቅት በሚያቀርቡዋቸው ሥልጣናዊ ስብከቶች አስተምህሮዎች ምዕዳን፣ ሐዋርያዊ መልእክቶቻቸው ብሎም ዓዋዲ መልእክቶቻቸው ባካሄዱዋቸው ዓለም አቀፍ እና ብሔራዊ ሐዋርያዊ ጉብኝቶች በተለይ ደግሞ በጀርመን ያካሄዱት ሐዋራዊ ጉብኝት እንዲሁም የዳግመ አስፍሆተ ወንጌል ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት በማቋቋም ጭምር ያሰመሩበት ጥልቅ ሐሳብ መሆኑ አባ ሎምባርዲ በርእሰ ዓንቀጹ አብራርተዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የእምነት ዓመት ሲያውጁ በእውነት ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ 50ኛው ዝክረ ዓመት በቅጽበት ቀድሞ የተገነዘበ የተፈጥሮ አስተዋይነታቸው ያጎላ እጅግ ደስ የሚያሰኝ ውሳኔ ነው። ይኽ ደግሞ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ለተለያዩ ዓውደ ጥናቶች ርእሰ ጉዳይ ሆኖ በሌላው ረገድም የገዛ እራስ አመለካከት ደጋፊ አድርጎ በማቅረብ ከሚደረገው መራወጥ ውጭ በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ መሪነት ሥር የሚሰጠው ንባብ፣ ትርግሙ እና ማብራሪያ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ አቢይ የቤተ ክርስትያን ሃብት መሆኑና እና ለቤተ ክርስትያን ጉዞ አቅጣጫ ጠቋሚ ብሶል ነው።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የእምነት ዓመት ሲያውጁ በር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ለሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ታማኝ በመሆን በሰጡት ውሳኔ መሠረት፣ እምነታችን የተሟላ ህይወት ያለው መሆኑ እና ግልጽነቱን ያበሠረው፣ ለማጠናቀሩ በተካሄደው አቢይ ሥራ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ እንዲሆኑ ከመሾማቸው በፊት የካቶሊክ አንቀጸ ሃይማኖት ተነከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ በነበሩበት ወቅት የተሳተፉበት የኩላዊት ቤተ ክርስትያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ለንባብ የበቃበት 20ኛው ዓመት ጭምር ያስተዋለ መሆኑ አባ ሎምባርዲ በርእሰ ዓንቀጹ አብራርተዋል።
የእምነት ዓመት፥ እምነት በእብራውን ምዕራፍ 11 እና 12 እንደተመለከተው ከጥንት ከዘፍጥረት ከብርሃም ከሙሴ ከቅዱስ ዳዊት ከነቢያት በጠቅውላላ ሁሉም ምስክሮች የሚዘክር፣ በዚህ የእምነት ጉዞ ቅዱስ አባታችን ዘወትር እይታችን ዕብራውያን ምዕራፍ 12 ቁጥር 2 “የእምነታችንንን ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን እንከተለው፣ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአል ተብሎ ወደ ተመሠከረለተ አዳኛችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሆን በማለት የማርያን የሐዋርያት የሰማዕታት የቅዱሳት የእምነት አብነት እምነት ለታሪክ እና ለሕይው ጉዞ አዲስ ምዕራፍ መሆኑ ያረጋግጥልናል። ስለዚህ የእግዚአብሔር ሕዝብ እረኛ ከሆኑት ከቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሌላ ስለ እምነት ማድረግ የሚገባን የሚነግረን የሚያስተምረን ማን ነው? በሚለው ጥያቄ ሥር ርእሰ ዓንቀጹን አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.