2011-10-24 14:18:17

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፥ “የመከላከያ ኃይል አባላት የእግዚአብሔር የፍቅር ትእዛዝ ለመከተል የተጠሩ ናቸው”።


ቫቲካን በሚገኘው የሲኖዶስ ቀዳሜ አዳራሽ እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 20 ቀን እስከ ጥቅምት 22 ቀን 2011 ዓ.ም. አለም ዓቀፍ የለመከላከያ ኃይል አባላት ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተንከባካቢ ብፁዓን ጳጳሳት እና ለመከላከያ ኃይል አባላት የነፍስ አባቶች ጉባኤ መካሄዱ ሲገለጥ፣ ይህ ለመከላከያ ኃይል አባላት RealAudioMP3 የሚሰጠው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎት የሚመለከት ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 24 ቀን 1986 ዓ.ም ይፋ ያደረጉት የመከላከያ ኃይል አባላት መንፈሳዊ እንክብካቤ ሐዋርያዊ መመሪያ ድንጋጌ 25ኛው ዓመት በሚዘከርበት በአሁኑ ወቅት የተከናወነ በመሆኑም የጉባኤው ሂደት ለየት እንዲል እንዳደረገው ቅዳሜ ጧት ለተጋባእያኑ ቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጳውሎስ ቤተ ጸሎት መሥዋዕተ ቅዳሴ ያሳረጉት የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ ባሰሙት ስብከት ማስታወሳቸው ተገልጠዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለተጋባእያኑ ያስተላለፉት ምዕዳን የብፁዓን ጳጳሳት ጉዳይ ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ የላቲን አመሪካ ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ድርገት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ማርክ ኦለት መነበቡ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለተጋባእያኑ ባስተላለፉት መልእክት፣ መንፈሳዊ አድማስ የሰው ዘር ሁሉ የሚመለከት መሆኑ በማብራራት በወታደር ሕይወት ጭምር ትኩረት የሚያሻው ሰብአዊ ባህርይ መሆኑ እንዳይዘነጋ አደራ ብለዋል።
የመከላከያ ኃይል አባላት ጥልቅ እምነት እንዲኖራቸው እና በሚኖሩበት እና በተሰማሩበት አገልግሎት እውነተኞች የክርስቶስ ምስክር ሆነው እንዲገኙ በማድረጉ ቅዱስ አላማ ክርስትያን የመከላከያ ኃይል አባላት የሚያንጽ የቤተ ክርስትያን የተልእኮ ዘርፍ መሆኑ በማስታወስ፣ ኩላዊት ቤተ ክርስትያን ለመከላከያ ኃይል አባላት መንፍሳዊ እንክብካቤ እንድታደርግ መጠራትዋ ቅዱስ አባታችን አስታውሰው፣ ለዚህ መሳካት የመከላከያ ሃይል አባላት ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተንከባካቢ ብፁዓን ጳጳሳት እና የመከላከያ ሃይል አባላት መንፍሳዊ አባቶች እና ቆሞሶች ወንጌላዊ ምስክርነት ወሳኝ ነው ካሉ በኋላ፣ የአንድ ክርትያን የመከላከያ ኃይል አባል መንፈሳዊ ሂደት፣ ለእግዚአብሔር እና ለባለንጀራው ባለው ፍቅር የሚገለጥ ነው። ስለዚህ የሰላም መሣሪያ እንዲሆን የተጠራ ነው ብለዋል።
በተለያየ ሰብአዊ እና የተፈጥሮ አደጋ በተከሰተበት ክልል ተሠማርተው ግብረ ሠናይ የሚፈጽሙ የመከላከያ ኃይል አባላት ለገዛ እራሳቸው ሕይወት ሳይሳሱ እራስ አሳልፎ ከመስጠት የበለጠ ፍቅር የለም የሚለው የእያንዳንዱ ክርስትያን ፍቅር ክርስቶሳዊ መመዘኛ በመኖር፣ ጦርነት በሚካሄድባቸው ክልሎች በሰላም አስከባሪ ተልእኮ ወንድማማቾች የእርስ በእርስ ሞት ምክንያት እንዳይሆኑ በማረጋገት ተልእኮ ተሰማርተው የሚሰጡት የግብረ ሠናይ አገልግሎት የሚደነቅ ነው። ኃይሉም ከእግዚአብሔር ነው ካሉ በኋላ፣ ለመከላከያ ኃይል አባላት የሚሰጠው የአስፍሆተ ወንጌል አገልግሎት ኃላፊነት ቀላል አይደለም። ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እ.ኤ.አ. በ 2002 ዓ.ም. ባስተላለፉት ዓለም አቀፍ የሰላም መልእክት እውነተኛ ሰላም የፍትህ ውጤት ነው ያሉትን ሐሳብ በማስታወስ፣ ሰብአዊ ፍትህ ኮሳሳ እና ኢፍጹም በመሆኑም በፍትህ ላይ ይቅር የመባባል መንፈስ መታከል አለበት። በማለት ያስትላለፉት መልእክት እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.