2011-10-24 14:16:51

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፥ “ብሩኽነር በሚዚቃ ድንቅ የሥነ ጥበብ ሥራው የእምነትን ምሥጢር የሚፈልግ”


ትላትና እሁድ ከቀትር በኋላ ቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ በኬን ናጋኖ የተመራው የሙዚቃ ቡድን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በተገኙበት ተ ደውም- እግዚአብሔር ሆይ እናመሰግንሃለን (የስብሓተ አምልኮ) ጥንታዊው የሚዚቃ ሥራ እና የአንቶን ብሩኽነር ድረስት RealAudioMP3 “ሲንፎኒያ-ውህደ ሙዚቃ ቍጥር 9” በማርቲን ስታይድለር የተመራው በአውዲ ዩገንድ የከፍተኛ የሙዚቃ ትምህርት ቤት መዘመራን ለትርኢት መቅረቡ ሲታወቅ፣ እነዚህ ውህደ ሙዚቃዎች በርግጥ ከእምነት ከመነጨው ብርሃን የተደረሰ መሆኑ ቅዱስ አባታች ር.ሊ.ጳ. በትርኢቱ ፍጻሜ ባሰሙት ንግግር በማብራራት፣ የብሩኽነር የሚዚቃ ሥራዎች ማዳመጥ እራስን ከነገር ባሻገር ወደ ሆነው ቀና ለማድረግ የሚያግዝ ልዩ የእምነት ስሜት የሚያነቃቃ መሆኑም ገልጠው፣ የዚህ ሙዚቃ ድርሰት ምንጭ በርግጥ የኦስትሪያው ተወላጅ የሚዚቃ ሊቅ እና የሙዚቃ ደራሲ ብሩኽነር የኖረው ያልተወሳሰበው ጽኑ ያልተበከለ እውነተኛ እና ቅን እምነት መሆኑ ቅዱስነታቸውም በማስረዳት፣ ብሩኽነር በዚህ በሳል እና የመጨረሻው የሚዚቃ ድርሰቱ አማካኝነት ሁለ መናው የሙዚቃ ጥበቡ እና ድርሰቱ ወደ አብ ያቀና ከእርሱ ጋር የሚወያይ ሆኖ መላ ኅልውናው ጥልቅ እምነት የኖረ መሆኑ ነው የሚያረጋግጥልን። በተስፋ በመጠባበቅ የመኖር ስሜት የሚገልጥ ብሩኽነር በዚህ ውህድ ሙዚቃው አማካኝነት ወደ እግዚአብሔር ምሥጢር ለመግባት ይኽ ደግሞ እግዚአብሔርን ለመወደስ ለማመስገን ዓለሞ በምድር እርሱን በሰማያዊ ቤትም በማወደስ እምነትን ለመኖር የሚሻ ጥልቅ ስሜት የሚተነትን ነው።
ምንም’ኳ ችግር ፈተና የሚፈራረቅበት ቢሆንም ቅሉ ወቅታዊው ሕይወታችንን ሳንዘነጋ ተጨባጩ ሕይወታችን ብርሃን ተስፋ እና ፍቅር እንዲኖረው ለማድረግ የሚያበቃን የእምነት ብርሃን በማስቀደም የመሆናችን አድማስ ለዘለዓለማዊ ሕይወት ክፍት እንድናደርግ እና ስለ ዘለዓለማዊው ሕይወት እንድናስተነትን የሚያሳስበን ውህደ ሙዚቃ ነው በማለት ያዳመጡት ውህደ ሙዚቃ በጥልቀት አስረድተዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.