2011-10-21 14:26:15

የሃይማኖት ነጻነት ጥበቃ ሁሉም በጋራ መትጋት ይኖርበታል


እ.ኤ.አ. ጥቅምት 26 ቀን 2010 ዓ.ም. የሚከበረው የሂንዱ ሃይማኖት ዲፓቫሊ በመባል የሚታወቀው የብርሃን በዓል ቀን ምክንያት ከሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች ጋር የጋራ ውይይት የሚያንቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ዣን ልዊስ ቱራን እና ዋና ጸሓፊያቸው ብፁዕ አቡነ ፒየር ልዊጂ ቸላታ ፊርማ የተኖርበት መልእክት ለሁሉም የሂንዱ ሃይማኖት ተከታዮች እና የሂንዱ ሃይማኖት መንፈሳውያን መሪዎች RealAudioMP3 መተላለፉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
በተላለፈው መልእክት የሁሉም የሰብአዊ መብት እና ፍቃድ መሠረት የሆነው በአሁኑ ወቅት በተለያየ ክልል ለአደጋ ተጋልጦ ያለው የሃይማኖት ነጻነት በሁሉም ሥፍራ አለ ምንም ልዩነት እና አድልዎ እንዲከበር ሁሉም ሃይማኖቶች በጋራ ነቅተው ይተጉ ዘንድ ጥሪ መተላለፉ ሲገለጥ፣ የሃይማኖት ነጻነት መጣስ ለተቀሩት የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ጥበቃ ለአደጋ ማጋለጥ ማለት እንደሆነና የሁሉም ሰው ዘር በማኅበራዊ ደረጃም ይሁን በግል ደረጃ የሚኖረው የሃይማኖት እና የአምልኮ ነጻነት እንዲከበር በማሳሰብ መንግሥታት ይኽ የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ መሠረት የሆነው ነጻነት ለማስጠበቅ ኃላፊነት አለባቸው።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. በ2011 ዓ.ም. ለዓለም ዓቀፍ የሰላም ቀን ባስተልለፉት መልእክት ዘላቂነት ያለው ሰላም ለማረጋገጥ የሃይማኖት ነጻነት በቅድሚያ ማክበር ከሚለው ውሳኔ መጀመር አለበት፣ አለ ሃይማኖት ነጻነት ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ የሚቻል አይደለም ያሉትን ሐሳብ የጠቀሰው መልእክት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ መልካም ፈቃድ መሠረት በቅዱስ ፍራንቸስኮስ ከተማ የተነቃቃው የሁሉም ሃይማንቶች የጋራ የውይይት እና የጸሎት ቀን 25ኛው ዝክረ ዓመት ምክንያት የሁሉም ሃይማኖት መሪዎች በአሲዚ ለጋራ ጸሎት አስተንትኖ እና ውይይት እ.ኤ.አ. ጥቅምት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. እንዲገናኙ ያቀረቡት ጥሪ በዚህ በሚደረገው የሁሉም ሃይማኖት ግኑኝነት መሠረት ሰላም እና ስምምነት የተካነው ማኅበራዊ ኑሮ እንዲረጋገጥ የተለያዩ ሁሉም ሃይማኖቶች ያለባቸው ኃላፊነት የሚያነቃቃ መሆኑ በማስታወስ፣ ለሁሉም የሂንዱ ሃይማኖት ተከታዮች መልካም በዓል መመኘታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.