2011-10-21 14:24:32

ብፁዕ ካርዲናል በርቶነ መልእክት ለኤውሮጳ ክርስትና ባህል መሠረት ማእክል


ሮማ በሚገኘው በስትሩዞ ተቋም በመካሄድ ላይ ወዳለው አንደኛው የኤውሮጳ ክርስትና ባህል መሠረት ማእከል ጉባኤ የቅድስት መንበር ዋና ፀሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ መልእክት ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ። RealAudioMP3
ብፁዕ ካርዲናል በርቶነ ባስተላለፉት መልእክት በዚህ የኤውሮጳው ክርስትያናዊ መሠረተ ባህል የቤተ ክርስትያን የማኅበራዊ አንቀጸ ሃይማኖት ትምህርት ያለው ሚና ላይ በማተኮር፣ ባለፈውም ይሁን በዚህ ባለንበት በአሁኑ ወቅት የቤተ ክርስትያን የማኅበራዊ ጉዳይ አንቀጸ ሃይማኖት ትምህርት ያለው ማእከልነት፣ እርሱም ለተረጋጋው ማኅበራዊ ኑሮ መሠረት መሆኑ የኤውሮጳ ታሪክ ምስክር ነው ካሉ በኋላ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ካሪታስ ኢን ቨሪታተ-ፍቅር በሐቅ በተሰኘው ዓዋዲ መልእክት እንዳመለከቱት፣ ማኅበረ ክርስትያን እንዲሁም መልካም ፈቃድ ላላቸው ሰዎች በጠቅላላ የሥራው ዓለም ያለው ክብር እንዳይዘነጋ በማሳሰብ፣ የሥራ ክብር ጥበቃ የኤኮኖሚ አመክንዮ መሆኑ በማብራራት፣ በሥራው እና በኤኮኖሚው ዓለም ማኅበራዊ ንዋይ ማእከል ሲሆን፣ ይኽ ደግሞ ለእርስ በእርስ መተማመን፣ ለመከባበር የሥራ ሕግ እና ሥርዓት ለመጠበቅ እንዲሁም በሥራ ዓለም ተቀጥሮ ለሚሰጠው የሠራተኛ ኃላፊነት ጭምር መሠረት ነው። ስለዚህ ይህ ንዋይ እና ሥራ በሚል ርእስ ሥር በመካሄድ ላይ ያለው ጉባኤ በቅድሚያ የሰው ልጅ የተሟላ እድገት በሁሉም የሥራ መስከ ዋጋ ሊሰጠው እንደሚገባ የሚያስገነዝብ መሆን ይጠበቅበታል እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።








All the contents on this site are copyrighted ©.