2011-10-21 14:22:38

ብፁዕ አቡነ ፊሎኒ፥ ወንጌላዉ ልኡክነት እምነት የማስፋፋት ተግባር


እ.ኤ.አ. በ 1926 ዓ.ም. ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፒዮ 11ኛ በኩላዊት ቤተ ክርስትያን በየዓመቱ የቤተ ክርስትያን ሐዋርያዊ ተልእኮ ቀን ታስቦ እንዲውል የሰጡት ነቢያዊ ተስተውሎ የተሞላው ውሳኔ እ.ኤ.አ. በ 1927 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ የተልእኮ ቀን በሚል ስያሜ አንድ በማለት ታስቦ እርሱም፣ የሐዋርያዊ ተልእኮ ወር ተብሎ በቤተ ክርስትያን ባህል የሚከበረው በጥቅምት ወር አጋማሽ በሚውለው እለተ ሰንበት የሚታሰብ ሲሆን፣ RealAudioMP3 ይኽ እንተ ላእለ ኩሉ ቤተ ክርስትያን የሚታሰበው የሐዋርያዊ ተልእኮ ቀን በማስመልከት የፕሮፓጋንዳ ፊደይ እርሱም ወንጌላዊ ተልእኮ የሚመለከት የአስፍሆተ እምነት ጉዳይ የሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ፈርናንዶ ፊሎኒ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የዚህ ዘንድሮ የሚታሰበው የወንጌላዊ ተልእኮ ቀን መሪ ቃል ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ውሳኔ መሠረት “አብ እንደላከኝ እኔ ደግሞ እልካችኋለሁ” (ዮሓ. 20፣21) የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል መሆኑ ጠቅሰው ቅዱስነታቸው የወንጌላዊ ተልእኮነት ጥሪ ከእግዚአብሔር መሆኑ እርሱም አብ እንደ ላከኝ የሚለው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል የሚያስገነዝበው ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠው ተልእኮ ሱታፌ እንደሆነና በመጀመሪያ ለሐዋርያት በመቀጠልም ለተከታዮቻቸው ያስተላለፉት በቤተ ክርስትያን የሚኖር የተልእኮ ሱታፌ ጥሪ መሆኑ በማብራራት የሰጡት ውሳኔ ነው። ስለዚህ ቤተ ክርስትያን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል በዓለም እውን እንዲሆን የተላከች ነች ብለዋል።
ዘንድሮ ይኽ የወንጌላዊ ተልእኮ ቀን ለየት የሚያደርገው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ውሳኔ መሠረት የዳግመ አስፍሆተ ወንጌል የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት የተቋቋመበት ዓመት በመሆኑ ነው። ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ አድ ጀንተስ ወደ አሕዛብ በሚለው ውሳኔ የቤተ ክርስትያን ቀዳሚው የተልእኮ ዓላማ ብሥራተ ወንጌል መሆኑ ያስገንዘዝባል። ስለዚህ ዳግመ አስፍሆተ ወንጌል ሌላም በቤተ ክርስትያን የሚፈጸመው ተልእኮ እና ግብረ ሠናይ ብሥራተ ወንጌል መሠረት ያደረገ ተልእኮ መሆኑ እንዳለበት አብራርተዋል። ስለዚህ በብሥራተ ወንጌል ተልእኮ መሠረት ወደ መላው የዓለም ሕዝብ ዘንድ ለመድረስ ነው ዓላማችን ብለዋል።
ሁሉም ምእመን የዚህ ተልእኮ እንደየ ጥሪው አማካኝነት ተካፋይ ወይን ተሳታፊ ነው። የቤተ ክርስትያን ልኡከ ወንጌል ዓላማ በተለያየ መልኩ በጸሎት በምጽዋት እና በሌሎች መንፈሳዊ ተግባሮች አማካኝነት የመደገፍ ኃላፊት ተቀብለዋል። ዕለቱ አስፍሆተ ወንጌል በሁሉም ሥፍራ መሆን እንዳለበት የሚያስታውስ ቀን ነው ብለዋል።
በሌላው ረገድ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 11 ቀን 2012 ዓ.ም. እስከ ህዳር 24 ቀን 2013 ዓ.ም. የእምነት ዓመት ተብሎ እንዲታሰብ ውሳኔ በሰጡበት በአሁኑ ወቅት የሚታሰበው የተልእኮ ቀን በመሆኑ ጥልቀት ባለው ትርጉም በበለጠ እንዲስተጋባ የሚያደርግ መሆኑ ብፁዕ አቡነ ፊሎኒ በማብራራት፣ በሁሉም ወቅት እምነትን በደስታ መመስከር እና መበሠር አለበት። እምነት ወደ ደረሰበት እና ወዳልደረሰበትም ሥፍራ በድረስ ይገባዋል። የእምነት ዓመት እ.ኤ.አ. ጥቅምት 12 ቀን 1962 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ 23ኛ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ያስጀመሩበት 50ኛው ዓመት እንዲሁም የኩላዊት ቤተ ክርስትያን የካቶሊክ ትምህርተ ክርስቶስ ሰነድ 20ኛው ዓመት ጋር የተያያዘ በመሆኑ በርግጥ ወቅቱ እምነት ዳግም ህያው ለማድረግ እና በደስታ ለሁሉም ለማቅረብ የሚለው ዓላማ በበለጠ የሚያጎላ መሆኑ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ያሳስቡናል፣ ስለዚህ የተልእኮው ቀን ይኸንን ሁሉ ግምት የሚሰጥ ነው ብለዋል።
ወንጌላዊ ተልእኮ ኩላዊነት አድማስ ያለው እርሱም በቤተ ክርስትያን ሥልጣናዊ ትምህርት ዘንድ የሚመራ በሁሉም ሥፍራ የቋንቋ የባህል ልዩነት የማያግደው ይዞታዊ ውህደት ያለው መሆን አለበት።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ሁለተኛው የመላ አፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ማካሄጃ ሰነድ ለማስረከብ እ.ኤ.አ. በ 2009 ዓ.ም. ወደ አፍሪቃ ያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት የሲኖዶስ ፍጻሜ ሰነድ መሠረት የደረሱት ሐዋርያዊ ምዕዳን ዳግም ወደ በኒን ሐዋርያዊ ጉብኝት በመፈጸም ለመላ የአፍሪቅ ብፁዓን ጳጳሳት ያስረክባሉ። ሁለተኛው የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ መሪ ቃል “እናንተ የምድር ጨው ናችሁ…እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ…” (ማቴ. 5፣ 13-16) የሚለውን ወንጌላዊ ቃል ዘክረው ይኽ አንዱ የልኡካነ ወንጌል ማንነት መለያ ነው። በዚህ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የበኒን ሐዋርያዊ ጉብኝ ቅዱስ አባታችን ጋር በመሆን እንዲሳተፉ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የቀረቡባቸው ጥሪ በቤተ ክርስትያን የወንጌላዊ ተልእኮ ጥሪ ለአፍሪቃ የሚሰጠው ትኩረት ክፍተኛ መሆኑ የሚገልጥ ነው በማለት የሰጡን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.