2011-10-21 14:21:02

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፥ የእምነት መሠረት እና ክፍን መልሶ ለማግኘት


ዛሬ እንደ ጥንቱም ወደ ጥንታዊት ከተማ ሮማ እና በጠቅላል በኢጣሊያ ወደ ሚገኙት ቅዱሳት ሥፍራ ለመሳለም እና ለመንፈሳዊ ጉብኝቶች ዓላማ ከተለያዩ አገሮች የሚመጡት መንፈሳውያን ነጋድያንን የማስተናገዱ ባህል መሠረት እዚህ ሮማ ከኦቺያኒያ ለሚመጡት መንፈሳውያን ነጋድያን ማስተናገጃ እንዲሆን በአውስትራሊያ የምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የወጪ እቅድ መሠረት ዶሙስ አውስትራሊያ-የአውስትራሊያ ሕንፃ RealAudioMP3 በሚል መጠሪያ የተገነባው የኦቺያንያ መንፈሳውያን ነጋድያም ማረፊያ ቤት ትላንትና ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለቪሲታ አድ ሊሚና ማለት የካቶሊክ ጳጳሳት በያምስቱ ዓመት በቫቲካን ሐዋርይዊ ጉብኝት ለማከናወንና ከመንበረ ጴጥሮስ ጋር ያላቸውን ውህደት በመመስከር ለማጽናት፡ ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ታዛዥነታቸውን፡ አንድነታቸውን ለመመስከርና የቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ለመሳለና ስለ ቤተክርስትያናቸው ወቅታዊና አንግብጋቢ ርእሶች አስደግፈው ከቅዱሱ ኣባታችን ጋር በመነጋገርም መሪ ቃል የሚያገኙበት መንፈሳዊ ጉብኝት ምክንያት ቫቲካን በሚገኙት የሲድኒይ ሊቀ ጳጳሳታ ብፁዕ ካርዲናል ጆርጅ ፐል የሚግኙባቸው በመላ የአውስትራሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ታጅበው በመሩት ጸሎት እና የቡራኬ ሥነ ሥርዓት መሠረት ተመርቆ መከፈቱ ሲገለጥ፣ በተካሄደው የጸሎት ሥነ ሥርዓት በቅድስት መንበር የአስትራሊያ ልኡከ መንግሥት ቲም ፊሸር መገኘታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።
ለቅዱስ አባታችን ብፁዕ ካርዲናል ፐል በሁሉም የአውስትራሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ስም እንኳን ደህና መጡ በማለት የምስጋና ቃል ካሰሙ በኋላ ቅዱስነታቸው ቀጥለው ባሰሙት ንግግር፣ የዛሬ አንድ ዓመት በፊት እንተ ላእለ ኩሉ ቤተ ክርስትያን ቅድስና ያወጀችላት የአውስትራሊያ ቀዳሜ ቅድስት ማርይ ማኪሎፕን ዘክረው በዚህች ቅድስት የሚንጸባረቀው ክርስትያናዊ የቅድስና ባህርይ ወይንም ክርስትያናዊ ግብረ ጽድቅ የዚህ ዓለም ኑሮአችን ግዚያዊ እና ጉዞአችንም እግዚአብሔር ለሚያፈቅራቸው ወደ ተዘጋጀው የሰው ዓይን ያላየው የሰው ጀሮ ያልሰማው የሰው ልጅ ልብ ያላሰበው ፍጻሜው ወደ ሆነው ዓላማ ነው በማለት የገለጠችው እምነት ጠቅሰው፣ የቆየው ጥንታዊው ህያው የሆነው ምእመናን ወደ ቅዱሳት ሥፍራ የሚያደርጉት መንፈሳዊ ንግደት፣ ለገዛ እርሱ ሕይወታችን ወደ መንግሥተ ሰማይ ያቀና መሆኑ የሚያረጋግጥልን ባህል ነው። ስለዚህ ለቅድስና መጠራታችን የሚያሳስበን በመንፈሳዊ ምግብ ተሸኝተን ወደ ጌታችን ዕለት በዕለት በበለጠ እየቀረብን መሄድ እንዳለብን የሚመክረን ባህል ነው። ከተለያዩ አገሮች ከጠቅላላው የዓለማችን ክልል የቅዱስ ጴጥሮስ እና የቅዱስ ጳውሎስ ባዚሊካ እንዲሁም ቅዱስ አጽም ለመሳለም የጎረፈው መንፈሳውያን ነጋድያን ጥንታዊው እና ህያው ባህል አለ ምንም ልዩነት መላ ምእመናን በሐዋርያት ላይ ጌታችን ኢየሱስ ከመሠረታት ቅድስት ቤተ ክርትያን ጋር ያላቸውን ውህደት የሚመሰከርበት መሆኑ አብራርተው፣ ከእናታችን ቅድስት ቤተ ክርስትያን መሠረት እና ክንፍ የሚሆነን ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገረ እና እየተወራረሰ የሚሄደው የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የሆነው ለየት ባለ መልኩም በቤተ ክርስትያን ቅዱሳት ምሥጢራት በኩል የሐዋርያት እምነትን ትጸግወናለች።
መንፈሳውያን ነጋድያን ቅዱሳት ሥፍራን ተሳልመው እና ጎብኝተው ወደ መጡበት ሲመለሱ በእምነታቸው ታድሰው እና ጸንተው ወደ መንግሥተ ሰማይ በሚያደርጉት ጉዞ፣ መንፈስ ቅዱስ እንደሚሸኛቸው ግንዛቤው ያሳድራሉ፣ ለሌሎችም ይመሰክራሉ ካሉ በኋላ፣ መንፈሳውያን ነጋድያን በእምነት ጸንተው በተስፋ እና ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ባላቸው ፍቅር ከፍ ብለው በአዲስ እና በጋለ መንፈስ ፣ በሚኖሩበት ዓለም እና ሥራ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚመሰክሩ እንዲሆኑ ጸልየው ያሰሙት አስተምህሮ ማጠቃለላቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.