2011-10-19 14:45:30

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መንፈሳዊ ንግደት


እ.ኤ.አ. ጥቅምት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በኢጣልያ አሲዚ ቅዱስ ሥፍራ የአንድ ቀን መንፈሳዊ ንግደት እንሚያከናውኑ የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል ከሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል። RealAudioMP3
ቅዱስነታቸው ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ መልካም ፈቃድ መሠረት በቅዱስ ፍራንቸስኮስ ከተማ የተነቃቃው የሁሉም ሃይማንቶች የጋራ የውይይት እና የጸሎት ቀን 25ኛው ዝክረ ዓመት ምክንያት የሁሉም ሃይማኖት መሪዎች በአሲዚ ለጋራ ጸሎት አስተንትኖ እና ውይይት እ.ኤ.አ. ጥቅምት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. እንዲገናኙ ባቀረቡት ጥሪ መሠረት፣ በአሲዚ የሚያከናውኑት መንፈሳዊ ንግደት መሆኑ የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል መግለጫ ያመልከታል።
የዛሬ 25 ዓመት በፊት የአሲዚው መንፈስ የሁሉም ሃይማኖቶች የጋራ ውይይት እና ጸሎት ያነቃቃው አዲስ ማኅበራዊ እና ሃይማኖታዊ ወቅት በውይይት ታሪክ አንድ ምዕራፍ ሆኖ ቀጣይነቱ የማይታበል መሆኑም ይኸው ዘንድሮ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. የሁሉም ሃይማኖቶች መሪዎች ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ጋር በመሆን የሚፈጽሙት የጸሎት አስተንትኖ እና የውይይት መርሃ ግብር ያረጋግጥልና።
የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል ትላትና መርሃ ግብሩን በማስደገፍ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የተሳታፊዎች ብዛት እና ሥም ዝርዝርም በማሳወቅ፣ ከምሥራቅ አቢያተ ክርስትያን ከቁስጥንጥንያ የሚመጡት ተሳታፍያን ልኡካን የሚመሩት የውህደት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ በርጠለሚዮስ አንደኛ እንዲሁም የመላ ሩሲያ እና ሞስኮ ኦርቶዶክስ ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል አንደኛን በመወከል አቡነ አለክሳንደር በጠቅላላ 17 ልኡካን፣ የሶሪያ ኦርቶዶክስ ፓትሪያርክ የአርመን ሐዋርያዊት ቤተ ክርስትያን፣ የሶሪያ ማላንካረስ ኦርቶዶስክ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ፣ የምስራቅ አሲራ ቤተ ክርስትያን ልኡካን ሌሎች 13 ከምዕራብ አቢያተ ክርስትያን ልኡካን፣ ከነዚህም ውስጥ የውህደት አንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን መንፈሳዊ መሪ የካንተርበርይ ሊቀ ጳጳስ ሮዋን ዊሊያምስ የሚመራው የአንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን ልኡካን፣ የዓለም ፈደራላዊት ሉተራን አቢያተ ክርስትያን ልኡካን፣ የተሃድሶ ዓለም አቀፍ አቢያተ ክርስትያን ውህደት ልኡካን የሜቶዲስት ዓለም አቀፍ አቢያተ ክርስትያን ምክር ቤት ልኡካን የዓለም አቀፍ የአይሁድ ሃይማኖት ልኡካን የእስራኤል ታላቁ የአይሁድ ሃይማኖት መምህር ጭምር እንደሚሳተፉ የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል መግለጫ አስታወቀ።
የክርስትና እና የአይሁድ ሃይማኖት ክፍል ያልሆኑት የሌሎች ጥንታውያን ባህላውያን ሃይማኖቶች ተጠሪዎች ከአረብ እና ከመካከለኛው ምሥራቅ በጠቅላላ 48 የምስልምና ሃይማኖት ተጠሪዎች ከነዚህም ውስጥ የሳውዲ አረቢያ ልኡክ፣ የካውካሶ የምስልምና ሃይማኖት መስተዳድር ሊቀ መንበር፣ የማህትማ ጋንዲ ወንድም ልጅ የሚገኙባቸ የሂንዱ ሃይማኖት ልኡልካን፣ የሲክ የዞራኦስትሪያን የቡዲስት የኮንፉቾ የሺንቶይስቲ ከአፍሪካ እና ከላቲን አመሪካ ባህላውያን ሃይማኖት ልኡካን የሚገኙባቸው በጠቅላላ 176 መሆናቸው ከተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.