2011-10-19 14:46:58

ብፁዕ ካርዲናል ትሩክሶን፥ የቅዱስ አባታችን ጥሪ ለሁሉም መልካም ፈቃድ ላላቸው ሰዎች


ልክ እንደ የዛሬው 25 ዓመት በፊት በእንተ ላእለ ኩሉ ቤተ ክርስትያን ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ያነቃቃቱ በየዓመቱ በቅዱስ ፍራንቸስኮስ ከተማ የሚከናወነው የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራ የጸሎት የአስተንትኖ እና የውይይት መርሃ ግብር የሚያረጋግጥ ከመሆኑም ባሻገር፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ዘንድር እ.ኤ.አ. ጥቅምት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. እንዲከናወን ለሁሉም መልካም ፈቃድ ላላቸው የሃይማኖት ሰዎች ያቀረቡት ጥሪ እና የጋራው ጸሎት አስተንትኖ እና ውይይት መርሃ ግብር በማስመልከት ትላትና የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ጋር በመሆን ጋዜጣዊ መግለጫ በማቅረቡ መርሃ ግብር ጳጳሳዊ የፍትህ እና የሰላም ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ፒተር ኮድዎ አፒያ ቱርክሶን ከተለያይሁ ሃይማኖቶች ጋር የጋራው ውይይት የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ፒየር ልዊጂ ቸላታ መሳተፋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ብፁዕ ካርዲናል ቱርክሶን በአሲዚ የሚካሄደው የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራው ጸሎት አስትንትኖ እና ውይይት ከተለያዩ 50 አገሮች የተወጣጡ የተለያዩ ሃይማኖቶች መሪዎች የሚያሳትፍ መሆኑና የወንድማማችነት አድማስ የሚያንጸባርቅ ቅዱስ አባታችን የዚህ መንፈስ ምስክር በመሆን ወደ አሲዚ መንፈሳዊ ንግደት በማከናወን ሁሉም እንደ አንድ ቤተሰብ በአንድ ጥላ ሥር የሚያሰባስብ ዕለት ይሆናል፣ በቅሩቡ በግብጽ እና በተለያዩ አገሮች የታየው ማኅበራዊ ውጥረት በማስታወስ፣ ሁሉም ሃይማኖትን ተገን በማድረግ የሚሰነዝረው ጸረ ሰብአዊ ጥቃት የሁሉም ሃይማኖት መሪዎች በጋራ ተቀባይነት የሌለው ጸረ ሃይማኖት ተግባር መሆኑ የሚመሰክሩበት፣ ሃይማኖታዊ ግጭቶች ለገዛ እራሱ የሃይማኖት እውነተኛው ባህርዩን የሚቀናቀን ከሃይማኖት የሚያርቅ ጸረ እግዚአብሔር ተግባር መሆኑ በይፋ የሚስተጋቡበት የተቀደሰ መርሃ ግብር ነው ብለዋል።
አክለውም እውነተን ለመሻት የሚደረገው ጉዞ አክራሪነት እና ጽንፈኝነት እርሱም ሰላም ሊረጋገጥ የሚቻለው የገዛ እራስ እማኔ ለሌሎች ባስገዳጅ እንዲቀበሉት የማድረጉ ዓላማ የማረማመዱ ተግባር ተቀባይነት የሌለው ምርጫ መሆኑ የሚገለጥበት ሁኔታ ጭምር ነው። ስለዚህ የጋራው ግኑኝነት ውይይት በዚህ ባለንበት ዓለም ከሚከሰቱት ሁኔታዎች አኳያ ምንኛ አስፈላጊ መሆኑ ለመገንዘብ ይቻላል። ይህ የምንኖርበት ዓለም ዓለማዊነት ትሥሥር መኖር ግድ በሆነበት ወቅት የውህደት መንፈስ ያስከተለ ሁሉንም የተለያዩ ሃይማኖቶች ካላቸው መሠረታዊ መለያዊ ሃብት እውነተኛ መሠረታውያን የሆኑት እሴቶች የሚያነቃቁ እንዲሆኑም ይጠበቅባቸዋል። ይህ ደግሞ የሁሉም ሰዎች ፍላጎት እና ተስፋም ነው ብለዋል።
የዘንድሮው የአሲዚው የሁሉም ሃይማኖቶች በጋራው ጸሎት አስተንትኖ እና ውይይት እንዲሳተፉ ቅዱስ አባታችን ለአራት ኢአማንያን ምሁራን ያቀረቡት የተሳታፊነት ጥሪ፣ ቅዱስ አባታችን ይላሉ የባህል ጉዳይ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ሳንቸስ ደ ቶካ፣ አማንያን ኢአማንያን እግዚአብሔርን እና ፍጹምነት፣ ካለ ማቋረጥ እና ካለ መርካትም ዘወትር እውነትን የሚሹ ናቸው የሚለው ሐሳብ የሚመሠክር ሱታፌ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.