2011-10-17 14:55:56

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፥ “የሚያስደንቅ ጽሞና”


የቅድስት መንበር የዜና እና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በሳምንት ማገባደጃ የሚያቀርቡት የቅድስት መበር ርእሰ ዓንቀጽ በመቀጠትል ትላትና ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 9 ቀን 2011 ዓ.ም. በካላብሪያ ባካሄዱት RealAudioMP3 25ኛው ብሔራዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት እውነተኛው የሕይወት ትርጉም ለይቶ ለማወቅ እና ለመኖር የእግዚአብሔር ኅልውና ውስጣዊ ማድመጥ የሚሰጥ ጽሞና ላይ ያተኮር የጽሞና አድማስ በቃል እና በተግባር ያመለከተ ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደነበር የሚያስደንቅ ጽሞና በሚል ርእስ ሥር በማቅረብ፣ መስከረም 29 ቀን 2011 ዓ.ም. ለዓለም አቀፍ የማኅበራዊ ግኑኝነት ቀን የማስተንተኛ ርእስ እዲሆን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. “ጽሞና እና ቃል፣ የአስፍሆተ ወንጌል ጉዞ” በሚል ርእስ የተመራ እንዲሆን በማሳሰብ ቀጥለውም በካላብርያ ባካሄዱት ሓዋርያዊ ጉብኝት በክልሉ የሚገኘው ሰራ ሳን ብሩኖ የቸርቶሳ የመናንያን ገዳም በመጎብኘት የጸሎት ኩራዝ ዘወትር ቦግ በማድረግ በጽሞና እና ተመንኖ የሚኖርበት ሥፍራ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛን በገዳሙ እንደደረሱ በመቀበል የምስጋና ቃል ያሰሙት የገዳሙ አበምኒየት ማብራራታቸው አባ ሎምባርዲ በርእሰ አንቀጹ በማስታወስ፣ በቃል እና በጽሞና እርሱም በጸሎት እና በአብሣሪነት መካከል ምንም ዓይነት ጸረ መሠረተ ሐሳብ ወይንም ተቃራኒነት የለም፣ ምክንያቱም ጽሞና ወይንም ጸጥታ የእግዚአብሔርን ቃል ለማዳመጥ እና ለማስተናገድ መሠረታዊ መግቢያ ወይም የመነሻ ተግባር ነው። የእግዚአብሔር ቃል ጥልቅ ትርጉም የሚሰጥ በጽሞና የማዳመጥ ጊዜ በመኃል የሚኖር የጽሞና ጊዜ እጅግ አስፈላጊ ነው።
በዚህ አካላዊ እና አእምሮአዊ ውካታና ጫጫታ በተከናነበው ዓለም የባህታውያን እና የመናንያን ሕይወት እጅግ የሚደነቅ ብቻ ሳይሆን በብዙ ሰዎች ልብ ውስጥ የጽሞና ጊዜ ጥማት እየቀሰቀሰው ነው። የእረፍት ጊዜአቸው በነዚህ ገዳማት ለማሳለፍ የሚሹ ቁጥር ብዛት ከፍ እያለ በመሄድ ላይ ያለው ጥልቅ ፍላጎት ያረጋግጠዋል። ስለዚህ ጽሞና ወይም ጸጥታ ባዶነት ማለት ሳይሆን የመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ የሚኖርበት መለኮታዊ የእግዚአብሔር ኅላዌ የሚረጋገጥበት የሚደመጥበት እንደ ፉጨት ያለ ቀጭን ድማጽ በቅዱስ መጽሓ አገላለጥም የዝምታ ድምጽ ማለት ሲሆን፣ የዝምታ ድምጽ የሚኖርበት ቅዱስ አባታችን እንዳሉትም ከሚሰማው ዓለም ባሻገር ያለ የተጨባጭ ጥልቅ ተጨባጭ የሚኖርበት ማለት ነው።
ቤተ ክርስትያን አስፍሆተ ወንጌል በታደሰ መንፈስ እንዲነቃቃ በማሳሰብ ላይ ባለችበት በአሁኑ ወቅት፣ የምታሰምረበት ሐሳብ፣ አስፍሆተ ወንጌል ቃለ ከማዳመጥ የሚመነጭ ነው የሚለው ሥልጣናዊ ትምህርት ጽሞና የእግዚአብሔር ሕይወት የሚደመጥበት ቅዱስ አባታችን እንዳሉት በጽሞና ለእግዚአብሔር ቅርብ በመሆን አማካኝነት ለሁሉም ሰው ዘር በተለይ ደግሞ በከፋው ድኽነት በስቃይ ከሚገኙት ጋር እንገናኛለን ያሉትን ሐሳብ አማካኝነት ርእሰ ዓንቀጹን አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.