2011-10-17 14:57:47

እራሱን የሚገልጥ እውነት


እ.ኤ.አ. ጥቅምት 15 ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 16 ቀን 2011 በቫቲካን የሲኖዶስ አዳራሽ “ለአዲስ አስፍሆተ ወንጌል አዲስ ልኡካነ ወንጌል፦ የእግዚአብሔር ቃል ያድጋል ይስፋፋልም” በሚል ርእስ ሥር RealAudioMP3 33 የተለያዩ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ልኡካን ሌሎች የተለያዩ 115 የቤተ ክርስትያን መዋቅሮች ተጠሪዎች የተለያዩ የቤተ ክርስትያን ከዳግመ አስፍሆተ ወንጌል ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎት የሚሰጡ የአገልግሎት ዘርፎች ተጠሪዎች ያካተተ በዚህ ዘርፍ ልምድ በማቅረብ የሃሳብ ልውውጥ የተከናወነበት እ.ኤ.አ. በ 2012 ዓ.ም. ጥቅምት ወር ለሚካሄደው የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ስለ ዳግመ አስፍሆተ ወንጌል ሐሳብ ከወዲሁ ያቀረበ አዲስ ልኡካነ ወንጌል ለዳግመ አስፍሆተ ወንጌል በሚል ርእስ ሥር የተመራ የዳግመ አስፎተ ወንጌል ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ያዘጋጀው ጉባኤ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ወንጌላዊ ልኡክነት ከመንፈስ ቅዱስ ኃይል ዳግም ለመወለድ በመፍቀድ መላ ቤተ ክርስትያን በዚህ በምንኖርበት ዓለም በአዲስ የተልእኮ መንፈስ ትነቃቃ ዘንድ የተገባ እና በቂ መልስ ለማቅረብ የሚችል መሆን አለበት ያሉትን ቀዋሚ ሓሳብ የዳግመ አስፍሆተ ወንጌል ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ሪኖ ፊዚከላ በማስታወስ “ለአዲስ አስፍሆተ ወንጌል አዲስ ልኡካነ ወንጌል፦ የእግዚአብሔር ቃል ያድጋል ይስፋፋልም” በሚል ርእስ ሥር የተካሄደው ጉባኤ በተጠናቀቀበት ጥቅምት 16 ቀን 2011 ዓ.ም. የዳግመ አስፍሆተ ወንጌል ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዳብሊው ዳብሊው ዳብሌው ነጥብ አለተያ ነጥብ ኦርግ በሚል አድራሻ የደረሰው ድረ ገጽ በይፋ እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 19 ቀን 2011 ዓ.ም. አገልግሎት መሥጠት እንደሚጀምር ማሳወቁ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ይኽ ድረ ገጽ ስለ ካቶሊክ እምነት ጉዳይ ለሚቀርቡት ጥያቄዎች ስለ ማኅበራዊ ጉዳይ እና ስለ ሕይወት ጉዳይ በተመለከቱ ለሚቀርቡት መሠረታውያን ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥ ድረ ገጽ መሆኑ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።







All the contents on this site are copyrighted ©.