2011-10-17 14:52:15

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፥ “የክፋት ውካታና ጫጫታ በተሞላው ዓለም የተስፋና የደስታ ምስክሮች ሁኑ”
የዳግመ አስፍሆተ ወንጌል ጉባኤ


እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 15 እስከ ጥቅምት 16 ቀን 2011 ዓ.ም በቫቲካን አዲስ ልኡካነ ወንጌል ለዳግመ አስፍሆተ ወንጌል በሚል ርእስ ሥር የተመራ የዳግመ አስፎተ ወንጌል ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት RealAudioMP3 ያዘጋጀው አቢይ ጉባኤ መካሄዱ የሚዝከር ሲሆን። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ወንጌላዊ ልኡክነት ከመንፈስ ቅዱስ ኃይል ዳግም ለመወለድ በመፈቅድ መላ ቤተ ክርስትያን በዚህ በምንኖርበት ዓለም በአዲስ የተልእኮ መንፈስ ትነቃቃ ዘንድ የተገባ እና በቂ መልስ ለማቅረብ የሚችል መሆን አለበት ያሉትን ሓሳብ የዳግመ አስፍሆተ ወንጌል ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ሪኖ ፊዚከላ በማስታወስ “ለአዲስ አስፍሆተ ወንጌል አዲስ ልኡካነ ወንጌል፦ የእግዚአብሔር ቃል ያድጋል ይስፋፋልም” በሚል ርእስ ሥር 33 የተለያዩ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ልኡካን ሌሎች የተለያዩ 115 የቤተ ክርስትያን መዋቅሮች ተጠሪዎች የቤተ ክርስትያን ከዳግመ አስፍሆተ ወንጌል ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎት የሚሰጡ የአገልግሎት ዘርፎች ተጠሪዎች ያካተተ በዚህ ዘርፍ ልምድ በማቅረብ የሃሳብ ልውውጥ መርሃ ግብር ሥር ያስጀመሩት እ.ኤ.አ. በ 2012 ዓ.ም. ጥቅምት ወር ለሚካሄደው የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ስለ ዳግመ አስፍሆተ ወንጌል ሐሳብ የሚያቀርበው ዓውደ ጥናት ትላትና ተጋባእያኑ በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 09.30 በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ባቀረቡት መሥዋዕተ ቅዳሴ በመሳተፍ እና ከቅዱስነታቸው መሪ ቃል በመቀበል መፈጸሙ የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።
ተጋባእያኑን ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ጋር በተገናኙበት ወቅት ቅዱስነታቸው “የክፋት ውካታና ጫጫታ በተሞላው ዓለም የተስፋና የደስታ ምስክሮች ሁኑ” በሚለው መሠረታዊ ጥሪ ላይ ያተኮረ ባሰሙት ሥልጣናዊ አስተምህሮ፣ ማኅበረ ክርስትያን አለ ምንም ፍራት እና በሚታየው የግድ የሌሽነትን የስደት እና የአለ መግባባት መንፈስ ተስፋ ሳይቆርጥ የተስፋ ምልክት በመሆን፣ የእግዚአብሔር ቃል በደስታ ለሌሎች ለማካፈል ይተጋ ዘንድ አደራ በማለት፣ ልኡካነ ወንጌል በተለያዩ ችግሮች ሳይበገሩ ዓለም ካንቀላፋበት ከግድ የለሽነት መንፈስ ለማነቃቃት ይተጉ ዘንድ መጠራታቸውን በማሳሰብ የአዲስ ልኡካነ ወንጌል ማንነት ለይተው በማሳወቅ፣ የአዲስ ኪዳን ብሥራት እምቢተኝነት እና ዝግ መሆን አደጋ የሚያጋጥመው ቢሆንም ቅሉ፣ የእግዚአብሔር ቃል በግብረ ሐዋርያት ምዕራፍ 12 ከቁጥር 24 እንደተረጋገጠው ዘወትር እያደገና እየተስፋፋ ይሄዳል ምክንያቱም፣ በቅድሚያ ደረጃ የእኛ የተግባር ብቃት ጥገኛ ሳይሆን በደካማነት ኃይሉን በሚገልጥ በእግዚአብሔር ላይ የጸና ስለ ሆነ እና ቀጥሎም የእግዚአብሔር ቃል በመንገድ ዳር በጭንጫ በእሾህ መካከል ወድቆ የሚቀር ሳይሆን ወድቆ ብዙ ፍሬ ለማፍራት በሚችልበት በመልካሙ መሬት ላይም ስለ ሚወድቅ ነው። ስለዚህ ልኡካነ ወንጌል የአሕዛብ ልብ እና አእምሮ ክርስቶስን ለሚያቀርበው ጥሪ ክፍት እንዲሆን እና ከእርሱ ጋር በመገናኘት የእርሱ ደቀ መዛሙርት እንዲሆኑ ካለ ምንም ፍርሃት እንዲተጉ አሳስበዋል።
የዳግመ አስፍሆተ ወንጌል የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ለቤተ ክርስትያን ተልእኮ በተለይ ደግሞ በጥንታውያን በአሁኑ ወቅት ለእግዚአብሔር ቃል ግድ የለሽነት ብሎም የጠላትነት መንፈስ እያሳየ ላለው የክርስትያን እምነት የባህል መሠረት ባላቸው አገሮች ቤተ ክርስትያት ለምታከናውነው ተልእኮ ለመደግፍ ታልሞ የተቋቋመ መሆኑ በማብራራት፣ ወቅታዊው ዓለም ቃል ገዛ እራሱ ሕይወት እና መንገድ የሆነው ክርስቶስ የመኖር ጥበብ የእውነተኛ ደስታ መንገድ የሚያስተምር መሆኑ የሚያበሥሩ እና የሚመሰክሩ ልኡካን እጅግ ያስፈልገዋል ብለዋል።
የምንኖርበት ዓለም ስለ እግዚአብሔር ለመናገር ይቻለውም ዘንድ የእግዚብሔር ቃል የሚናገሩ ምስክሮችን ይሻል ካሉ በኋላ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ያዳነው በመልካም እና በማራኪ ቃል ሳይሆን በስቃዩ እና በሞቱ ነው። ስለዚህ በእውነት በመሬት ወድቃ የምትሞት የስንዴ ቅንጣት ባኅርያዊ ደንብ ኅያው በመሆኑ ለሌሎች ሕይወት ለመስጠት የገዛ እራሳችን ሕይወት ሳንሰጥ የሚቻል አይደለም ብለዋል።
ሞት አፈሸንፎ ዘለዓለማዊ ሕይወት ከሰጠን ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሆን ይኸ መጻኢ በእርግጠኝነት ለማተኮር ብቃት ያላችሁ ትእምርተ ተስፋ ሆኑ፣ ለሁሉም ሁሉን ነገር አዲስ በሚያደርገው በመንፈስ ቅዱስ መነቃቃት በሚሰጠው በተጋጋለ የስሜት መንፈስ የእምነትን ደስታን አበሥሩ በማለት የሰጡት ሥልጣናዊ አስተምህሮ በማጠንቃቃ ለሁሉም ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው አሰናብተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.