2011-10-17 14:53:55

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፥ ኤኮኖሚን ሰብአዊነት ማልበስ


እ.ኤ.አ. ግንቦት 15 ቀን 1891 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ሊዮነ 13ኛ የማኅበራዊ ጉዳይ ጥያቄዎች በጥልቀት በመለየት ቤተ ክርስትያት የተሟላ እና ቅጥ ባለው አገባብ የቤተ ክርስትያን የማኅበራዊ ጉዳይ ትምህርት የምትገልጥ ረሩም ኖቫሩም አዳዲስ ነገሮች በሚል ርእስ ሥር የደረስዋት ዓዋዲት መልእክት RealAudioMP3 ዝክረ መቶኛ ዓመት ምክንያት ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ግንቦት አንድ ቀን 1991 ዓ.ም. ከቀዝቃዛው ጦርነት በመንደርደር ኅብረሰብአዊነት እና መደብ አልባ ሥርዓተ ማኅበር ያኖረ የዓለም እና የሰብአዊ የታሪክ ገጠመኝ ላይ በማነጣጠር የረሩም ኖቫሩም የአዳዲስ ነገሮች ዓዋዲ መልእክት ወቅታዊነት የሰጠ በተሟላ ደንብ እና ቅጥ የቤተ ክርስትያን የማኅበራዊ ጉዳይ ትምህርት የሚትዘርዘር ቸንተዙሙስ አኑስ-መቶኛ ዓመት በሚል ርእስ ሥር የደረስዋት ዓዋዲት መልእክት ዝክረ 20ኛው ዓመት ምክንያት “ቤተሰብ እና የኤኮኖሚ አውታሮች በሚል ርእስ ሥር በተመራው ባለፈው ቅዳሜ የተጠናቀቀው የሁለት ቀን ዓወደ ጥናት ተጋባእያን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ተቀብለው “ከምን ጊዜም በበለጠ በአሁኑ ወቅት ለኤኮኖሚ ሰብአዊ ገጽታ ማጎናጸ እጅግ ወሳኝ መሆኑ የሚያበክር ሥልጣናዊ አስተምህሮ መለገሳቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ አቀባበል የተደረገላቸው ተጋባእያንን ወክለው በቅዱስነታቸው ፊት የምስጋና ንግግር ያሰሙት የቸንተዚሙስ አኑስ ማኅበር ሊቀ መንበር ዶሚንጎ ሱግራንየስ ቢከል ሲሆኑ፣ በመቀጠል ቅዱስ አባታችን፣ ቤተሰብ እና ሥራ የሰው ልጅ ጥሪ ግንዛቤ የሚረጋገጥበት የታደለ ሥፍራ ነው። የር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ፋሚሊያሪስ ኮንሶርዚዮ-ቤትሰብአዊ ማኅበርነት” በሚል ርእስ ሥር ቤተሰብ በዚህ በምንኖበት ወቅታዊው ዓለም ላይ ተንተርሰው የደረስዋት ሓዋርያዊ ምዕዳን በመጥቀስ በዚህ የቁጠባ እና የኤኮኖሚ ቀውስ ባንሰራፋበት በአሁኑ ወቅት ኤኮኖሚ የኅብረተሰብ ማእከል የሆነው የቤተሰብ ጥቅም የሚንከባከብ መሆን አለበት የሚለው ሐሳብ በአክብሮት የሚታሰብ መሆን አለበት ብለዋል።
የአንድ ማኅበርሰብ ሕንጸት ሕይወት ለማገልገል ያለመ መሆኑ ገልጠው፣ ይህ ደግሞ በማኅበራዊ እና በቤተ ክርስትያናዊ ዘርፍ ያለው ሱታፌ ምን መሆኑ ለይቶ የሚያሳስብ ነው። የዚህ የሕይወት ሕንጸት መሠረትም እውነተኛው ፍቅር መሆኑ ገልጠው፣ ስለዚህ ቤተሰብን የሚያጸናው የሚያንጸው ይኽ እውነተኛው ፍቅር ነው። ቤተሰብ የሁሉም መሠረት ነው። በቅንነት የመኖር የተስተካከለ ጠባይ ለመደጋገፍ ለግብረ ሠናይ እና የመተሳሰብ ብሎም ለኃላፊነት ሥነ አመክንዮ መሠረት በማኅበረሰብ በኅብረተሰብ በሥራው ዓለም በኤኮኖሚው ዓለም በመልካም አገባብ ለመኖር የሚያግዝ ሥርዓት እና ትምህርት የሚቀሰምበት ማእከል መሆኑ ማስረዳታቸው የቅድስ መንበር መግለጫ አስታወቀ።
በዚህ አኳያ ቤተሰብ ነገር ሳይሆን ንቁ ባለ ቤት በመሆን ምክንያት ኤኮኖሚ በጠቅላላ የምንኖርበት ዓለም ሰብአዊ ልክነት ሊኖረው ይገባል። ስለዚህ የሥራው ዓለም ቤተሰብ እግምት ውስጥ የሚያስገባ መሆን አለበት። ቤተሰብ እና ሥራ የሚነጣጠሉ ሳይሆን ሁለቱን የሚያገናኝ ከዚህ በተያያዘ ሥርዓተ አዲስ ውህደት የሚረጋገጥበት መሆን አለበት በማለት የቤተ ክርስትያን የማኅበራዊ ጉዳይ አንቀጸ ትምህርቶች ይኸንን ለዚህ ሁሉ መሠረት የሆነው ሐሳብ እና ትምህርት በማቅረብ ለኅብረተሰብ አቢይ አገልግሎት ይሰጣል። ካሪታስ ኢን ቨሪታተ እውነት በሓቅ የተሰኘችው ዓዋዲት መልእክት ለማቅረብ ያነቃቃቸውም ፍቅር ሥነ አመክንዮ መሠረት አለው የሚለው እውነት መሆኑ በማስታወስ፣ ቤተሰብ የሚያጸናው የፍቅር ሥነ አመክንዮ ኩላዊነት መልኩ እንዴት ለማልበስ እንደሚቻል እና ዓለም የዚህ የላቀው የፍቅር ትርጉም የሚኖርበት ለማድረግ ምን መደረግ አለበት ለሚለው ጥያቄ የኩላዊት ቤተ ክርስትያን መልስ ለማቅረብ መሆኑም አብራርተዋል።
ክርስትያን፥ የሰው ልጅ ክብር የሚጸናባቸው እሴቶች ኅያዊነታችውን ለማቀብ እና ለመመስከርም ብሎም የጋራው ጥቅም መተባበር እና መተሳሰብን በማነቃቃት በጠቅላላ የሰው ልጅ የእግዚአብሔር ቤተሰብ በመሆኑ በሚገልጥ ሂደተ እያደገ እንዲሄድ ግድፈቶች እና የክፋት መንፈስ ማውገዝ ይጠበቅባቸዋል ግዴታም አለባቸ ካሉ በኋላ አያይዘውም በአዲሱ አስፍሆተ ወንጌል የቤተሰብ ሚና ማእከል መሆኑ በማስመርም፣ ቤተሰብ የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተቀባይ ብቻ ሳይሆን የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ንቁ ክፍል በመሆኑም፣ በተግባር እና በቃል የማኅበርሰብ ውስጣዊ ሕይወት እና ፍቅር በመሆን ለቤተ ከርስትያን ለኅብረተሰብ አገልግሎት የሚሰጥ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.