2011-10-14 14:03:54

የዓረብ አገሮች እና የኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት፣ ለግብጽ ማኅበረክርስትያን ድጋፍ


የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ባለፈው ረቡዕ የተለመደው ረቡዓዊ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ አቅርበው በሽግግር RealAudioMP3 በምትገኘው ባዲሲቷ ግብጽ ታሪክ ጥቁር ምዕራፍ የሆነው ባለፈው እሁድ በኦርቶዶክስ ምእመናን ላይ የተጣለው ጥቃት፣ ላስከትለው ሐዘን ተካፋይ መሆናቸው በመግለጥ፣ የውሁዳን የኅብረተሰብ ክፍል መብት እና ፈቃድ ጥበቃ ለማኅበራዊ ሰላም መሠረት ነው። ሁሉ ምእመን የግብጽ ሕዝብ ፍትህ የርእስ በእርስ መከባበር ነጻነት የሁሉም ዜጋ ሰብአዊ ክብር ጥበቃ ከማረጋገጥ የሚመነጨው እውነተኛው ሰላም እንዲታደል እንዲጸልይ በማለት ያቀረቡት የሰላም ጥሪ መሠረት፣ የአረብ እና የኤውሮጳ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት የተጣለው ጥቃት በማውገዝ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የግብጽ ማኅበረ ክርስትያንን ለብቻው እንዳይተወው ቅርብ በመሆን ድጋፉን እና ትብብሩን ያቀርብ ዘንድ የጥሪ መልእክት አስተላልፈዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም ግብጻዊ የእሱሳውያን ማኅበር ኣባል የሥነ ምስልምና ሊቅ አባ ሳሚር ካሊል ሳሚር በግብጽ ስለ ተከሰተው ጸረ ክርስትያን ዓመጽ በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በአሁኑ ወቅት በሽግግር በምትገኘው ግብጽ የተለያዩ የምስልምና ሃይማኖት አክራሪያን የፖለቲካ ሰልፎች አሉ፣ በተለይ ደግሞ ሳላፊት እና ገሚሱ እስላማውያን ወንድሞች የተሰየመው የፖሊቲካ ሰልፍ የሚከትሉ ናቸው። እነዚህ አክራሪያን ሙስሊሞች በግብጽ ክርስትያን ዜጎች አቢያተ ክርስትያን የመገንባት መብት የላቸውም የሚል አመለካከት የሚያንጸባርቁ ናቸው። ስለዚህ ይኸንን አመለካከት በመከተል የተለያዩ አቢያተ ክርስትያን በእሳት ያጋያሉ። ክርስትያኖችን ያሳድዳሉ። ስለዚህ በአገሪቱ ከእስላማዊ እምነት ውጭ የሆነው የአኗኗር ዘይቤ እንዳይኖር ማገዱ በተለይ ደግሞ የሰላም መሠረት የሆነው የሃይማኖት ነጻነት ምጣስ የሚያሳዝን ነው። የአገሪቱ ክርስትያን ማኅበርሰብ በአሁኑ ወቅት ወደ ስደት እያቀና ነው ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን ያቀረቡት የሰላም ጥሪ ጸረ ሁሉም ግዚያዊ ተስፋዎች በመሆን እውነተኛ ተስፋ ለመኖር እርሱም ተስፋ ላለ መቁረጥ የሚደግፍ ነው ካሉ በኋላ፣ በግብጽ ስለ ዴሞክራሲ ሥርዓት ሕንጸት እጅግ አስፈላጊ ነው። የአረብ አገሮች ለውጥ ጠሪው ሕዝባዊ ዓመጽ፣ የማኅብራዊ የሰላም ኑሮ ግንባት ነው። ስለዚህ ለጸንፈኝነት እና ለአክራሪነት ለም መሬት እንዳይሆን ነቅቶ መጠበቅ ይገባል በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃልዋል።
የመላ ሩሲያ እና ሞስኮ የኦርቶዶክስ ቤተ ክስትያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ክሪል ከሊቢያ እስከ ሶሪያ የተቀጣጠለው የዓረብ አገሮች ሕዝባዊ አብዮት ሕዝባዊ ባህርዩ እና ግብታዊነቱ አጠያያቂ ነው ካሉ በኋላ፣ የተባበሩት መንግሥታት እና ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ በግብጽ ለክርስትያን ማኅበረሰብ ጥበቃ ይተጋ ዘንድ ጥሪ አቅርበው፣ ሁሉም ይኽንን በግብጽ የተከሰተው ጸረ ኦርቶዶክስ ምእመናን ጥቃት በዝምታ እና በቸልተኝነት ሳይመለከት፣ ለክርስትያን ወንድሞች ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ጥበቃ እንዲንቀሳቀስ በማሳሰብ፣ በመጨረሻ የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖት መሪዎች በጋራ ለሰላም ግንባታ እና ለጋራው የእርስ በእርስ መግባባት ደጋፊ በሆነው ተግባራዊ ውሳኔ አማካኝነት እንዲተጉ አደራ ማለታቸው ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አመለከተ።







All the contents on this site are copyrighted ©.