2011-10-14 13:55:33

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. መተባበር ሰላም እና የጋራ ጥቅም


ትላትና ጧት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የሆንዱራስ ርእሰ ብሔር ፖርፊሪዮ ሎባ ሶሳ በቅድስት መንበር ተቀብለው ማነጋገራቸው የቅድስት መንበር RealAudioMP3 የዜና እና የማኅተም ክፍል ያሰራጨው መግለጫ አስታወቀ።
ርእሰ ብሔር ፖርፊሪዮ ሎባ ሶሳ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ስንበት ቀጥለው በቅድስት መንበር የውጭ ግኑኝነት ጉዳይ ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ዶሚኒክ ማምበርት በተሸኙት ከቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ ጋር መገናኘታቸው የቅድስት መንበር የዜና እና ማኅተም ክፍል ከሰጠው መግለጫ ለመረዳት ሲቻል፣ በተካሄዱት ሁለቱ ግኑኝነቶች፣ በሆንዱራስ የምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ለሰብአዊ ማኅበራዊ እድገት እና ለሆንዱራስ ብልጽግና በተለይ ደግሞ በሕንጸት እና በጤና ጥበቃ መስክ ብሔራው እርቅ እንዲረጋገጥ የምተሰጠው አስተዋጽዖ የሚደነቅ መሆኑ እንደተሠመረበት እና የሆንዱራስ ርእሰ ብሔር ቤተ ክርስትያን በዚህ ዘርፍ የምትሰጠው አስተዋጽዖ ትቀጥልበት ዘንድ አደራ ማለታቸው የቅድስት መንበር የዜና እና የማኅተም ክፍል መግለጫ ያመለክታል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በተካሄደው ግኑኝነት የእርስ በእርስ መግባባት መተባበር ሰላም እና ካለ መታከት ዘወትር የማኅበራዊ ጥቅም ማስቀደም ለአንዲት አገር እድገት መሠረት ነው እንዳሉም የቅድስት መንበር የዜና እና ማኅተም ክፍል መግለጫ ጠቁሞ፣ ርእሰ ብሔር ፖርፊሪዮ ሎባ ሶሳ የሆንዱራስ ዓለም አቀፍ ግኑኝነቶች እና በዓለም አቀፍ ደረጃ አንገብጋቢ ናቸው በሚባሉት ጥያቄዎች የሆንዱራድ አመለካከት ምን እንደሚመልስ በስፋት ማብራራታቸው አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.