2011-09-29 19:08:40

የር.ሊ.ጳ የጥቅምትና የኅዳር ወሮች ፕርግራም


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ የዘንድሮውን የኤውሮጳውያን ዓመት በአፍሪቃ በሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉዞና በጣልያን አገር በሚያደርጉት ሐውጾተ ኖልዎ እና ሌሎች በመንበረ ጴጥሮስ በሚደረጉ ሥርዓተ አምልኮአዊ አገልግሎቶች እንደሚፈጽሙት ከቅድስት መንበር የወጣ ዜና አመልክተዋል። ይህንን ያመለክቱት የቅዱስነታቸው የሥርዓተ አምልኮ ተግባሮች አስተማሪ የሆኑ ብፁዕ አቡነ ጒዶ ማሪኒ ናቸው፣
ብፁዕነታቸው በሰጡት ማብራርያና የቅዱስነታቸው መርኃ ግብር መሠረት ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ እፊታችን ጥቅምት 9 ቀን 2011 ዓም በላመጽያ ተርመ እና ሰራ ሳን ብሩኖ በሚባሉ የካላብርያ ክፍለሃገር ከተሞች ሐውጾተ ኖልዎ ያደርጋሉ፣ ላመጽያ ተርመ የሚባለ በካታንዛሮ ክልል የሚገኛ ሃገረ ስብከት ነው። በመርኃ ግብሩ መሠረት ቅዱስነታቸው እኁድ ጥቅምት 9 ቀን ጥዋት 9፡15 በላመጽያ አለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፍያ በመገኘት ወዲያውኑ መሥዋዕተ ቅዳሴ ያሳርጋሉ ከዛ የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ በማቅረብ ከምእመናኑ ጋር የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ያሳርጋሉ፣ ከክልሉ ጳጳሳት ጋር ምሳ ከተጋበዙ በኋላ በሄሊኮፕተር ወደ ሰራ ሳን ብሩኖ ይጓዛሉ። ማምሻውን በጥንታዊው የቸርቶዚና ገዳም ከሚኖሩ መነኮሳን ጋር ጸሎተ ሠርክ እንደሚያሳርጉም ተመልክተዋል። ጉብኝቱን ከፈጸሙ በኋላ ሰባት ሰዓት ተኩል ወደ መንበራቸው ሮማ ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል፣
ቅዱስነታቸው ይህንኑን ሐውጾተ ኖልዎ ከፈጸሙ ከአንድ ሳምንት በኋላ በአዲሱ የስብከተ ወንጌል ጳጳሳዊ ምክር ቤት በተዘጋጀው ለጥቅምት 15 እና 16 ቀኖች የሚካሄደውን ጉባኤ በመሥዋዕተ ቅዳሴ ይከፍታሉ። በጉባኤው የሃገረ ስብከቶች ተወካዮ መንፈሳውያን ማኅበራት ቊምስናዎች እና በምዕራቡ ክፍለ ዓለማችን ለስብከተ ወንጌል የተላኩ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን እንቅስቃሴዎችና ማኅበራት አባላትም እንደሚሳተፉ ተመልክተዋል።
ከዚሁ ጉባኤ አንድ ሳምንት በኋላ ደግሞ ጥቅምት 23 ቀን 2011 ዓም፡ የሳቨርያኒ መሥራች የሆኑ ብፁዕ ጒዶ ማርያ ኮንፎርትና ከኢጣልያ ቅዱሳን ካህናት አንዱ የሆነው የልዊጂ ጓነሎ እንዲሁም የቅዱስ ዮሴፍ ደናግ መሥራች የሆነው የቦኒፋቻ ሮድሪግወዝ ካስትሮ ሥርዓተ ቅድስና ያውጃሉ፣
ጥቅምት 26 ቀን ደግሞ በብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በተጀመረው የአዚሲ የኅብረት ጸሎት ለመሳተፍ እንዲዘጋጁ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከምእመናን ጋር አብረው ጸሎት ያሳርጋሉ፣
በመጀመርያው የኅዳር ወር ቀኖች የተለመደውን የቅዱሳንን የሙታን ዕለታትን በተለያዩ ሥርዓተ ጸሎቶች በቫቲካን ያስታውሳሉ፣
በመጨረሻም ከኅዳር 18 እስከ 20 ቀን በበኒን ሐዋርያዊ ጉዞ እንደሚያደርጉ አጋጣሚውም የበኒን ክርስትና 150 ዓመት መሆኑ ሲመለከት ቅዱስነታቸውም ለአፍሪቃ ጳጳሳት የሁለተኛው የአፍሪቃ ጳጳሳት ሲኖዶስ ውጤት የሆነውን ሐዋርያዊ ምዕዳናቸውን ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.