2011-09-29 19:04:43

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ።


ባጭሩ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ያቀረቡት፣ ውድ ወንድሞችና እኅቶች፡ ባለፈው የሳምንት መጨርሻ ላይ በትውልድ አገሬ ሃገረ ጀርመን ሐዋርያዊ ጉብኝት አድርጌ ነበር። ባደረግሁት ሐውጾተ ኖልይ የበርሊን የኤርፉት የኣይኽስፈልድ እና የፍራይቡርህ ከተሞችን ጎበኘሁ፣ የሐውጾተ ኖልዎየ መሪ ቃል “እግዚአብሔር ባለበት ብሩኅ የመጪ ግዜ ተስፋ አለ” የሚል ሆኖ ይህም ለሕይወታችን ማለትም ለኑሮአችንና ለኅልውናችን ትርጉም የመጨረሻው ትርጉም የሚሰጥና የሁሉ መልካም ነገር ምንጭ በመሆን ፍትሓዊ ነጻና የሚያባብ ኅብረተሰብ ለመገንባት በምናደርገው ጥረት የሚደግፈን እግዚአብሔር መሆኑን ለማስታወስ ነው፣ በበርሊን ባደርግሁት ሐዋርያዊ ጉብኝት ለጀርመን ፓርላመንት አባላት ንግግር ለማድረግ በቃሁኝ። ከማርቲን ሉተር ዝክር ልዩ ትሥሥር ባለው በኤርፉርት ቆይታ ደግሞ ከጀርመን ወንጌላዊት ቤተ ክርስትያን ምክር ቤት በመገናኘት ለክርስትያን አንድነት አብረን ለመጸለይ በቅተናል። በኤጸልስባኽ ሥርዓተ ዋዜማ ዘሌሊትና በኤርፉርት ባሳረግነው መሥዋዕተ ቅዳሴ የዞኑ ኃያል የክርስትና እምነት ምስክርነት ባህልን ሊያስታውሱ በማሳሰብ በቅድስና እንዲኖሩና ለኅብረተሰቡ ኅዳሴ እንዲሰሩ ጥሪ አቀርብኩኝ። በመጨረሻም በፍራይቡርግ ባሳረግነው የሌሊት ሙሉ ጸሎት ስግደትና አስተንትኖ እንዲሁም በነጋታው ባሳረግነው መሥዋዕተ ቅዳሴ ለመጪው የጀርመን ቤተ ክርትያን ለክርስቶስ ባላቸው እምነት ትልቅ ተስፋ ከሚሰጡ ብዙ ወጣቶች ጋር ተገናኘሁ፣









All the contents on this site are copyrighted ©.