2011-09-21 17:21:38

ርሊጳ በነዲክቶስ እና የጀርመን ሐዋርያዊ ጉብኝት እና ዝግጅት ፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16 በትውልድ ሀገራቸው

ጀርመን የአራት ቀናት ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማድረ ከሐዋርያዊ መንበራቸው እንደሚነሱ የሚታወስ ነው ።

ቅድስነታቸው ከመስከረም 22 ቀን እስከ 25 እኤአ ጀርመን ላይ በሚቆዩበት ግዜ የተለያዩ ሀገረ ስብከቶች ይገበ`ኛሉ ከሀገሪቱ መንግስት የበላይ ባለስልጣናትም እንደሚገናኙ መርሃ ዑደታቸው ያመለክታል ።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ሐዋርያዊ ዑደት የሚያካሄድባቸው የጀርመን ሀገረ ስብከቶች ርእሰ ከተማ በርሊን ኤርፉርት ፍራይቡርግ እና ኤትዘልስ ባኽ መሆናቸው ታውቆዋል።

የጀርመን ህዝብ 82 ሲሆን ከዚህ 25 ሚልዮን ካቶሊካውያን መሆናቸው ይታወቃል።

ቅድስነታቸው በቡንደስታግ በጀርመን ፓርላማ ተገኝተው ንግግር እንደሚያደርጉም የጀርመን ሐዋርያዊ ዑደታቸው መርሃ ዑደት ያሳያል።

ለመንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ ከተሰየሙ 2005 እኤአ የውልድ ሀገራቸው ጀርመን ሲጐበኙ ይህ ሶውስተኛ ግዜ መሆኑ የሚታወስ ነው ።

የቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ የጀርመን ሐዋርያዊ ዑደት

እግዝአብሔር ባለበት ቦታ መጻኢ አለ ሕይወት አለ በተሰየመ መሪ ቃል እንደሚከናወን ቫቲካን ላይ የወጣ መግለጫ አስታውቀዋል።

ይሁን እና በጀርመን የቅድስት መንበር ሐውርያዊ ወኪል ማለት አምባሳደር ብፁዕ አቡነ ጂ ክላውደ ፐሪሰት እንዳመለከቱት ፡ ቅድስነታቸው በጀርመን የሚያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝ ለሕብረተ ሰብ ብሩህ ተስፋ ለመስጠት ክርስትያናዊ እሴቶች ለመቀስቀስ ነው ።

ጀርመን ጨምሮ በኢንዱስትሪ የበለጸጉ የምዕራብ ሀገራት እምነታቸው እየላላ መምጣቱ ያስታወሱ በጀርመን የቅድስት መንበር ሐውርያዊ ወኪል ብፁዕ አቡነ ጂን ክላውደ ፐሪሰት የበነዲክቶስ ሐዋርያዊ ጉብኝት ክርስትያናዊ ባህል እና እሴቶች ለመመለስ እንደሚረዳ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ከየሌሎች እምነቶች መሪዎች እና ተወካዮች ጋር የሚያደርጉት ግንኙነት እና ውይይት ለሰላም እና ትብብር ዓቢይ ሚና እንደሚኖረው ሐዋርያዊ ወኪሉ አክለው አመልክተዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ በቅድስት መንበር የጀርመን መንግስት አምባሳደር ቫልተር ዩርገን ሽሚድ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ጀርመን ጉብኝት አስመለክተው፡

አስተያያት ሲሰጡ ቅድስነታቸው ከአሁን በፊት በጀርመን ያካሄዱት ጉብኝት ሐዋርያዊ ከቤተ ክርስትያን ጋር የተያያዘ ነበር የአሁኑ ጉብኝት ከሁለቱ ጉብኝቶች የተለየ ነው ፡ ምክንያቱም የቡንደስታግ ፓርላማ ፕረስዲዳንት ባደረጉላቸው

ጥሪ መሠረት ሀገሪቱ ላይ መንግስታዊ ይፋዊ ጉብኝት ስለ ሚያደርጉ ብለዋል።

በቅድስት መንበር የጀርመን አማባሳደር ቫልተር ዩርገን ሽሚድ በማያዝ እንደገለጡት ፡ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ቡንደስታግ ፓርላማ ፊት ቀርበው ንግግር ያደርጋሉ ከርእሰብሔር ቻንስለር እና ከተለያዩ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ይገናኛሉ ይህ ሁሉ ይፋዊ መንግስታዊ ጉብኝት መሆኑ ያመላክታል ።

ሆኖም ግን በተለያዩ ሀገር ስብከቶች ሐዋርያዊ ግብኝት ስለሚያደርጉ እና ከየካቶሊካዊት አንገሊካዊ እና የተለያዩ እምነቶች መሪዎች እና ተወካዮች ጋር ስለሚገናኙ እዚህ ላይ ሐዋርያዊ ጉብኝት ተብሎ ሊሰየም ይችላል ብለዋል በቅድስት መንበር የጀርመን መንግስት አምባሳደር ቫልተር ዩርገን ሽሚድ ።

ከአሁን በፊት ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ለፖላንድ እና ጣልያን ፓርላማዎች ንግግር ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን ፡ በነዲክቶስ 16ኛ ለቡንደስታግ ለጀርመን ፓርላማ የሚያደርጉት ንግግር ሶሰተኛ መሆኑ የሚታወስ ነው።








All the contents on this site are copyrighted ©.