2011-09-17 15:48:55

ር.ሊጳ በነዲክቶስ አዲሶች ጳጳሳት ተቀብለው አነጋግረዋል፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በቅርቡ መዓርገ ጵጵስና የተቀበሉ ጳጳሳት ቫቲካን ውስጥ ተቀብለው ማነጋገራቸው ከካስተል ጋንዶልፎ መካነ አርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት የደረሰ አስታውቀዋል ።

ጳጳሳቱ ሥርዓተ አምልኮ ላቲን እና ምስራቅ ተከታይ መሆናቸው እና በብጹዓን ካርዲናላት ማርክ ኰለት እና ለኦናርዶ ሳንድሪ ተሸኝተው ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ጋር መገናኘታቸው ዜናው ለጥቆ አመልክተዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ለኦናርዶ ሳንድሪ በቅድስት መንበር የምስራቅ ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ማሕበር ሊቀመንበር መሆናቸው የሚታወስ ነው ።

ብጹዓን ጳጳሳቱ ለህንጸተ ቤተ ክርስትያን የወረደው መንፈስ ቅዱስ ተቀብለው ከካህናታቸው ጋር ለቤተ ክርስትያን ሐዋርያዊ አገልግሎት እንዲሰጡ እና እግዚአብሔር ሙያቸው ባርኮ እንድያግዛቸው ቅድስነታቸው በጸሎታቸው እንደሚያስታውስዋቸው ገልጸውላቸውል በማለት ለካስተል ጋንዶልፎ የደረሰ ዜና አመልክተዋል።

በተለይ ለምስራቅ ቤተ ክርስትያን ጳጳሳት እንዳመለከቱት የወቅቱ የቤተ ክርስትያኒቱ ሁኔታ መልካም እንዳልሆነ ጠቅሰው ከሄሉ ኩሉ እግዚአብሔር ጳጳሳቱ ለሚሰጡት ሐዋርያዊ አገልግሎት እንዲረዳቸው ተመኝቶውላቸዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ባለፈው ቅርብ ግዜ በእስፓኛ ርእሰ ከተማ ማድሪድ የተካሄደው ዓለም ዓቀፍ የወጣቶች ዕለት አስታውሰው የኩላዊት ቤተ ክርስትያን ወጣቶች ምእመናን ከቤተ ለቤተ ክርስትያናቸው ያላቸው ፍቅር እና ከስዋ ጐን ተሰልፈው በዓለም አቀፍ ደረጃ ሰላም ለማስፈን ያላቸውን ፍላጎት መረዳት መቻላቸው አስገንዝበዋል።

የማድሪዱ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን የቤተ ክርስትያን ህልውና ያንጸባረቀ ማራኪ እና መነፈሳዊ ግንኙነት መኖሩ በዚሁ ከወጣቶች ጋር ያደረጉት ግንኙነት መርካታቸው በዓለም ዙርያ ለህዝቦች በአዲስ መልክ ቅዱስ ወንጌል ማብሰር ትልቅ ዕድል መሆኑ በነዲክትሶስ 16ኛ መግለጻቸው ይህ ከካስተል ጋንዶልፎ የመጣ ዜና ገልጸዋል።

በቅርቡ መዓርገ ክህነት የተቀበሉ ካህናቱ ለካህናት እና ምአመናንን መልካም አርአያ እንዲሆኑ መንፈሳውነት ቀዳሚ ዓላማቸው መሆኑ ጸሎት እንድያዘውትሩ ማሳሰባቸው ተያይዞ ተመልክተዋል።

ሁላችን የቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ሰዎች እዚህ ዓለም ላይ የክርስቶስ ምስክሮች እንደመሆናችን መጠን በየፊናችን ሙያዎቻችን በእግዚአብሔር እገዛ እና የመፈስ ቅዱስ ኀይል የተሳካ እንዲሆንልን አበክረን መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል በነዲክቶስ 16ኛ በማለት ከካስተል ጋንዶልፎ የደረሰ ዜና አስገንዝበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.