2011-09-16 09:21:55

የህንድ ጳጳሳት ሐዋርያዊ ጉብኝት እና የቦፖል ሊቀ ጳጳስ መግለጫ ፡




የህንድ ብፁዓን ጳጳሳት ቫቲካን ውስጥ ቪሲታ አድ ሊሚና ሐውርያዊ ጉብኝት እያካሄዱ መሆናቸው የሚታወስ ሲሆን ፡ የቦፓል ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ለኦ ኮርኖልዮ ወቅታዊ የህንድ ሁኔታ በተመለከተ መግለጫ ሲሰጡ ፡ ህንድ እጅግ ትልቅ ሀገር መሆንዋ ጠቁመው ፡ የተለያዩ ባህላች ሃይማኖቶች እና ቋንቋዎች አቀፍ መሆንዋ አመልክተው በሃብታሞች እና ድሆች ከፍተኛ ልዩነት እየተከሰተ መሆኑ ገልጸዋል።

የሀገሪቱ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን በየኢንዱ ሃይማኖት አክራሪዎች ችግር እየገጠማት መሆኑ እና ችግሩ በትዕግስት ለመወጣት እየጣረች መሆንዋ የቦፓል ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ለኦ ኮርነልዮ አመልክተዋል።

የኢንዱ ሃይማኖት አክራሪዎች ከዚህ ሃይማኖት ውጭ ክርስትና ኢስላም እና አይሁድነት እንደ እንግዳ ነገር በመቁጠር በነዚህ ሃይማኖት ላይ ችግር ሲፈጥሩ እንደሚታዩ ሊቀ ጳጳሱ አስገንዝበዋል።

አለመጣጣሙ ሃይሞናትዊ ሳይሆን ፖሊቲካዊ መሆኑም የቦፓል ሊቀ ጳጳስ በተጨማሪ አመልክተዋል።

ሆኖም ይላሉ ሊቀ ጳጳሱ ሀገሪቱ ነጻ እና ዲሞክራስያዊት ስለሆነች ሁሉም በነጻነት ሐሳባቸው ለመግለጽ ተክህሎ ስላላቸው ብዙ አዎንታዊ ነግሮችም አቀፍ መሆንዋ አስገንዝበዋል።

ህንድ ውስጥ ዲሞክራሲ ባይኖር ኖሮ እና ህዝቡ ሐሳቡ በጽሑፍ በቃል ለመገልጽ ባይችል ኖሮ ችግር በሆነ ነበር ብለዋል ሊቀ ጳጳሱ ።

የህንድ ኤኮኖምያዊ እድገት ለወጦቶች ተስፋ እየሰጠ መሆኑ እና ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኤኮኖሚ ተወዳዳሪ እሆነች መምጣትዋ ሃይሞኖት የግጭት መንስኤ ለማድረግ የፖሊቲካ ሰዎች የሚጫወቱት ሚና ሊቀነስ ብሎም ሊገታ ትችላል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ለጥቀው መግለጻቸው ታውቆዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.