2011-09-14 14:55:22

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ድርሰቶች ለትርኢት


እ.ኤ.አ. ከመስከረም 22 ቀን እስከ መስከረም 25 ቀን 2011 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በጀርመን የሚያካሂዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት ምክንያት በቅድሚያ በካስተል ጋንደልፎ ቅዱስነታቸው ለመንበረ ቅዱስ ጴጥሮስ RealAudioMP3 ከመሾማቸው በፊት ብፁዕ ካርዲናል ራትዚገር እና በመቀጠልም የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታዮ ሆነው ከተሾሙ ወዲህ የደረሱዋቸው ጥልቅ እና አበይት እንዲሁም ተከታታይ የጥናት መጻሕፍቶቻቸው ለሳቸው ክብር በካስተል ጋንዶልፎ እ.ኤ.አ. መስከረም 15 ቀን 2011 በመቀጠልም እ.ኤ.አ. መስከረም 16 ቀን 2011 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን በቅዱስ ተውቶኒኮ ሠፈር በጀርመንም በአገሪቱ የሚገኘው የሄርደር ማተሚያ ቤት ከቫቲካን ማተሚያ ቤት ጋር በመተባበር ለትርኢት እንደሚቀርብ ተገለጠ።

በተለያዩ ቋንቋዎች ተተርጉመው ለንባብ የበቁት የቅዱስ አባታችን ጥልቅ መጻሕፍት እ.ኤ.አ. መስከረም 24 ቀን 2011 ዓ.ም. በጀርመን ለትርኢት ለማቅረቡ የጀርመን ሄርደር እና የቫቲካም ማተሚያ ቤት በመተባበር የወጠኑት እቅድ ለቅዱስ አባታችን ምስጋና እና አክብሮት ያለመ መሆኑ ለማወቅ ሲቻል፣ እነዚህ የተለያዩ የቅዱስ አባታችን ድረሰቶች በተለያዩ ቋንቋዎች ተተርጉመው ለንባብ የበቁት መጻሕፍት እንዲህ ባለ መልኩ ለትርኢት ማቅረብ በርግጥ ለሁሉም አቢይ ደስታ የሚሰጥ መሆኑ የቫቲካን ማተሚያ ቤት አስተዳዳሪ ክብሩ አባ ጁዜፐ ኮስታ መርሃ ግብሩ በማስደገፍ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.