2011-09-14 14:57:01

25ኛው የኢጣሊያ ብሔራዊ የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ


“ጌታ ሆይ ወደ ማን እንሄዳለን? ቅዱስ ቁርባን በዕለታዊ ሕይወት” በሚል ርእስ ሥር በኢጣሊያ አንኮና ከተማ እ.ኤ.አ. ከመስከረም 3 ቀን 2011 ዓ.ም. እስከ መስከረም 11 ቀን 2011 ዓ.ም. 25ኛው ብሔራዊ የቅዱስ ቍርባን ጉባኤ መካሄዱ RealAudioMP3 የሚዝከር ሲሆን፣ ይህ የተካሄደው የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ በቅንፍ የሚባል ወይንም ትኵረትን ለማዛባት ሳይሆን ቤተ ክርስትያን የወለደው እርሷን በመሠረተው ቅዱስ ምሥጢር ፊት ኣረፍ ተብሎ ምሥጢሩ የተስተነተነበት እንደነበር ጌታ ሆይ ከእኛ ጋር እደር (ሉቃ. 24 ቍ.29) በሚል ርእስ ሥር በተጠናቀረው የጉባኤው የማጠቃለያ ሰነድ ዘንድ ተመልክቶ ይገኛል።

በጠቅላላ ስለዚሁ ባለፈው እሁድ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክስቶስ 16ኛ በመሩት እና ስለ ቅዱስ ቁርባን ሥልጣናዊ ትምህርት በሰጡበት መሥዋዕተ ቅዳሴ የተጠናቀቀው 25ኛው ብሔራዊ የቅዱስ ቍርባን ጉባኤ በማስመልከት የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የማስታወቂያ እና የሕዝብ ግኑኝነት ጉዳይ ምክትል ተጠሪ ክቡር አባ ኢቫን ማፈይስ ከቫቲካን ራዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በኢጣልያ ባሪ ከተማ የተካሄደው 24ኛው ብሔራዊ የቅዱስ ቍርባን ጉባኤ፣ እኛ ክርስትያኖች አለ ሰንበት ለመኖር እንደማንችል አበክሮ ሲያስገነዝብ ይህ 25ኛው የአንኮና ብሔራዊ የቅዱስ ቍርባን ጉባኤ ክርስትና በሰንበት ሕይወት የሚታጠር ወይንም የሰንበት ሕይወት ብቻ ሳይሆን፣ ዕለት በዕለት የሚኖር መሆኑ አበክሮ ያስተምራል። በዚሁ ጉባኤ አስተምህሮ ያቀረቡት ብፁዓን ጳጳሳት በጠቅላላ ሁላችን በዚህ ጥልቅ ቅዱስ ምሥጢር ፊት ገዛ እራሳችንን በማኖር ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድሚያ በመስጠት በዕለታዊ ሕይወታችን ዕለታዊ እንቅስቃሴአችን ክንዋኔያችን በጠቅላላ በአኗኗር ሥልታችን ከሌሎች ጋር ባለን ግኑኝነት የሚለንን በማዳመጥ እና ፍቃዱን በመከተል መኖር ማለት መሆኑ አስምረውበታል።

በእንተ ላእለ ኩሉ ቤተ ክርስትያን ዳግም ከእምነት ጋር መገናኘት እና የእምነት ጣዕም ዳግም በማጣጣም በሕይወታችን ከሌሎች ጋር ባለን ግኑኝነት መሠረት ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት የተጠራን መሆናችን ያስገነዘበ እና ይኸንን ክርስትያናዊ አመክንዮ ዳግም ያነቃቃ ጉባኤ መሆኑ ገልጠው፣ በቅዱስ ቁርባን ፊት በግል እና በኅብረት በጽሞና ጥልቅ ምሥጢሩን ማስተንተን መጸለይ ማምለክ ብሎም ቅዱስ ምሥጢሩን ዕለት በዕለት መኖር ያስገነዘበ እና ያስተማረ ጉባኤ ነበር በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.